ስፔን ሴቶ ዜጎቿ የሚከፈልበት የወር አበባ ፈቃድን ያገኙ ዘንድ በሕግ ያጸደቀች የመጀመሪያዋ የአውሮፓ ሀገር ሆነች!


✍ ዘርአዳዊት ዘ-ኢትዮጵያ 

ይህ በእውነት በጣም ጥሩ ነገር ነው። በመላው ዓለም በሥራ ላይ መዋል ያለበት ሕግ ነው። እስካሁንም አልመተግበሩ የሚያስገርም ነው። ከእርግዝና እስከ ወር አበባ የሴቶች ሸክማቸው በጣም ብዙ ነው፤ ይሳዝኑኛል።

በተረፈ፤ "የወር አበባ" የሚለውን ቃል እንዲህ በጣም ቆንጆ በሆነ መልክ የሚጠቀም የዓለማችን ብቸኛ ቋንቋ ኢትዮጵያኛችን ነው። የብዙ ሃገራት ዜጎችን በተለይ ለሴቶች ስለዚህ ቃል ስነግራቸው በመገረምና ደስ በመሰኘት ነው ምላሹን የሚሰጡት። በእነዚህ ሁለት ቃላት የእኅቶቻችንን ወርሃዊ ሥነ ሥርዓት የሰየሙት አባቶች ወይንም እናቶች ፥ "ወታደሮቻችንን በሳንጃ፣ ሴቶቻቸው ግን በወንድ ነው የተደፈሩት!" እያለ ከሚሳለቀው ከዚህ የኢትዮጵያ ማሕፀን ካልወደችው መጤ አውሬ የሰማይና መሬት ያህል ልዩነት እንዳላቸው ይጠቁመናል። የቀደሙት አባቶችና እናቶች እጅግ በጣም የተሻሉ ናቸውና፤ ምስጋና ይገባቸዋል።

Share on Google Plus

ስለ የተለጠፈበት ቀን

    Blogger Comment
    Facebook Comment