✍ ዘርአዳዊት ዘ-ኢትዮጵያ
በአክሱም ጽዮን ታቦተ ጽዮንን ለመከላከል ሲሉ አንድ ሺህ የሚሆኑ አባቶቻችንና እናቶቻችን የሰማዕትነትን አክሊል ተጎናጽፈዋል። የቤተ ክህነት ፈሪሳውያንና የህወሓት ከሃዲዎች ስለ ጽዮን ዝም ብለዋል። የሰማዕታቱን መታሰቢያ ለማስታወስ እንኳን ፈቃደኞች አይደሉም። የሠሯቸውን ግፎችና ወንጀሎች ፶ ዓመታት ያህል ሲያደርጉት እንደነበረው እንዲሁ ሸፋፍነው የሚያልፏቸው ይመስላቸዋል። አሁን በጭራሽ አይሆንም፤ እያንዳንዳቸው ተገቢውን ከባድ ቅጣት ይቀበሉ ዘንድ ግድ ነው!
❖ ታቦተ ጽዮንን ፍለጋ ❖
አሜሪካ በአክሱም ጽዮን ላይ ጂሃድ ያካሂዱ ዘንድ ወታደሮችን በሶማሊያ፣ በጅቡቲ እና በኤርትራ በተቀናጀና ሥውር በሆነ መልክ ስልጠና በመስጠት ላይ ትገኛለች። እንግዲህ የአፍጋኒሳትን ሙጃህዲን/ታሊባኖችን፣ የአልኬይዳና አይሲሲ፣ የኢራቅና ሶርያ እንዲሁም የናይጄሪያውን ቦኮ ሃራምንና የሞዛምቢኩኑ አል-ሸባባ ጂሃዳውያንን የሚያሰለጥኗቸውና መመሪያ የሚሰጡትም እነ አሜሪካ፣ አውሮፓ እና ዓረቦች ናቸው። ገንዘቡ ከእነ ሳውዲ፣ ኳታርና ዓረብ ኤሚራቶች ይፈልቃል። አሜሪካ ክርስቲያናዊ የሆኑ ወታደሮችን አታሰለጥንም፤ በኢትዮጵያም ያየነው ይህን ነው፤ አክሱም ጽዮናውያንን መጨፍጨፍና ማስጨፍጨፍ እንጂ በጭራሽ አትረዳም መርዳትም አትፈልግም። ከሰይጣን/የሰይጣን የሆኑትን ብቻ ነው ባቢሎን አሜሪካና አጋሮቿ የሚረዷቸው።
እንግዲህ ከአክሱም ጽዮን ጭፍጨፋ በኋላ አሜሪካ የያኔውን የሶማሊያ ፕሬዚደንትን ፎርማጆን አንስታ በአዲሱ ሰው የተካችው ፎርማጆን ከተጠያቂነት ለማዳን ስትል ነው። ልክ ዛሬ አረመኔዎቹን ወኪሎቿን ግራኝ አሕመድን፣ ኢሳያስ አብዱላ ሐሰንን እና ደብረ ጽዮንን ከተጠያቂነት ለማዳን እየሠራች እንዳለቸው።
ከ፭፻/500 ዓመታት በፊት ሶማሌዎች እና ጋላ-ኦሮሞዎች በኢትዮጵያ ክርስቲያኖች ላይ ጅሃድ እንዲያደርጉ በኦቶማን ቱርኮች የሰለጠኑ ሲሆን የዛሬ ፹/80 ዓመት ደግሞ በሙሶሎኒ ፋሺስት ኢጣሊያ - አሁን ደግሞ በቱርክ እና አሜሪካ በመሰልጠን ላይ ናቸው።
የጦር ወንጀለኞች ጎሳ ሚሊሻዎችን ወደ ሶማሌ ብሄራዊ ጥምረት መጨመር ለሁለቱም ወገኖች ትልቁ ስህተት ነው የሚሆነው። እ.ኤ.አ. በ 2004 ሲ.አ.ይኤ የታጠቁ እና የገንዘብ ድጋፍ የተደረገላቸው የጎሳ ሚሊሻዎች ንፁሀን ዜጎችን የገደሉ ሲሆን ይህም ከዚያም አልሸባብ አሸባሪ ድርጅት እንዲፈጠር ምክንያት ሆኗል ። ዛሬም ሉሲፈራውያኑ የብጥብጥ፣ ግርግርና ጥፋት ጌቶች በተደጋጋሚ ተመሳሳይ ስህተት በመሥራት ላይ ናቸው። ሊወድቅ የተዘጋጀ ኃይል ይቅበዘበዛል፤ ሁሉም ያምረዋል።
ከጽላተ ሙሴ እና "ከሌላ ጠፈር መጡ" ከሚሏቸው ባዕዳውያን ጋር በተያያዝ እ.አ.አ በ2012 የወጣውንና "Prometheus /ፕሮሜቴየስ" የተሰኘውን የሪድሊ ስኮት ፊልም እባክዎ ይመልከቱ። ሪድሊ ስኮት በሶማሌዎች ተመትቶ እንዲወድቅ የተደረገውን ሄሊኮፕተር አስመልክቶ 'Black Hawk Down' (2001) የተባለውን ፊልም የሰራ የፊልም ዳይሬክተር ነው። በዚህ ምንም የአጋጣሚ ነገር የለም!
Blogger Comment
Facebook Comment