መጋቢት 7 | ጻድቁ ንጉሥ ቴዎድሮስ መታሰቢያው ነው!

 
አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም

👑 + ጻድቁ ንጉሥ ቴዎድሮስ + 👑

በሃገራችን ታሪክ በጣም ተወዳጅ ከነበሩ ነገሥታት ጻድቁ ቴዎድሮስ ቅድሚያውን ይወስዳል። በርግጥ በርካቶቻችን የምናውቀው ስለ ሃገሩ ፍቅር ራሱን የሰዋውን ዳግማዊ ዐፄ ቴዎድሮስን (1845-1860) ነው::

በበጎ ሥራውና በቅድስና ሕይወቱ የተመሠከረለት ግን ዛሬ የምናስበው ቀዳማዊው ነው።

ቀዳማዊ ዐፄ ቴዎድሮስ የደጉ ዐፄ ዳዊት (ጒንደ መስቀሉን ያመጡት) እና የተባረከችው ሚስታቸው የፅዮን ሞገሳ ልጅና የጻድቁ ዐፄ ዘርዐ ያዕቆብ ታላቅ ወንድም ነው።

በኢትዮጵያ ለ3 ዓመታት (ከ1396-1399) ብቻ ነግሦ እያለ እንደ ንጉሥ ሳይሆን፦

● ከጠዋት እስከ ማታ ድሃ እንዳይበደል ፍርድ እንዳይጓደል ይታትር የነበር፣

● ጾምና ጸሎትን የሚያዘወትር፣

● ወገገቡን ታጥቆ ነዳያንን የሚያበላ፣

● ለአብያተ ክርስቲያናትም የሚጨነቅ ደግ ሰው ነበር።

ስለዚህም በሕዝቡ እጅግ ተወዳጅ ነበር። በነገሠ በ3 ዓመቱ ዐርፎ በዝማሬና በለቅሦ ሥጋውን ተሸክመው ሲሔዱ ወንዝ ተከፍሎላቸዋል። ከመቃብሩም ላይ ጸበል ፈልቋል::

ዘለዓለም ሥላሴ ደግ መሪና ሰላማዊ ዘመንን ያድሉን።


Share on Google Plus

ስለ የተለጠፈበት ቀን

    Blogger Comment
    Facebook Comment