🚫 አሁን እኮ የዋሃኑን የሚመስላቸው ሕዝበ ክርስቲያኑ በአንድ ድምፅ "እምቢ!" ብሎ ለቤተክርስቲያን በመቆሙ አገዛዙ ፈርቶ "የኦሮሚያና የብሔር ብሔረሰቦች ሲኖዶስ!" ብሎ የመሠረተውን የውሸት ሲኖዶስ ትቶ እነ አቶ አካለወልድን ለእነ አቦይ ማትያስ በማስረከብና የተቀሩትን 26ቱን ተሿሚዎችም ወደ ቀድሞ ማንነታቸው እንዲመለሱ የተስማማ ነው የሚመስላቸው‼️
🤔 እንደዚያ ነው አይደል የሚመስላቹህ⁉️
📌 ሲጀመር ተቃውሞ የመሰላቹህን ትዕይንት በዚህ መልኩ አስተባብሮና አቀናጅቶ ማን ከወነውና ነው እነ ጅሎ??? እራሱ አገዛዙ አይደለም ወይ አንድ የቀረ ሰው እንዳይኖር አድርጎ ከየጎሬው እያስወጣ ከአርቲስት እስከ ታዋቂ ሰው፣ ከፖለቲከኛ እስከ ምሁር፣ ከሚያምን እስከ የማያምንና የክልል መንግሥታት ተብየዎችንም እንኳ ሳይቀር እያስወጣ ለቤተክርስቲያን አጋርነታቸውን እንዲገልጹ እያደረገ በማስለፍለፍ ተቃውሞ የመሰላቹህን ትዕይንት የመራውና ያስተባበረው??? አገዛዙ እሱ እራሱ አስተባብሮ እራሱን እያስወገዘ ለቤተክርስቲያን አጋርነታቸውን እንዲገልጹ ያደረገው የድራማውን መጨረሻ በዚህ መልኩ እንደሚዘጋው ስለሚያውቅ ነው‼️
❓❓❓ለመሆኑ አገዛዙ በዚህ ድራማው ላይ ምን ዕኩይ ፖለቲካዊ ዓላማ እንዳሳካ ታውቃላቹህ⁉️
⚠️ ካድሬዎቹ እነ አቡነ አብርሃም አሁን ማምሻውን የስምምነት መግለጫቸውን ሲያነቡ እንደሰማቹሃቸው ለየ ብሔረሰቡ በየቋንቋው የሚያገለግለው ጳጳስ እንዲሾምለትና አገልግሎቱም በየቋንቋው እንዲሆንለት ስምምነት ላይ መደረሱን ሲገልጹ ሰምታቹሃቸዋል አይደል⁉️
❓❓❓ይሄ ምን ማለት ነው የሚመስላቹህ ለመሆኑ??? ይሄ ማለት ግእዝ ተሰናብቷል ማለት ነው እሽ??? ቅጥረኛው ሲኖዶስ ግእዝን ከአገልግሎት ውጭ ለማድረግ ተስማማ ማለት ነው እሽ እነ አህዮ??? ይሄ ነው ያስደሰታቹህ ታዲያ ምድረ የእፉኝት ልጅ??? በዚህም ስምምነት አሸባሪው አገዛዝ ግእዝን ከመላ ኢትዮጵያ የማጥፋትን ከምዕራባውያን የተቀጠረበትን ፕሮጀክት ሙሉ ለሙሉ አሳካ ማለት ነው። ምናልባት አንዳንዶቻቹህ ግእዝ በዚህ መልኩ አገዛዙ የአማራ ክልል ከሚለው የሀገራችን ክፍል ውጭ ካለው የሀገራችን ክፍል ቢሰናበትም የአማራ ክልል ከሚለው የሀገራችን ክፍል ግን ግእዝ የሚኖር ይመስላቹህ ይሆናል። ነገር ግን እዚህም ቢሆን ለምእመኑ ያዘኑ መስለው ካድሬ የአገዛዙ ካህናት አገልግሎቱ በግእዝ መሆኑ ቀርቶ በአማርኛ እንዲሆን በማድረን ግእዝን እንዲጠፋ ስለሚያደርጉትና ዋናው የዚህ በቋንቋ መገልገልን ሽፋን ያደረገው የአገዛዙ ተልእኮ በዚህ አሳቦ ግእዝን ማጥፋት በመሆኑ አማራም ላይ እንደዚህ አድርገው ያጠፉታል‼️
❓❓❓ግእዝ ጠፋ ማለት ምን ማለት እንደሆነ ይገባቹሃል ወይ ለመሆኑ??? ግእዝ ጠፋ ማለት ቅድስት ቤተክርስቲያን ከብሉይ ኪዳን ጀምሮ ከሰበሰበችው ዕውቀት፣ ትምህርት፣ ጥበብና አምልኮተ እግዚአብሔር ጋር ተቆራረጠች ማለት ነው። ይሄም ብቻ ሳይሆን ከድጓዋ፣ ከጾመ ድጓዋ፣ ከዝማሬዋ፣ ከመዋሥዕቷ፣ ከቅኔዋ ወዘተረፈ ጋር ተለያየች ተቆራረጠች ማለት ነው። ታዲያ "ቤተክርስቲያን ይሄንን ሁሉ አጥታ ሞታ ተቀበረች እንጅ ምኑን ቤተክርስቲያን ሆና ኖረች?" አትሉም??? አዎ አንዱ የአሸባሪው አገዛዝ በቋንቋ መገልገልን ሽፋን ያደረገው ስልታዊ ጥቃቱ ዓላማ ይሄ ነው‼️
👉 ሲጀመር አገዛዙን በዚህ ጉዳይ ላይ ምን አግብቶት፣ ምን ጥልቅ አድርጎት "ብሔረሰቦች የየራሳቸው ጳጳሳት ተሹሞላቸው በቋንቋቸው እንዲገለገሉ ይደረግ!" ምንንትስ እያለ ገብቶ ፈተፈተ??? አገዛዙን በዚህ ደረጃ በማያገባው ገብቶ እንዲፈተፍት ያደረጉት የቤተክርስቲያን ጠላት የሆነው አገዛዝ ቅጥረኞች ወይም ታማኝ አገልጋይ የሆኑት አስመሳይ ካድሬ ጳጳሳት ማለትም ሲኖዶስ ተብየው ነው⁉️
😣 አልገባቹህም እንጅ "ለየክልሉ ለየራሱ የየራሱን ሲኖዶስ በማቋቋም የአንድነት ኃይሉ የመጨረሻ ምሽግ የሆነችውን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያንን ፈረካክሶ ማጥፋትና የአንድነት ኃይሉ ህልውናው እንዲያከትም ማድረግ!" የሚለው የአገዛዙ ዕኩይ ዓላማም ተሳክቷል። ለየብሔረሰቡ የየራሱ ጳጳስ መሾሙና አገልግሎቱም በየቋንቋው እንዲሆንለት መደረጉ የሚገልጸው ይሄንን ነው። ክልሎቹ ወይም ብሔረሰቦቹ የግድ ሲኖዶስ የሚል ሥያሜ ካልተጠቀሙ ካላላቹህ በስተቀር ክልሎቹ ለአገዛዙ ጠንቀኛ የጎሳ ፖለቲካ ምቹ የሆነ የየራሳቸውን ሲኖዶስ እንዲያገኙ አድርጓል። ለዚህ የአገዛዙ የጥፋት ዓላማ ስኬት ተባባሪዎች ደግሞ የእግዚአብሔር ነፍስ በእጅጉ የምትጸየፋቸው እርጉሞቹ ካድሬ ጳጳሳት ወይም ሲኖዶስ ተብየው ነው‼️
❓ ምንድን ነው ታዲያ አገዛዙ ያጣው ወይም ያላሳካው ነገር⁉️
😡 አገዛዙ ከዚህም ሌላ እግር መንገዱን ቆሻሾቹን ጳጳሳት በመጠቀም በዚህ ድራማው አሳስቶ ማኖ ያስነካቸውን ለሀገር ተቆርቋሪ የሆኑ የአማራና የጉራጌ ባለሀብቶችን ለቃቅሞ አስሯል። ባለሀብቶችን ብቻ ሳይሆን ሌሎች ተቆርቋሪ ወገኖችንም ጭምር እያፈሰ አስሯል። ልብ በሉ እያልኩ ያለሁት አገዛዙ ቅጥረኞቹ መሆናቸው እንዳይነቃባቸውና ለሌላ ጊዜ የሕዝብን አመኔታ አግኝተውለት የቅጥረኝነት ሥራቸውን እንዲሠሩለት ለማድረግ ለይስሙላ ያሰራቸውን የሰንበት ትምህርት ቤት፣ የመንፈሳዊ ማኅበራት ኅብረት፣ የጴጥሮሳውያን የምንንትሴ የሚባሉ እነ ፌቨንንና ጓደኞቿን አስመሳይ የአገዛዙ ካድሬዎችና ቅጥረኞችን፣ እነ ምሕረተአብን ወዘተረፈ. አይደለም እያልኩ ያለሁት‼️
😭 እጅግ የሚያሳዝነው ነገር ቤተክርስቲያንን ከምንም ላያድኗት ነገር ለአገዛዙ አጀንዳ ወይም ለድራማው ማድመቂያ ሲባል ንጹሐን ማለቃቸው ነው። ሞታቸው መሥዋዕትነት ሆኖ ከእግዚአብሔር ዘንድ ዋጋ እንዳያሰጣቸው እንኳ ሟች ወገኖቻችን ቀኖና ቤተክርስቲያንን የማያውቁትን ወይም በወያኔ እንዲሻር አድርገው ሕገወጥ ፕትርክና የተሾሙትን እነ አቦይ ማትያስን ለቤተክርስቲያን የቆሙና ትክክለኛ ፓትርያርክ አድርገው በማሰብ እነ አቶ አካለወልድን እየተቃወሙ ከእነ አቦይ ማትያስ በስተቀር እንደማይቀበሉ እየተናገሩ አገዛዙን በመቃወም ነው በግፍ የተገደሉት። ስለሆነም እግዚአብሔር ሟች ወገኖቻችንን የሚያያቸው የወንበዴዎቹ የእነ አቦይ ማትያስ ደጋፊዎች አድርጎ ነው እንጅ የቀኖና ቤተክርስቲያን ደጋፊዎችና ለቤተክርስቲያን ቀኖና መጠበቅ ዋጋ የከፈሉ ሠማዕታት አድርጎ አይደለም የሚያያቸው። ነገር ግን እነኝህ ማቾች እነ አቦይ ማትያስም ቀኖና ቤተክርስቲያንን የሻሩ ሕገወጥ ተሿሚዎች መሆናቸውን ሳያውቁ እንደትክክለኛ አባት ቆጥረው የተሠው ካሉ ግን ፈጣሪ እነሱን ሳያውቁ የተሠው ናቸውና ሠማዕታት አድርጎ የሚቀበላቸው ይመስለኛል‼️
🔴 ለማንኛውም ለአገዛዙ ድራማ ድምቀት ሲባል በግፍ የተገደሉ የንጹሐን ወገኖቻችንን ደም የንጹሐን አምላክ ለዚህ የአገዛዙ ድራማ ድምቀት እንዲገደሉ ካደረጓቸው ቅዱስ ቃሉ አስቀድሞ "ለመንጋው የማይራሩ ጨካኞች!" ሐዋ. 20፤29 ሲል ከገለጻቸው ከምንደኞቹ እርጉማን ካድሬ ጳጳሳት እጅ የሚቀበል ይሆናል‼️
😭 ሳልናገረው ማለፍ የማልፈልገው ነገር ብሔረሰቦች በየቋንቋቸው እንዲገለገሉ ሲደረግ የሚያመጣው ጣጣ ከላይ የተገለጸው ብቻ አይደለም። ባዕዳን አማልክት የእግዚአብሔርን ቦታ ወስደው በእግዚአብሔር ቤተመቅደስና መንበር ፊት የመጠራትን፣ የመወደስን፣ የመቀደስን፣ የመከበርን፣ የመመለክን የሰይጣን መንገድንም ይከፍታል። ለምሳሌ በተደጋጋሚ ጊዜ አንሥቸዋለሁ በኦሮምኛ ፈጣሪ ለማለት ዋቃ ተብሎ የሚጠራው ስም የዋቄፈታ ወይም የዋቄፈና ባዕድ አምልኮ ጥቁር ባዕድ አምላክ ስም ነው። በዋቄፈታ ፈጣሪ ተብሎ የሚጠራው የዚህ ባዕድ አምላክ ማንነት፣ መገለጫ እንዲሁም አስተምህሮ እና የእግዚአብሔር ማንነት፣ መገለጫ እንዲሁም አስተምህሮ ፈጽሞ የተራራቀና የሚቃረን ነው። የዋቄፈታው ጥቁር ባዕድ አምላክ ዋቃ ገነትና ሲዖል ወይም ሲሞቱ ለፍርድ መቅረብ የሚባል ነገርን አያውቅም። ስለ እግዚአብሔር ልጅ ክርስቶስ ምንም የሚያውቀው ነገር የለም ወይም አያምንም። ስለሆነም እግዚአብሔርን ዋቃ ብለን ልንተረጉም አንችልም። እግዚአብሔርን ዋቃ ብለን ከተረጎምን ባዕድ አምላክን እያስመለክን መሆናችን እንደሆነ መታወቅ አለበት። እንዳለመታደል ሆኖ እየሆነ ያለው ግን ይሄ ነው። በኦሮምኛ ሲቀድሱ የዚህን ጥቁር ባዕድ አምላክ ወይም የሰይጣን ስም እየጠሩ ነው የሚቀድሱት። እንዴት ዓይነት ሀገርንና ሕዝብን ለመዓት ለቅስፈት የሚዳርግ እጅግ ድፍረት የተሞላበት የእርኩሰት ሥራ እየተሠራ እንደሆነ ልብ በሉ‼️
✝️ እግዚአብሔር የሚለው ቃል አማርኛ አይደለም የግእዝ ቃል ነው። ይሁንና ግን አማርኛ ወስዶ ይጠቀምበታል። ግእዝም የሚጠቀምባቸውን የጌታን ስሞች እንዳለ ከዕብራይስጥ ወስዶ ነው የሚጠቀምባቸው። ለምሳሌ አማኑኤል፣ ኢየሱስ፣ ክርስቶስ። እግዚአብሔር የሚለው ስም እግዚአ ከሚልና ብሔር ከሚል ቃላት ጥምረት የተገኘ የፈጣሪ ስም ነው። ትርጉሙም እግዚአ ማለት ጌታ ማለት ሲሆን ብሔር ማለት ደግሞ ሀገር ማለት ነው። ሀገር የሚለው ቃል የሚወክለው አንድን ሀገር ሳይሆን በእንግሊዝኛው Universe የሚለውን አጠቃላዩን ፍጥረተ ዓለም አንድ አድርጎ ቆጥሮ ነው ሀገር ያለው። ቤተክርስቲያን ስለ እግዚአብሔር ማንነት መገለጫና አስተምህሮ የምትሰጠውን ትምህርት የምታውቁት ነው። አንድም እግዚአብሔር ማለት እግዚ፣ አብ፣ ሔር ከሚሉ ቃላት ጥምረት የተገኘ ስም ነው። እግዚእ ማለት ጌታ ወይም ወልድ ሲሆን፣ አብ ደግሞ አባት ማለት ነው፣ ሔር ደግሞ ቸር ማለት ሲሆን ቸር ተብሎ የሚገለጸውን መንፈስ ቅዱስን ይወክላል። ስለሆነም እግዚአብሔር ማለት አብ ወልድ መንፈስቅዱስ ማለት ነው‼️
✝️ እግዚአብሔር የሚለው ቃል አማርኛ አይደለም የግእዝ ቃል ነው። ይሁንና ግን አማርኛ ወስዶ ይጠቀምበታል። ግእዝም የሚጠቀምባቸውን የጌታን ስሞች እንዳለ ከዕብራይስጥ ወስዶ ነው የሚጠቀምባቸው። ለምሳሌ አማኑኤል፣ ኢየሱስ፣ ክርስቶስ። እግዚአብሔር የሚለው ስም እግዚአ ከሚልና ብሔር ከሚል ቃላት ጥምረት የተገኘ የፈጣሪ ስም ነው። ትርጉሙም እግዚአ ማለት ጌታ ማለት ሲሆን ብሔር ማለት ደግሞ ሀገር ማለት ነው። ሀገር የሚለው ቃል የሚወክለው አንድን ሀገር ሳይሆን በእንግሊዝኛው Universe የሚለውን አጠቃላዩን ፍጥረተ ዓለም አንድ አድርጎ ቆጥሮ ነው ሀገር ያለው። ቤተክርስቲያን ስለ እግዚአብሔር ማንነት መገለጫና አስተምህሮ የምትሰጠውን ትምህርት የምታውቁት ነው። አንድም እግዚአብሔር ማለት እግዚ፣ አብ፣ ሔር ከሚሉ ቃላት ጥምረት የተገኘ ስም ነው። እግዚእ ማለት ጌታ ወይም ወልድ ሲሆን፣ አብ ደግሞ አባት ማለት ነው፣ ሔር ደግሞ ቸር ማለት ሲሆን ቸር ተብሎ የሚገለጸውን መንፈስ ቅዱስን ይወክላል። ስለሆነም እግዚአብሔር ማለት አብ ወልድ መንፈስቅዱስ ማለት ነው‼️
Blogger Comment
Facebook Comment