"ወንድሞቼ ሆይ በዚያን ዘመን በምድር ኹሉ ላይ አዲስ ምሥጢርን አፈስሳለሁ ።ራሳቸዉን መነኩሳት ነን እኮ የሚሉ ስዎች ሕገ ምንኩስናን የማይጠብቁ ሐሰተኞች ናቸዉና ይኽንን ትተዉ መሪሩን የዓለምን ነገር ይከተላሉ። ቃሌን መዘበቻ ሕጌንም እንደ ከንቱ ነገረ ዘርቅ ይቋጥራሉ።
በዚያን ዘመን መሪዎችና ዐላዋቆች ጠቢባኑና ንጹሓኑ ርኩሳኑና አሳዳሪዉ አሽከሩና ድኻዉ ሀብታሙም ሕዝብና ባለሥልጣናቱም በሦስት ነገሮች አንድ ይኾናሉ። እሊኽም ኋጢአትና መሽሟጠጥ መታጀርም ናቸዉ።"ያን ጊዜ ሕዝቡ እንደ ካህኑ ካህኑም እንደ ሕዝቡ ይኾናል"። ካህኑም ከወይን ጠጅ የተነሣ ይፋንናል። ሐጢአታቸዉን እንደ ጽድቅ እቆጠሩ የሚዘብቱ ይበዛሉ ።
ዳግመኛም ሕዝቡም ካህኑም በፊቴ ቆመዉ ይለምኑኛል። እኔም አልመልስላቸዉም ።ዘወትርም ያመሰግኑኛል ትሕትናና ፍቅር የላቸዉምና ምስጋናቸዉም በእኔ ዘንድ ዋጋ አያሰጣቸዉም ።ይኼዉም ከጉድጓድ ዉስጥ ያለ ፍሬ እንደ አኖሩት ገለባ ነዉ ። እኔም እንዲሁ አደርጋቸዋለሁ። ጸሎታቸዉን አልሰማም። ዕጣናቸዉም ወደኔ አይደርስም ።
"ወንድሞቼ ሆይ በዚያን ዘመን በአንገቱ ጥቁር ቀሚስ የአጠለቀ ቁራ ይከብራልና ተጠንቀቁ።ቁራ የምላችሁም ቁራ አይደም። መንፈስ ቅዱስ ሳያድርባቸዉ ቀሲሳን የተሰኙ ወደ ቤተ ክርስቲያን የማይገሠግሡ ሰነፎችና ልግመኞች ከስብሐተ እግዚአብሔር (ከማሓሌት) ይልቅ ዓለማዊ ግብርን የሚወዱ ባልንጀራቸዉን የማይወዱ የዝሙት መንፈስን የሚከተሉ ኹለት ሚስቶችን የሚያገቡና ብዙ ሴቶችን የሚለምዱ በልባቸዉ ሕጌን የማያኖሩ ዓለማዊ ሥራን የሚወዱ ለወንዱም ለሴቱም በሐሰት እየሰበኩ እንደ ልባቸዉ ፈቃድ የሚኖሩ ስለ ቅዱስ ስሜ ክብር የሚያገለግሉ ናቸዉ።
"ያን ጊዜ ጥበብና ዕዉቀት እንደ ከንቱ ይቆጠራል ጠቢባን እንደ ሰነፎች ሰነፎችም እንደ ጠቢባን ይቆጠራሉና ።ያን ጊዜ መምህራን ያለቅሳሉ ደንቆሮች ይከብራሉ ሊቃውንት ይራባሉ። ከማስተዋል የራቁ ሰነፎች ይጠግባሉ።
"ወንድሞቼ ሆይ በዚያን ዘመን ውኋ ወደ ዳገት እንጂ ወደታች አይፈስስምና ተጠንቀቁ። ውኋ የምላችሁ ውኋ አይደለም የሰዉ ከንቱ ሐሳብ ነዉ እንጂ። በዚያን ዘመን ትንሹ ለታላቁ አይታዘዝም ። ወንድም ወንድሙን ወገን ወገኑን ይጠላል። ይዘላለፋሉ።ያን ጊዜ የጎበዝ አለቆች ይበዛሉ ።በሀይላቸዉ ታጅረዉ ይመካሉ።ሰዉንም ከትዉልድ መንደሩ አሳድደዉ ወደውጭ ያስወጡታል።"
"ከመጽሐፈ ፍካሬ ኢየሱስ" ገጽ 35 አና 39 የተወሰደ
""እህት ወንድሞቸ አንብበን ለመረዳት የእግዚአብሔርን መንፈስ ቅዱስ ይጎብኘን አሜን ይቆየን።
Blogger Comment
Facebook Comment