በሰሜን ኢትዮጵያ ላይ የተከፈተው ጦርነት ዋና ዋና ዓላማዎች


✍ዘርአዳዊት ዘ-ኢትዮጵያ 

 “ረጅም እድሜ የሚያስገኘው የውሃ ምንጭ የሚገኘው በኢትዮጵያ ነው”።

ኮሮና ቫይረስ – ኦክስጅን – እስትንፋስ – ዕጣን — የሕይወት ዛፍ

በሰሜን ኢትዮጵያ ላይ የተከፈተው ጦርነት ዋና ዋና ዓላማዎች፤

❖ ጥንታዊውን የአዳም ዘር ለማጥፋት

❖ ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነትን ለመዋጋት

❖ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ክርስትናን ለማዳከም

❖ የሕይወት ዛፍን ለመቁረጥ (አዲስ የ’ሰው’ዘር ለመፍጠር)

❖ የዕጣንና ከርቤ ዛፎችን ለማጋየት (እንደ ኮሮና ላሉ ወረርሽኞች ፈውስ ስለሆኑና ክትባትን እንዳይፎካከሩ)

❖ የወርቅና ሌሎች ማዕድናት መገኛዎቹን ለማቆሸሽ (ዛሬ ወርቅ በጣም ተፈላጊ ነው)
❖ የጤፍ ዘሮችን ለማጥፋት (ዛሬ ጤፍ በጣም ተፈላጊ ነው)

❖ ውሃዎቹን (የጥምቀትና ፈውስ ጠበሎቹን) ለመበከል ብሎም ለማድረቅ። “የታሪክ አባት” በመባል የሚታወቀው ዝነኛው የግሪክ ዓለማዊ ፈላስፋ፤ ሄሮዶትስ እንኳን ከሁለት ሺህ ዓመታት በፊት እንዲህ ሲል ተናግሮ ነበር፤ “ረጅም እድሜ የሚያስገኘው የውሃ ምንጭ የሚገኘው በኢትዮጵያ ነው”።

መልካምንና ክፉን መለየት የሚያስችለው ‘የሕይወት ወይም የእውቀት ዛፍ‘ እንዲሁም የዕጣንና የክርቤ ዛፎች ብሎም የወርቅ ኮረብታዎችብዙ ቅዱሳን በሚገኙባት በአክሱማዊቷ ኢትዮጵያ ነው የሚገኙት። በሕክምናው ዓለም እንኳን ብዙ የመፈወስ ብቃት ያለው ዕጣን ከእነዚህ ምስጢራዊ ዛፎች መካከል አንዱና በተለይ ለወረርሽኞች የተፈጠረ ዛፍ ነው። በአክሱም ጽዮን ላይ የተከፈተው የዘር ማጥፋት ጦርነት የዛፎች፣ አትክልቶች፣ እጽዋትና የጤፍና ስንዴ ሰብሎችን ጤና አዳምን ወዘተ. የማጥፊያም ጦርነት ነው። ይህች ዓለም ከእግዚአብሔር ፍጥረት የተገኙ ጥንታዊ የሆኑ ነገሮች ላይ ጂሃድ አውጃለች። ሉሲፈራውያኑም ማን/ምን የት እነድሚገኝ ያውቁታል፤ በደንብ ደርሰውበታል።
አዎ! ዛሬ ከጽዮናውያን ጤፉን፣ ገብሡን፣ ሰሊጡን ፣ ስጋውን፣ ውሃውን፣ ማሩንና ወተቱን ሁሉ ሲነጥቁ፤ ጽዮናውያንን ግን በእርዳታ ስም፤ ምንነቱና ጥራቱ ለማይታወቅ የ‘ዩ.ኤስ.አይ.ኤይድ- USAID‘ ዱቄት ተገዥ ለማድረግ እየሠሩ ነው። አብዛኛው ኢትዮጵያዊ ደግሞ ለዚህ ከባድ ወንጀል ተባባሪ ለመሆን መብቃቱ እጅግ እጅግ በጣም ያሳዝናል። መሪ የለው፣ መምህር የለው፣ ጠባቂ የለው!!!

ሆኖም ሉሲፈራውያኑ ያቀዱት ሁሉ ከንቱ ሆኖ ይቀራል፤ ያው ዛሬ በመደናገጥ ላይ ናቸው፤ በመጨረሻ ምንም አይሳካላቸውም፤ ሁሉም ይወገዳሉ፤ ጥቂቶቹ የምንተርፈው ተፈጥሯዊ ህጉን እንደገና ለመከተል የምንበቃበት ጊዜ ሩቅ አይሆንም። እግዚአብሔር ይጠብቀን!

ጥር ፲ ቀን ፣ ፳፻፲፭ ዓም

Share on Google Plus

ስለ የተለጠፈበት ቀን

    Blogger Comment
    Facebook Comment