የአሜሪካ መንግስት ቃል አቀባይ ኔድ ፕራይስ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት ተከታዮች ላይ እየተካሄደ ስላለው የዘር ማጥፋት ወንጀል ሲጠየቅ ስለ ሌላ ነገር በመቀበጣጠር ይመልሳል
✍ ዘርአዳዊት ዘ-ኢትዮጵያ
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት ተከታዮች ላይ ለተፈጸመው የዘር ማጥፋት ወንጀል አሜሪካ ከጀርባ እንዳለችበት አቶ ኔድ ፕራይስ አረጋግጦልናል!
የ፳፩/21ኛው ክፍለ ዘመን አስከፊው የጅምላ ጭፍጨፋ የፈጸመው አረመኔ የኖቤል የሰላም ተሸላሚ ዐቢይ አሕመድ ዓሊ ፥ ከሂትለር በኋላ በአሜሪካ አስተዳደር የሚደገፍ እጅግ ክፉው 'መሪ' ነው።
አሜሪካ ግን ከዚህ አረመኔ ኦሮሞ አገዛዝ ጋር ለመስራት ፈቃደኛ ነች። ምክኒያቱም፤ አሜሪካ ፀረ-ኦርቶዶክስ፣ ፀረ-ኢትዮጵያ፣ ፀረ-ግዕዝ ባጠቃላይ የክርስቶስ ተቃዋሚ ስለሆነች ነው። አሜሪካ፤ ብልጽግና ኦነግን፣ ህወሓትን፣ ሻዕብያን፣ ብአዴንን፣ ኢዜማን፣ አብንን እና ሌሎች ብዙ ቡድኖችን በመጠቀም ነው በአክሱማዊቷ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ክርስቲያኖች ላይ የዘር ማጥፋት ወንጀል በመፈጸም ላይ ያለችው። ለዚህም ነው "በስምምነት ስም" ሁሉም ነገር ታፍኖ እንዲቀርና ወደ ተጠያቂነት የሚወስዱ መረጃዎች እንዲጠፉ ከሁሉም ከሃዲ ቡድኖች ጋር አሜሪካ በመስራት ላይ ያለችው። አሜሪካም ተጠያቂ ናትና። ሰሜን እዝ ቅብርጥሴ ድራማ በጂቡቲ ተቀማጭነት ያለው የአሜሪካ ሰራዊት ያቀነባበረው ድራማ ነው። ጦርነቱም ልክ እንደጀመረ ወደ ባሕር ዳር እና አስመራ ተተኩሰው የነበሩት ሮኬቶች የአሜሪካ ሰራዊት (የእነ ደብረጽዮን ሰዎችም አሉበት) ከጂቡቲ የተኮሳቸው ሮኬቶች ናቸው። ፋሺስት ሙሶሊኒ ሰሜን ኢትዮጵያን በወረረበት ወቅት እንኳን የውጭ ሀገራት ጋዜጠኞች፣ አሜሪካውያን ጦር ግንባር ድረስ ተገኝተው ምስሎችን እያነሱ ይዘግቡ ነበር። ዛሬ ይህ ሁሉ ቴክኖሎጂ ባለበትና መላው ዓለም የአንዲትን ዝንብ እንኳን እንቅስቃሴ በቀላሉ ማየት በሚችልበት ዘመን ያው ለሦስት ዓመታት ያህል አንድም መረጃ ከትግራይ እንዳይወጣ ተደርጓል። ወደዩክሬይን ያለምንም ስጋት ሰተት ብሎ ለመግባት የበቃው ወስላታው የተመድ ዋና ፀሐፊ ጉቴሬዝ፤ "ዐቢይ አሕመድ ወደ መቐለ እንዳትሄድ ብሎ ከለከለኝ!" ብሎ ሳይሄድ ቀረ። አይይይ! ይህ የዘር ማጥፋት ወንጀል ሁሉንም ተጠያቂ ስለሚያደርጋቸው እኮ ነው ሁሉንም ነገር ለመደባበቅና ጊዜ ለመግዛት በጋራ በመስራት ላይ ያሉት።
Blogger Comment
Facebook Comment