አየ ቤተክርስቲያን የማንም ተኩላና ምንደኛ መጫወቻ ሆነሽ ትቀሪ⁉️


ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው

⚠️ እኔ እኮ አስቀድሜ "በዚህ ሰበብ መምታት የፈለጉትን አካል ለመምታት ነው እንጅ ሽኩቻው የውሸት ነው፣ አገዛዙ የሚያስተውነው ድራማ ነው፣ ሁለቱም ቡድኖች የአገዛዙ ታማኝ አገልጋዮች ናቸው፣ ሁለቱም ቡድኖች ከቀኖና ቤተክርስቲያን ውጭ የሆኑ ወይም ቀኖና ቤተክርስቲያንን ሽረው የመጡ ስለሆኑ አንዱ በሌላው ላይ 'ቀኖና ቤተክርስቲያንን ሽረሃል!' ብሎ ጣቱን የመቀሰር ወይም የመክሰስ የሞራል ልዕልናና መብት የለውም.... !" ወዘተረፈ. ብያቹህ ነበረ እኮ‼️

👉 ይሄው ድራማ የመሆኑ ማሳያው አወኩ በጠበጡ የተባሉቱ ቅድስት ቤተክርስቲያንን በእጅጉ እስከ ማዋረድ የደረሰ፣ በርካታ ምእመናንን እስከ ማስገደል፣ ማፈናቀል፣ ማሰደድ፣ ማሳሰር፣ የአካል ጉዳተኛ ማድረግ ወዘተረፈ ድረስ የደረሰ ከፍተኛ ጉዳትና ኪሳራ በቤተክርስቲያን ላይ ያደረሱ ሆነውና ከዚህም ነፍስ እስከማስጠፋትና መቅደስ ውስጥ የማያምኑ ሰዎችን በጫማ አስገብቶ መቅደሱን እስከማርከስ ድረስ የደረሰ ከፍተኛ ጥፋታቸው የተነሣም ክህነታቸው (በትክክል ክህነቱ ከነበራቸው ማለቴ ነው) በበርካታ የፍትሕ መንፈሳዊ አንቀጾች ወይም ድንጋጌዎች ክህነታቸው የፈረሰ ወይም የተሻረ ሆኖ ሳለ ምንም እንዳልተፈጠረና ቀኖና ቤተክርስቲያንን በተላለፈ አሠራር በአንድ ደብዳቤ "ውግዘቱ ተነሥቶላቹህ በቀደመ ክህነታቸው እንድታገለግሉ ተወስኗል!" ተባለላቹህ‼️

🤔 ቀኖና ቤተክርስቲያን ባይፈቅድላቸውም ለማስመሰል እንኳ "ቀኖና ወይም ንስሐ ተሰጥቷቸዋል ቀኖናቸውን ሲጨርሱ ክህነታቸው ተመልሶላቸው ወደቀደመ አገልግሎታቸው የሚመለሱ ይሆናል!" አላሉም‼️

🔔 አንዳንድ የዋሃን ይሄንን እጅግ የተሳሳተ የሲኖዶስ ተብየውን ቀኖና የጣሰ ውሳኔ ወይም እርምጃ "ለቤተክርስቲያን ሰላምና አንድነት ሲባል ነው!" ትሉት ይሆናል። ሰላም የሚገኘው ግን ከእግዚአብሔር እጅ እንጅ ከዐመፃ ልጆች እጅ አይደለም። ሰላምን ከእግዚአብሔር እጅ መፈለግን ትተን እግዚአብሔርን አስቀይመን ወይም የእግዚአብሔርን ሕግ ተላልፈን ከዐመፃ ልጆች እጅ ለማግኘት የፈለግን ጊዜ ሰላምን መቸም ላናገኛት ከእኛ እንድትርቅ እናደርጋታለን እንጅ ፈጽሞ አናገኛትም‼️

📌 ዳሩ ይሄ ሁሉ ከላይ እንዳልኳቹህ አገዛዙ ለራሱ ዕኩይ ዓለም ካድሬ ጳጳሶቹን ለሁለት ከፍሎ ያስተወነው ድራማ ነበር እንጅ የእውነት ሽኩቻ አልነበረም። እንዲያው ለነገሩ የተታለላቹህ ምእመናንን አፍ ለማዘጋት ብየ ሰላምን ከእግዚአብሔር እጅ እንጅ ከዐመፃ ልጆች እጅ ልንሻ አይገባም አልኩ እንጅ እነሱስ በመሃከላቸው ፀብም፣ ሽኩቻም፣ መለያየትም አልነበረባቸውም እንዲተውኑ አገዛዙ የሰጣቸውን ገጸባሕርይ ተላብሰው ነው ሲተውኑ የሰነበቱት‼️

😭 አየ ወገኔ በዚህ ዘመን አባትና እረኛ ያለ መስሎህ ዝም ብለህ ትጃጃልልኛለህ‼️

✝️ ይብላኝልኝ እነሱ ባመጡት ድራማ በግፍ ለተገደሉት ወይም በከንቱ ደማቸው ፈሶ ቤተሰቦቻቸውን በትነው ደመከልብ ሆነው ለቀሩት፣ ለቆሰሉት፣ ታስረው ለሚሰቃዩት፣ ከሥራ ለተባረሩት ወዘተረፈ.‼️

✝️ አቤት ይሄ እግዚአብሔር ፈጽሞ እንደማይሰማና እንደማያይ ይሄንን ሁሉ ግፍ ተመልክቶና ቆጥሮ የፈረደ ጊዜ ፍርዱን ማን ይችለው ይሆን⁉️⁉️⁉️


Share on Google Plus

ስለ የተለጠፈበት ቀን

    Blogger Comment
    Facebook Comment