[መጽሐፍ ቅድስ] እስማኤላውያን ሳዑዲ እና ኢራን ግንኙነታቸውን ወደነበረበት ለመመለስ ተስማሙ!

✍ ዘርአዳዊት ዘ-ኢትዮጵያ 

እስማኤላውያን እንደገና ተገናኙ፤ ሳዑዲ እና ኢራን ግንኙነታቸውን ወደነበረበት ለመመለስ ተስማሙ

እርሱን ( እስማኤልን ) ታላቅ ሕዝብ አደርገዋለሁ = 'አንድ' የበዳ አህያን የሚመስል የክርስቶስ ተቃዋሚ ሕዝብ፤ 'እጁ በሁሉም ላይ ይሆናል የሁሉም እጅ ደግሞ በእርሱ ላይ ይሆናል' … ቃል ኪዳኔን ግን በሚመጣው ዓመት በዚሁ ጊዜ ሣራ ከምትወልድልህ ከይስሐቅ ጋር አቆማለሁ።

ዛሬ የምናየውና ባለፉት ፲፻፬፻/ 1400 ዓመታት ውስጥ የሆነውም ይኸው ነው።

ሁሉም ሃጋራውያን / እስማኤላውያን፤ ሳውዲ አረቢያ፣ ኢራን፣ ቱርክ፣ ግብጽ፣ አልጀሪያ፣ ሱዳን፣ ሶማሊያ፣ ኳታር፣ ኤሚራቶችና እስራኤል ዘ-ስጋ (የስጋ ማንነትና ምንነት ያላቸው ሃጋራውያን/ እስማኤላውይን) ታቦተ ጽዮንን ለመፈለግ በአክሱማዊቷ ኢትዮጵያ ላይ ዘምተዋል፤ በድጋሚም ለመዝመት ከፍተኛ ዝግጅት በማድረግ ላይ ናቸው።

[ኦሪት ዘፍጥረት ምዕራፍ ፲፮]

፲፩ የእግዚአብሔር መልአክም አላት። እነሆ አንቺ ፀንሰሻል፥ ወንድ ልጅንም ትወልጃለሽ፤ ስሙንም እስማኤል ብለሽ ትጠሪዋለሽ፥ እግዚአብሔር መቸገርሽን ሰምቶአልና።
፲፪ እርሱም የበዳ አህያን የሚመስል ሰው ይሆናል፤ እጁ በሁሉ ላይ ይሆናል፥ የሁሉም እጅ ደግሞ በእርሱ ላይ ይሆናል፤ እርሱም በወንድሞቹ ሁሉ ፊት ይኖራል።
፲፫ እርስዋም ይናገራት የነበረውን የእግዚአብሔርን ስም ኤልሮኢ ብላ ጠራች፤ የሚያየኝን በውኑ እዚህ ደግሞ አየሁትንብላለችና።

[ኦሪት ዘፍጥረት ምዕራፍ ፲፯]

 እግዚአብሔርም አብርሃምን አለው። የሚስትህን የሦራን ስም ሦራ ብለህ አትጥራ፥ ስምዋ ሣራ ይሆናል እንጂ።
፲፮ እባርካታለሁ፥ ደግሞም ከእርስዋ ልጅ እሰጥሃለሁ፤ እባርካትማለሁ፥ የአሕዛብም እናት ትሆናለች፤ የአሕዛብ ነገሥታት ከእርስዋ ይወጣሉ።
፲፯ አብርሃምም በግምባሩ ወደቀ፥ ሳቀም፥ በልቡም አለ። የመቶ ዓመት ሰው በውኑ ልጅ ይወልዳልንዘጠና ዓመት የሆናትም ሣራ ትወልዳለችን?
፲፰ አብርሃምም እግዚአብሔርን። እስማኤል በፊትህ ቢኖር በወደድሁ ነበር አለው።
፲፱ እግዚአብሔርም አለ። በእውነት ሚስትህ ሣራ ወንድ ልጅን ትወልድልሃለች፥ ስሙንም ይስሐቅ ብለህ ትጠራዋለህ፤ ከእርሱ በኋላ ለዘሩ የዘላለም ቃል ኪዳን እንዲሆን ቃል ኪዳኔን ከእርሱ ጋር አቆማለሁ።
 ስለ እስማኤልም ሰምቼሃለሁ፤ እነሆ ባርኬዋለሁ፥ ፍሬያምም አደርገዋለሁ፥ እጅግም አበዛዋለሁ፤ አሥራ ሁለት አለቆችንም ይወልዳል፥ ታላቅ ሕዝብም እንዲሆን አደርገዋለሁ።
፳፩ ቃል ኪዳኔን ግን በሚመጣው ዓመት በዚሁ ጊዜ ሣራ ከምትወልድልህ ከይስሐቅ ጋር አቆማለሁ።
Share on Google Plus

ስለ የተለጠፈበት ቀን

    Blogger Comment
    Facebook Comment