✍ ዘርአዳዊት ዘ-ኢትዮጵያ
በትግራይ አዲሱ ሉሲፈራዊ የዓለም ሥርዓት መመሥረት አይቻልም!
“ተዋሕዶ” ነን ለሚሉት “አባቶች” ሳይቀሩ ከተዋሕዶ ክርስትና ይልቅ 'ጎሣቸው' በልጦባቸዋል።
የኢትዮጵያ ተዋሕዶ ቤተክርስትያን የአውሬው አገልጋዮች ፖለቲከኞች የምዕራባውያን አሽከሮች መጫወቻ መሆን ከጀመሮች ፶ ዓመታት አልፈዋል። በዚህ ሳምንት ደግሞ በብልጽግና ፓርቲና በህወሓት ፓርቲ ኢትዮጵያንና መሰረትዋ የሆነቺው ቅድስት ተዋሕዶ ሃይማኖትዋ በመከፋፈል ለማጥፋት "የትግራይ ቤተ-ክህነት” እንደተመሰረት በመገናኛ ብዙሃን ተገልጿል።
የመጥፎ ትንቢት መፈጸሚያዎቹ 'ፖለቲከኞች' ሰይጣናዊ የአጽራረ ኢትዮጵያ አጀንዳ በግልጽ ፀረ እግዚአብሔር እና ፀረ ተዋሕዶ ክርስትና የሆነ ባሕርይ የለበሰ ነው። ያለንበት ዘመን ክፉ ስም ይዞ የሚያልፈው ባለዘመኖቹ እኛ በምንፈጽመው ክፉ ድርጊት በመሆኑ ሌሎቻችንም የትንቢቱ መፈጸሚያዎች እንዳንሆን በጊዜ ወደ ንስሓ ብንመለስ ይሻላል።
[ኦሪት ዘኍልቍ ምዕራፍ ፲፬፥፱]
“ነገር ግን በእግዚአብሔር ላይ አታምፁ፤ እንደ እንጀራ ይሆኑልናልና የምድሪቱን ሰዎች አትፍሩ፤ ጥላቸው ከላያቸው ተገፍፎአል፥ እግዚአብሔርም ከእኛ ጋር ነው፤ አትፍሩአቸው ብለው ተናገሩአቸው።”
ባጠቃላይ የኤዶማውያኑ ምዕራባውያን እና እስማኤላውያኑ ምስራቃውያን ዘላለማዊ ፖሊሲ ፀረ-ኢትዮጵያ ነው። የሁሉም ዓላማ “ኢትዮጵያ” የሚለውን መጠሪያ ከሀገረ ኢትዮጵያ ማጥፋት ነው። ከሰሜን ኢትዮጵያውያን (ኤርትራ) ቀጥሎ ትግራይን እና ዐምሐራን በራሳቸው “የብሔር” ሳጥን ውስጥ እንዲቆለፉና እግዚአብሔር የሰጣቸውን "ኢትዮጵያ" የሚለውን መጠሪያ እንዲክዱት ማድረግ ነው። በዐምሓሮች እና ተጋሩ ላይ የሚካሄደው ጭፍጨፋ የአማርኛንና ግዕዝ ቋንቋን ከማጥፋት ጋር በተያያዘ ካላቸው ተልዕኮ ጎን “ኢትዮጵያ” የሚለውን መጠሪያ ከኢትዮጵያውያን ማጥፋት ያለመ ነው ። ይህንን ሴራ ለእግዚአብሔር ቅርብ ናቸው ተብለው የሚታሰቡ የኃይማኖት አባቶች እንኳን ሊነቁበት አለመቻላቸው ያሳዝናል ። በተቃራኒው ዲያብሎስ ባዘጋጀው የብሔርተኝነት ወጥመድ ተጠምደዋል።
አይይ ወገኔ የዚህ የዲያብሎስ የግብር ልጅ እርኩስ መንፈስ (ግራኝ ዐቢይ አሕመድ) ገና በደንብ አልታያችሁም! ልክ እንደ መሐመድ፣ ሂትለርና ሙሶሊኒ በአጋንንት የቆሸሸ ነፍስ እንዳለው እኮ ዓይኑ በደንብ ያሳያል። እንግዲህ ይህ ሁሉ ጉድ ባለፉት ሃምሳ ዓመታት በተግባር ላይ እየዋለ የመጣ ሤራ ነው፤ ደርግን፣ ህወሓትን፣ አብዮት አሕመድን እና ደብረ ጽዮንን ጨምሮ ሁሉም በ666 መርፌ የተወጉት ባንዳዎች የተሳተፉበት ትልቅ የፀረ-ኢትዮጵያን ፀረ-ተዋሕዶ ሤራ ነው።
ትናንትና አውሬው አሁን ኤርትራ በተሰኘው ቦታ የሚገኙትን ሰሜን ኢትዮጵያውያንን ከአኩስም ጽዮን በመነጠልና ትግርኛ ተናጋሪ ኢትዮጵያውያንን እርስበርስ በማባላት ለጨረቃው አምላክ አሳነባሪዎችና ጊንጦች አሳልፎ ሰጣቸው።
ዛሬ ደግሞ በመሐል አገር የሚገኙትን ብሎም አማርኛ እና ትግርኛ ተናጋሪ ኢትዮጵያውያንን እርስበርስ በማባላት ከአክሱም ጽዮን ለመነጠልና ለዋቄዮ-አላህ ዘንዶዎችና አዞዎች አሳልፎ ለመስጠት ተግቶ በመስራት ላይ ይገኛል። ተዋሕዷውያንን ከአክሱም ጽዮን መነጠል የአውሬው ዋና ፍላጎት ነው!
ሁለቱን ድመቶች ያባሏቸውን ተንኮለኛ ቁራዎች እናስታውሳለን?
የአውሬው የጥንት ጠላታችን ዲያብሎሰ መሰረቱ አንድ ነው፤ መጠሪያ ስሙን፣ መልኩንና አካሄዱን እየቀያየረ ይመጣል እንጅ ማንነቱ/ምንነቱ፣ ዓላማውና ተግባሩ ሁሌም አንድ ነው። ማንኛቸውም ሃገራትና መንግስታት በኢትዮጵያ ጉዳይ አንድ አቋም ነው ያላቸው፤ የድሃ ሆነ የበለጸጉ ሃገራት መንግስት፣ አፍሪቃዊ ሆነ እስያዊ፣ አሜሪካዊ ወይም አውሮፓዊ ሁሉም ህልማቸው ኢትዮጵያ እንድትጠፋ ብቻ ነው። ምክኒያቱ አንድ እና አንድ ነው፤ በኢትዮጵያ ሃገራችን ከአባቶቻችን ዘመን ጀምሮ በጽናት የቆመች የርትዕት ተዋሕዶ እምነታችን በእግዚአብሔር መወደድ እና መመረጥ ዲያብሎስን እና ምድርን የከደኑ አለቃ እና መንዝሮቹ እጅግ ስላበሳጨ፣ ስላወከና የህልውናቸው ሁሉ አደጋ ስለሆነ ነው። ስለዚህ ዛሬ ገዢዎች ሁሉ በዓለም ላይ በዚሁ ክፉ ጠላታችን በዲያብሎስ ተመርቀውና ጸድቀው ስልጣን ላይ የተኮለኮሉና ለጥፋት የተሰማሩ ስለሆኑ ኢትዮጵያን ቢጠሉ፣ ኢትዮጵያን ለማፈራረስ ቢደክሙ፣ እምነታችንን እና የኢትዮጵያ ርትዕት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን ለማጥፋት ቢተጉ ፥ የተሰጣቸው የጨለማው ኃይላት ስራ ነውና፤ እነሱም ወደው ለሱ የተገዙ ናቸውና እኛ ልንገረም አይገባንም።
ኢትዮጵያ በእግዚአብሔር የተመሰረተችና በቅዱሳን ቃል ኪዳን የተጠበቀች፤ ከሁሉ በላይ ደግሞ የድንግል ማርያም አስራት አገር ስለሆነች እንኳን በአገር ዉስጥ ለጥፋቷ የተሰለፉ ፖለቲከኞችና አስመሣዮች አይደለም፤ እርሷን ለማጥፋት የተሰለፉ የዉጭ መንግሥታት ሰላቢ እጆች (Illuminati) በሙሉ በእግዚአብሔር ቁጣ ይጠፋሉ፤ ከምድር ይጠረጋሉ። እርሷ ግን በእግዚአብሔር መንግሥትነቷ እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ትቆያለች። ታዲያ አሁን ቢሆን “የአዲሲቷ ኢትዮጵያ መሪዎች ነን” እያሉ በተለይ ወጣቱ ግራ በማጋባት በኢትዮጵያና በኢትዮጵያዊነት ላይ የሚያላግጡ ፥ እርሷን ለማጥፋት የተሰለፉ የተለያዩ ቡድኖችና ድርጅቶች እንዲሁም መንግሥታትና ግለሰቦች ዛሬ ነገ ሳይሉ በእዉነተኛ ንስሐ ለእግዚአብሔር እጃቸዉን ቢሰጡና ወደማንነታቸዉ ወይንም ወደ ኢትዮጵያዊነታቸዉ ቢመለሱ የሚበጃቸዉ እንደሆነ በዚሁ አጋጣሚ መልእክቴን አስተላልፈለሁ።
ኢትዮጵያ እንኳን ዜጎቿን “ኢትዮጵያዉያን ነን” የሚሉትን ቀርቶ የዓለምን ሕዝብ ትመራለች ብንላችሁ “ኡ!ኡ!“ልትል ስለምትችሉ የንስሐ እድሜ ካገኛችሁ ተፈጽሞ እንደምታዩ እንነግራችኋለን።
ኢትዮጵያ ሆይ! እናት ሀገሬ! ትግሬነቴ በልጦብኝ አንቺን ረስቼሽ እንደኾን፡ ቀኜ ትርሳኝ!
ኢትዮጵያዊነት ታላቅ ክብር ነው!
የካቲት 3 ቀን ፣ 2014 ዓ/ም
Blogger Comment
Facebook Comment