ከአምኃ ኢየሱስ ገብረ ዮሐንስ አሁንም ለሁለተኛ ጊዜ ድንገተኛና አስቸኳይ ትምህርታዊ መልእክት።

ከመልእክቱ በፊት ግን አጭር ምስጋና ለወልደ ገብርኤል ይድረስልኝ። ወንድማችን ወልደ ገብርኤል፦ የበቀደሙን የጽሑፍ መልእክቴን ከእኔ በላይ አሳቢ ሆነህ የሀገራችን ኢትዮጵያ አራቱ የዜማ ቅኝት ከሆኑት መካከል ምርጥ በሆነው በትዝታ ቅኝት በተቃኘ በሀገርኛ የትዝታ ዜማ በሆነ የመሣሪያ ድምፅ አጅበህ በመልቀቅህ መንፈሳዊ ምስጋናችን በጣም የላቀ ነውና እግዚአብሔር ይባርክህ፣ ከማያስተውሉት፣ ከማያስቡት፣ ከማያገናዝቡት፣ ከደናቁርት ማይም ስብስብ ይሰውርህ ያርቅህ። በእውነትና በእውቀት የማስተዋል መንገድ ይምራህ። እውቀት ማለትና የማንነት ባለቤት መሆን እንዲህ ነውና። እኔ ግን እንደተለመደው በመሣሪያ ድምፅ ሳላጅብ የለቀቅሁት አጭር መልእክት ስለሆነና አያስፈልገውም ብየ ነበር። አንተ ግን ደግ ሠራህ።ስሰማው በጣም ነው ደስ ያለኝ። የሀገርኛውን የትዝታ ዜማ አመራረጥ አውቀህበታልና። በተጨማሪ ይህንን መልእክት ግን በመንፈሳዊይም ሆነ በአለማዊ የድምፅ ማጀቢያ አትጀበው ተወው። ምክንያቱም መልእክቱም አጭር ነው። ደግሞም ሰዉ ሁሉ ሲያነብ ቪዲዮው እየቆመበትና እየቸኮለበት በደቂቃ ጥበቃ እንዳይቸገርና እንደፈለገ ወደ ታች ወደ ላይ እያመላለሰ እንዲያነበው ብየ በማሰብ ነው። በል ደህና ሁንልን። በተረፈ ግን ሰሞኑን ስለ ወንጌሉ ደላላ በጻፍኩት የተግሣጽና የእውነት መልእክት አማካኝነት ክፉ ርኩስ መንፈስ ፡ ቅዱስ መንፈስ መስሎ በልቦናቸው አድሮ የሚጫወትባቸውና የእሱ አጫፋሪ በመሆን በሲዖል የሚኖሩ የዲያብሎስ አሻሮ የሆኑ የስም ክርስቲያኖች እየጮሁና እየተንጫጩ ስለሆነ ጤነኞች የሆናችሁ፣ አእምሮና ልቦና ያላችሁ ክርስቲያኖች ምንም አይነት የአጸፋ መልስ እንዳትሰጧቸው። ምክንያቱም እነሱ ማለት ምንም ማለት ናቸውና። ዋናውና ትልቁ ነገር ደግሞ እነዚህ አሁን ክርስቲያን መስለው በስሜት ብቻ የሚንጫጩትና የሚብላሉት በዘመነኞቹ የወንጌል ደላላወች በሐሰት ዘር ተዘርተው የተወለዱና ያደጉ ስለሆኑ ባዶ ናቸው። በተጨማሪም እንደነዚህ አይነቶች የስም ክርስቲያኖች ሁሉ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በቅዱስ ቃሉ "እኔ የሕያዋን አምላክ ነኝ እንጅ የሙታን አምላክ አይደለሁም" ብሎ ከተናገረባቸው መሃል ናቸው። እነሱ ግን በስሜት መንፈስ የሚነዱ ስለሆነ ከምን ላይ እንደቆሙ ጨርሰው አያውቁትም። ስለዚህ ዝም ብላችሁ በመንፈሳዊ ኩራትና ንቀት እለፏቸው። ምክንያቱም አጫፋሪዎቹ ሁሉ እሱን ሊያድኑ ይቅርና ራሳቸውንም ማዳን የማይችሉ ምናምንቴዎች ናቸውና። ተጨማሪውን የተግሣጽ ዱላ ከታች ያገኙታልና ወደላይ ሳይሆን ወደታች ይውረዱ። ቃሌ ይገባቸው ይሆን? በሉ እንግዲህ ጤነኞች ክርስቲያን የሆናችሁት ቤተሰቦቼ ሁሉ ከቻላችሁ መርዷቸውን ስትሰሙ ውይ ውይ ውይ ምነው ምነው ምነው ከቶ ምኑ አገኛችሁ? አይይይይይይይ እያላችሁ እያጽናናችሁ ውጡ። በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ። ይድረስ ለተከበራችሁና ለተመረጣችሁ እውነተኛ አድማጮቼ ለሆናችሁት ክርስቲያኖች ሁሉ፦ በቅድሚያ እድሜ፣ ሰላምና ጤና......ለእናንተ ይሁን እያልኩ አሁን በቅርብ ቀናት ስለ ወንጌል ደላላው በጻፍኩት መልእክት አማካኝነት በውስጥ መስመሬ መልካም ነገር የጻፋችሁልኝ፣የተመኛችሁልኝ፣ የጠየቃችሁኝ፣ የነገራችሁኝ ኀዘናችሁ፣ቁጭታችሁ፣ብሶታችሁ፣ምኞታችሁ ሁሉ፣ እንዲሁም በግልሽ የድምፅ መልእክትሽን በከባድ የልመና ተማጽኖ እኔን ለማግኘት ብለሽ ያሰማሽኝ እህቴም የሁላችሁ መልእክት ደርሶኝ በሚገባ አይቸዋለሁ ሰምቸዋለሁ በጣም አመሰግናለሁ። መድኃኒዓለምና እናቱ ድንግል ማርያም በሥጋ በነፍስ ይባርኳችሁ። ግን አይዟችሁ ተረጋጉ አትጨነቁ፣ ጭንቀት ለአጉል ሕመም እንጅ ለንስሐ አያደርስምና እያልኩ ወደ ፍሬ ነገሩ እገባለሁ። ይኸውም፦ አብዛኞቻችሁ ክርስቲያን አድማጮቼ ሁሉ ከዚህ ላይ የእያንዳንዳችሁን ስም መጥቀስ ስለማልፈልግ ነው ይግባችሁ። እናም በጭንቀትና በተማጽኖ ላይ ሆናችሁ ከፊታችን ይመጣል ስለሚባለው ስለ ታላቁ ንጉሥ ቴዎድሮስ እውነታውን ከእኔ ለማወቅና መልስ ለማግኘት እንደምትጠብቁና እንድነግራችሁ እንደምትፈልጉና ሳንጠራጠር በማንም ቃል ሳንወናበድ፣ ሳንሰናከልና ሳንወድቅ ጸንተን እንድንቀመጥ.........የሚል የተማጽኖ ጥያቄ አቅርባችሁልኛል። ምክንያቱም ስለ ንጉሡ በየድህረ ገጹ ብዙ ነገር እየተወራ ስለሆነ እውነታው የቱ እንደሆነ ለማወቅና ለማመን ግራ ተጋባን ብላችሁኛል። አሁን ይህንን መልስ እንድነግራችሁ የፈቀድኩበት ምክንያት ተጨንቃቸሁ ስላስጨነቃችሁኝና ስላሳዘናችሁኝ ነው እንጅ ለመናገር አልፈቅድም ነበር። በተረፈ ስለ ንጉሡ ማንነት አሁን የምነግራችሁ በጣም ባጭሩ ነው። ዝርዝር ሁኔታ አልገባም። ለወደፊቱ በድምፅ ሰፊ የሆነ ምስጢራዊ የትርጉም ትምህርት ስለ ንጉሡና ስለ ጳጳሱ ማንነት ስለምለቅላችሁ በተስፋ ጠብቁኝ አትቸኩሉ። ሳለቅላችሁ ቀድመው ከመጡ ግን መጡ ነው። የማቀርብላችሁ ራሴ በጥያቄና በመልስ ባዘጋጀሁት መሠረት ነው። ይኸውም በደንብ እንዲገባችሁ ብየ በማሰብና በማመን ነው። በሉ ተቀበሉኝ፦ ጥያቄ፦ ንጉሥ ቴዎድሮስ የሚባል አለ የለም? መልስ፦ በደንብ አለ እንጅ። ጥያቄ፦ የት ነው የሚኖረው? መልስ፦ ከጥንት ጀምሮ እንደነ ሄኖክ፣ኤልያስ፣ዕዝራ፣አቡነ አረጋዊ፣ቅዱስ ያሬድ...........በክብር ተሰውሮ የሚኖር ነው እንጅ ጊዜው ደርሶ እስኪገለጥና እስኪመጣ ድረስ ከአሁን በፊት ለማንም ለማን አልታየም አይታይም። ጥያቄ፦ መቼ ነው የሚመጣ? መልስ፦ አይነገርም። ግን ግን በጣም በጣም ቅርብ ጊዜ ነው። ከበራፋችሁ ደርሶ ሊገባ ቆሟልና ደስ ይበላችሁ። ጥያቄ፦ በየት ነው የሚመጣ? መልስ፦ በምሥራቅ። ጥያቄ ፦ በየትኛው የኢትዮጵያ ምሥራቃዊ ክፍል ነው? በበጌምድር ጎንደር ምሥራቅ? በሸዋ ምሥራቅ? በጎጃም ምሥራቅ? በቤተ አምሐራ ( ወሎ) ምሥራቅ? መልስ፦ አሁን አይነገርም፣ ሲመጣ ማየትና መቀበል ብቻ ነው። ጥያቄ፦ ነገዱ ምንድን ነው? መልስ፦ ቤተ አይሁድ እስራኤላዊ እና ኢትዮጵያዊ አማራ ነው። ጥያቄ፦ ትውልድ ሀገሩ የት ነው? መልስ፦ አሁን አይነገርም። የት እንደሆነ ያኔ ሲመጣ ታውቁታላችሁ። ጥያቄ፦ ቴዎድሮስ ማለት ትርጉሙ ምን ማለት ነው? መልስ፦ ቴዎድሮስ ቃሉ የግሪክ ነው እንጅ አማርኛም ግእዝም አይደለም። ትርጉሙም ስጦታ፣ የፈጣሪ ስጦታ ማለት ነው። ጥያቄ፦ ግዛቱ እስከምን ነው? መልስ፦ መላ ኢትዮጵያን፣ መላ አፍሪካን፣በፈጣሪ ፈቃድና ትእዛዝ እንደዛሬዋ አሜሪካ መላ ዓለምን በኃያልነት ይገዛል ይመራል። እንደ ንጉሥ ሰሎሞን ዘመን መላው ዓለም ሁሉ ወዶና ፈቅዶ ይገብርለታል፣ ይሰግድለታል..........ያኔ ግብጽና ሱዳን እንደዛሬው ኢትዮጵያን መረበሽ ይቅርና መተንፈስም አይችሉም። ጥያቄ፦ በሌላ መልኩ ደግሞ የሚመጣው ንጉሥ ንጉሥ ሕዝቅያስ ነው የሚሉ ስላሉ ይህስ እንዴት ነው? ለምትሉኝ፦ መልስ፦ ሌላ ሁለተኛ ሆነ ሦስተኛ ንጉሥ ሕዝቅያስ የሚባል የለም፣ አይመጣምም። ንጉሥ ሕዝቅያስ የሚባለው ራሱ ንጉሥ ቴዎድሮስ ነው እንጅ ሌላ አይደለም። ሰዎች ትምህርትና እውቀት ሳይኖራቸው ዝምብለው ንጉሥ ሕዝቅያስ የሚባል ከቴዎድሮስ ቀድሞ ይመጣል፣ አገሩንና ሕዝቡን ያረጋጋል ምናምን ምናምን እያሉ ይቀባጥራሉ። ይህ ካለመማርና ካለማወቅ፣ እንዲሁም የፈጣሪን ምስጢራዊ የፀጋ ስጦታ ያለማግኘት ነው እንጅ የሚያናግራቸው ሕዝቅያስ የሚባለው ራሱ ቴዎድሮስ ነው። ሕዝቅያስ የተባለበትም ራሱን የቻለ ትምህርታዊ ትርጉምና ምስጢር ስላለው በድምፅ በምለቅበት ጊዜ ስለምተረጉምላችሁ በትእግስት ጠብቁኝ አትቸኩሉ። ጥያቄ፦ ስንት ዓመት ይገዛል? መልስ፦ ከቁጥር አራት የጽሑፍ መልእክቴ ከሆነው መጨረሻ ላይ ብሥራት ከሚለው ላይ አለላችሁ ያንን አንብቡ እላችኋለሁ። በአንጻሩ ደግሞ የሚመጣው ጳጳስ መደበኛ ስሙ ፀሓይ ነው። ግን ግን በትንቢቱ ላይ ኤርምያስ የሚባል ጳጳስ ይመጣል፥ አቡነ አረጋዊ የሚባል ስውሩ ጳጳስ ሆኖ ይመጣል እየተባለም ይነገራል። አዎ ልክ ነው። ግን ግን ኤርምያስ የሚባለውም ሆነ አረጋዊ የሚባለው ራሱ ፀሐይ ነው እንጅ ሌላ ኤርምያስና ሌላ አረጋዊ አይደሉም። ፀሐይን ኤርምያስና አረጋዊ የሚባልበትም ምክንያት ራሱን የቻለ ትምህርታዊ ትርጉምና ምስጢር ስላለው ሁሉንም በድምፅ ስለቅ እተረጉምላችኋለሁና በተስፋና በትእግስት ጠብቁኝ አትቸኩሉ። ከዚህ ውጭ ስውሩ አቡነ አረጋዊ አሁን ጳጳስ ሆነው የሚገለጡና የሚመጡ ሳይሆን በሐሳዊ ዘመን ስውራን ሁሉ ተገልጠው ሲያስተምሩና ሲዋጉ እሳቸውም ያኔ ተገልጠው የሚያስተምሩ፣ የሚዋጉና ሰማዕት የሚሆኑ ናቸው። በጥቅሉ የጳጳሱ ማንነትም ምስጢሩ እንደ ንጉሥ ቴዎድሮስ ነው። ሳልነግራችሁ የማልተወው ሌላ ተጨማሪ ጉዳይ ግን የሚመጡት ጳጳሳት ሁለት ናቸው። አንደኛው በትንቢት የታወቀው አቡነ ፀሐይ ሲሆን ይህ ጳጳስ ዓለምን የሚመራ የዓለም ፓትርያርክ ነው። ፀሐይ የተባለበትም ምስጢርና ትርጉም ስለዚህ ነው ባጭሩ። ዜግነቱ ኢትዮጵያዊ ነው። ትውልድ ሀገሩ ግን አሁን አይነገርም። ያኔ ሲመጣ ታውቁታላችሁ። ሁለመናው እንደ ንጉሡ ነው። ነገዱ ግን በእስራኤል በኩል ነገደ ሌዊ ሲሆን በኢትዮጵያ በኩል ደግሞ ነገደ አምሓራ (አማራ) ነው። ሁለተኛው ጳጳስ ደግሞ ትንቢት ያልተነገረለትና ሱባኤ ያልተቆጠረለት ሲሆን ሆኖም ግን ያኔ የሚሾም ነው። ይኸውም የኢትዮጵያ ፓትርያሪክ የሚሆን ነው። ሥራውም ከዋናው የዓለሙ ፓትርያሪክ ከፀሐይ በታች ሆኖ ኢትዮጵያን ይመራል። ይህኛውም ጳጳስ ነገዱ ኢትዮጵያዊ አማራ ሲሆን ነገደ እስራኤል ይኑርበት አይኑርበት አላውቅም፣ አልተገለጠልኝም። የምነግራችሁ የተማርኩትን፣ የተገለጠልኝንና የማውቀውን ብቻ ነው። ከዚህ ውጭ መናገር የወንጌል ደላላዎች ሰይጣናዊ ስብከት ነው። ትውልድ ሀገሩን ግን አሁን አይነገርም። ሁሉንም ነገር ያኔ ከፈጣሪ መቅሰፍት፣ ከኢትዮጵያ ቅጣት በሥጋ ሕይወት የተረፈ ሁሉ በደስታ ሆኖ ያያል ያውቃል። ከዚህ ከነገርኳችሁ ውጭ ስለ ንጉሡና ስለ ጳጳሱ ማንነት ማንም የወንጌል ደላላና የደንቆሮ ማይም ስብስብ የሆነው ቃዣታም ሁሉ በየቦታው እየተነሳ ያለምንም ትምህርቱ፣ እውቀቱና ፀጋው በየድህረ ገጹ የሚቃዡትን ሰዎች ሁሉ አትስሙ፣ አትመኑ፣ አትቀበሉ ተጠንቀቁ፣ ዘመኑ የራስ ወዳዶች ዘመን ነውና። አይ ካላችሁ ደግሞ ገደል ግቡ። ይህ አሁን በኢትዮጵያና ከኢትዮጵያ ውጭ ያለው የቤተ መንግሥትና የቤተ ክህነት መላው ባለሥልጣናትና የምክር ቤት አባላት፣ የፍርድ ቤት ዳኛው ሁሉ፣ ቅዱስ ሲኖዶስ የሚባለው የወንበዴ ስብስብ ሁሉ፣ ፖለቲከኛ ተቃዋሚ የሚባለው አስመሳይ ሁሉ ያኔ ዋጋውን ያገኛል። ሁሉም እንደ ቆሻሻ ተጠርጎ ወደ እሳት ባሕር ይጣላል ቆሻሻ ነውና። ስለ ጠየቃችሁኝ ስለ ንጉሡና ጳጳሱ ጥያቄአችሁ በቂ መልስ ሰጥቻችኋለሁ ብየ ለአሁኑ አምናለሁ። ሰፊውንና ቀሪውን ምስጢር እንዳልኳችሁ ሌላ ጊዜ በድምፅ ስመጣ። ስለነሱ ጉዳይ ከዚህ ላይ አበቃሁ አበቃሁ። ሌላው ተጨማሪ መልእክቴ ከላይ በውስጥ መስመሬ መልእክት የጻፋችሁልኝ ሁሉ መልእክታችሁ እንደደረሰኝና እንዳመሰገንኳችሁ፣ እንደመለስኩላችሁ ሁሉ በውጭ መስመርም ብዙ ሰዎች የጻፋችሁልኝን መልካም መልእክታችሁን ሁሉ ባየሁት ድህረ ገጽ ያየሁትን አይቻለሁ እናም በጣም አመሰግናለሁ። በተለይ በተለይ ደግሞ "ታማኝ ሰው በለጠ" የተባልከው ታላቅ ምሁር አንተ ምሕረተ አብ ስላልከው እኔ ደግሞ በማውቀው ምስጢር የወንጌሉ ደላላ ስለምለው ሰባኪ ተብየ የጻፍክልኝን እጅግ አስተዋይነት፣ ተመራማሪነት፣ ትእግስተኛነት የተሞላበትን ትምህርታዊ መልእክትህንና ስለ ሕዝበ ክርስቲያኑም ጭምር የችግሩን ጉድለት የነገርከኝ መልእክትህን አይቸዋለሁ። በጣም አመሰግናለሁ። ግን አንድ ጥያቄ ልጠይቅህ። አንተና መሰሎችህ፣ ለምሳሌም ከዚህ በፊት በሶስተኛ መልእክቴ ላይ ግሩም የሆነ ትምህርታዊ መልእክት የጻፈልኝ "ዳኘ አንተነህ" የተባላችሁት ዓለማዊይም መንፈሳዊይም የሆነ ከትህትና እና ከእውነት ጋር የተሞላ ትልቅ እውቀት ይዛችሁ ሳለ ነገር ግን ወደ ሕዝበ ክርስቲያኑ ብቅ አለማለታችሁና ማንም የወንጌል ደላላ ደንቆሮና ዕውር የሆነው ሁሉ እየተነሳ በተስኪያኗንና ምእመኑን በብዙ ጸያፍ ነገር ሲነግዱበት ራሳችሁን ሰውራችሁና ርቃችሁ በዝምታ እያያችሁ መቀመጣችሁ እንዴት ቢያስችላችሁና ሕዝበ ክርስቲያኑም እውነተኞችን እንዲህ ማጣቱና በአስመሳዮች ስብከት ገደል እየገባ መቅሩቱ ምስጢሩ ምን ይሆን? ኃጢአቱስ ምን ቢከፋ ነው? ኧረ እባካችሁ እናንተ ራሳችሁን ሰውራችሁና አርቃችሁ የተቀመጣችሁ ምርጦች ሁሉ ተነሱና ይህን ከንቱና ግብዝ ሕዝበ ክርስቲያን ከወንጌል ደላላዎች አፍና እጅ አድኑት። እኔንም አግዙኝ እባካችሁ። በተረፈ ግን አንባቢያን ሆይ፦ የወንጌሉ ደላላ የሆነው የምሕረተ አብ ተንጠልጣይ ጅራትና ተጎታች ቀሚስ የሆነው አጫፋሪውና እልል ባዩ አጨብጫቢ ጯሂ የሆነው ደናቁርቱና ዕውሩ ክርስቲያን ተብየው ሁሉ ነገ ከሰባኪው ጋር በሥጋ በነፍስ ዋጋውን እስኪቀበል ድረስ ሰሞኑን ስለ ወንጌሉ ደላላ ሰባኪያቸው በለቀቅሁት እውነተኛ መልእክት ምክንያት በየድህረ ገጹ በኮሜንቱ ቱቦና መቃብር አፉን እየከፈተ በሰይጣናዊ ጥላቻ እየተንጫጫና እየተብላላ ስለሆነና ገናም ገናም የበለጠ በእኔ ላይ በጥላቻና በተቃውሞ በኮሜንት ብቻ ሳይሆን በአደባባይም በምጣድ እንደተጣደና በእሳት እንደሚንጫጫ ተልባ ቁሊት ሁሉንም አጫፋሪና ያደረባቸውን ሰይጣን በመድኃኒዓለምና በድንግል ማርያም ኃይል ስለማንጫጫቸውና ስለማቃጥላቸው መንጫጫቱ አይቀርምና ሰምታችሁ እንዳልሰማችሁ፣ አይታችሁ እንዳላያችሁ በዝምታና በንቀት እለፏቸው። ከመንጫጫት አልፈው ገናም ይብላላሉ። የወንጌሉን ደላላ ሰባኪያቸውን ጉድና የራሳቸውን ውድቀት፣ ውርደትና ኃፍረት ነገ ሲያውቁት መደበቂያና ማምለጫ ይፈልጋሉ፣ ግን አያገኙም። " የኢትዮጵያ ሕዝብ short memory ነው" አለ ዓብይ አህመድ። ከዚህ ላይስ እውነቱን ነው። ምንም ሐሰት የለበትም። ይህ ቃሉ የሚሠራው ደግሞ በተለይ በተለይ አሁን በዘመናችን ላለው እንደ ኤሳውና እንደ አስቆሮቱ ይሁዳ ቅድሚያ ከእውነት ይልቅ እንጀራውና ገንዘቡ ለሚበልጥበት ምናምንቴ ለሆነው አስመሳይ አማራና አስመሳይ ክርስቲያን ለሆነው ሁሉ ነው። እኔ ስለነሱ ለነሱ ከአሁኑ አፈርኩ፣ መድኃኒዓለም ከእነዚህ ኅብረት ለዘላለም አርቀኝ አበቃሁ። በመጨረሻም እንደተለመደው ወደ ሀገራችንና ወደ ነጻነታችን ጉዳይ ልግባና ስለ ሁለት ሰዎች ጉዳይና ስለ አዲስ አበባ ጉዳይ ባጭሩ ተናግሬ ልሰናበታችሁ። አርበኛ፣ ታጋይና ፕሮፌሰር ተብየው ብርሃኑ ነጋ ሆይ፦ ትናንት በባሕረ ነጋሽ (በኤርትራ) እና በጎንደር፣ በአርባ ምንጭ..........ምድር ላይ በነጻነት የትግል ስም በኢትዮጵያዊያን ዜጎችና በተለይ በተለይ ደግሞ በአማራ ነገደ ትውልድ ላይ በንጹህ ደማቸውና በሕይወታቸው ሞት ላይ እንደቀለድክ አትቀርም። በመድኃኒዓለምና በድንግል ማርያም ኃይልና ትእዛዝ ዋጋህን ታገኛለህ አይቀርልህም። የትም አታመልጥም። የፈጣሪን ኃይልና ጥበብ አታውቅምና ጠብቅ። ዛሬ ደግሞ ኢትዮጵያ አዲስ አበባ ገብተህ ከዓብይ አመድ ጋር እየተሞዳሞድክ በአማራ ነገድ ላይ የምትሠራውን ሰይጣናዊ የግፍ ሥራና የውሸት ፖለቲካህን ሁሉ በደንብ ነው የምንከታተልህና የምናውቅብህ። ትናንት ጥሩ አድርገን ያከበርንህንና የወደድንህን፥ ያመንንህን ያህል ነገ ግን በደንብ አድርጎ የሚያዋርድህና የሚቀጣህ ኃይል ይመጣብሃልና ጠብቅ። እንዲህ በሀገርና በሕዝብ ላይ ነግደህና ቀልደህ አትቀርም። እናንተየዋ፦ እኔ እኮ የሚገርመኝ ነገር ዓለማዊውም መንፈሳዊውም የሚባለው ሁሉ በየፊናው በሕዝብ ላይ፣ በበተስኪያን ላይ፣ በምእመኑ ላይ፣ በሀገር ላይ ዘራፊ ነጋዴ መሆኑ ነው። ኧረ መድኃኒዓለም ሰውረኝ አደራህን። እንዲያው ከዚህ ጉድና ከጉደኞች እንዳትጨምረኝ። ከብርሃኑ ጉድ ስለጥቅ ደግሞ ወደ ሲሳይ አጌና እገባለሁ። በ፪ሺ፲፫ ዓ ም የካቲት ወር ላይ የኢሳት ጋዜጠኛ የሆነው ሲሳይ አጌና ስለ ወልቃይት ጉዳይ የተናገረው አስደሳችም አሳዛኝም ቃል፦ አስደሳቹና እውነታው ቃል ወልቃይት የጎንደር ግዛት እንጅ የትግሬ እንዳልነበርና እንዳልሆነ ዶክተር አረጋዊ በርሄ በእኛ በኢሳት ተጠይቀው ወልቃይትን የፈለግነው ለሱዳን መሸጋገሪያ ብለን ነው እንጅ የእኛ መሬት ነው ብለን አይደለም ብለዋል። እንደገና የአጼ ዮሐንስ የልጅ ልጅ የሆኑት ራስ መንገሻ ሥዩም ደግሞ በVOA ተጠይቀው ወልቃይት የትግሬ ግዛት ሆኖ አያውቅም ማለታቸውን ከተናገረ በኋላ አስለጥቆ ወልቃይት የጎንደር መሆኑን ራሱም ተናገረና መልሶ እኔ ግን አሁን የምለው ወልቃይት በትግሬም በአማራም ክልል መሆን የለበትም። ነገሩ በትክክል እስኪፈታ ድረስ ወልቃይት ለብቻው ራሱን ችሎ ዞን ተባለ ምን ተባለ ራሱን ችሎ ቢቆይና ለምርጫ ቢመርጥ ሲል ስሰማው ያ እውነተኛና ጀግና ሲሳይ አጌና መሆኑን ማመን አቃተኝ። ከዚህ ላይ ቃሉን የሰማሁት እኔው ራሴ በጀሮየ ሲሆን የጻፍኩት ግን ከተናገረ በኋላ ብዙ ቀናትን ከቆየሁ በኋላ ስለሆነና መዋሸቴ ሳይሆን ልረሳ ስለምችል ድንገት ያልተናገርከውንና የተናገርከውንም አጣምሜና ተናግሬ ከሆነ አስቀድሜ ከባድ ይቅርታ እጠይቃለሁ። ካሳ የሌለው ይቅርታ። ካሳማ እንዳልከፍልህ ደግሞ ምንም የሌለኝ ነጭ ድሃ ነኝ። እንዳልተሳሳትኩ ግን አውቃለሁ፣ በቃልህ ማለቴ ነው። እናማ ትናንት በነጻነት ትግል ላይ ሳለህ ስንወድህ፣ ስናከብርህ፣ ስናምንህ፣ ስንኮራብህ የነበርከው ታላቁና አንጋፋው ጋዜጠኛችን አርበኛው ሰማዕት ሲሳይ አጌና ሆይ፦ አሁን በመድኃኒዓለም ስም የምነግርህ ነገር በማንነት ሁለመናህ ላይ ልክ እንደ ትናንቱ ሁን እንጅ ዛሬ ተቀይረህ ዓብይ አመድ ስለ ወልቃይት ጉዳይ ስለሚነሳው ጭቅጭቅ ምን ማድረግ እንዳለበት ለመጠቆም ብለህ የዓብይ አመድ የማሰቢያ አእምሮ፣ የማገናዘቢያ ልቦና፣ የመናገሪያ አንደበት ለመሆን መሞከርህ ለእኔ ለአምኃ ኢየሱስ ስውርና ድብቅ አይደለም። እናም የሰማንህ ሁሉ እጅግ በጣም አዝነንብሃል። ለመሆኑ ግን እንዲያ ብለህ የምትናገር ስለ ወልቃይት ሕዝብና መሬት ማንነትና ባለቤትነት ወሳኞቹ ወልቃይቶች ብቻ ናቸው ያለህ ማን ነው? ወልቃይትና ወልቃይቶች እኮ የበጌምድር ጎንደር የመላው አማራ መሬትና ሰዎቹም መላው በጌምድሬ ጎንደሬና አማራዎች ናቸው። ወልቃይትንም ወደ ርስቱ የመለሰው መላው የሸዋ አማራ፣ የጎጃም አማራ፣ የቤተ አምሓራ አማራ፣ የበጌምድር አማራ ደሙን አፍስሶ አጥንቱን ከስክሶ ሥጋውን ቆርሶ ሕይወቱን ሰውቶ፣ ከሕጻናት እስከ ሽማግሌ ሕዝብ አልቆበት ነው እኮ። ስለዚህ ወልቃይትና ወልቃይቶች የጎንደርም የትግሬም ሳይሆኑ ለጊዜው ራሱን የቻለ ዞን ሆኖ ቢቆይና ለምርጫ ራሱን ችሎ ቢሳተፍ የሚለውን ክህደታዊ ሀሳብና ቃል እንዴት ልታስበውና ልትናገረው ደፈርክ? ምነው እውነታውን ብቻ አስረግጠህ ወልቃይትና ወልቃይቶች አማራ ናቸው፣ ጎንደሬ ናቸው፣ ከእንግዲህ በኋላ ሌላ ቋንቋ አያስፈልግም ብለህ ብትናገር ከዓብይ አመድ ምን ሊቀርብህና ምን ሊደርስብህ ነው? ተው ትናንት እንዳከበርንህ፣ እንደወደድንህ፣ እንዳመንንህ ሁሉ ዛሬም ነገም ተከበር፣ ተወደድ፣ ታመን። ባይገርምህ ከእንግዲህ በኋላ ወልቃይትና ራያ ወደ ትግሬ ሊሄዱ ይቅርና እንደነሱ የድንቁርና ድፍረትና በማን አለብኝነት፣ በእልህና በብልጠት ከሆነ ተከዜን ተሻግረን አኩሱም ድረስ ያለውን መሬት ጠቅልለን ወደ አማራው ግዛት ማስገባት እንደምንችል እወቅ፣ይወቁ። አኩሱም ማንነቷ ሁሉ የአማራና የቤተ እስራኤሎች ነበረችና። አሁን መናገር የማልፈልገውን ነገር ሳልወድ በግዴ ነው በእልህ ለመናገር የተገደድኩ። እናማ ወንድሜ ሲሳይ አጌና ሆይ፦ የወልቃይትና የራያ ጉዳይ ዶሴው ያላንዳች እሰጥ አገባ ለመጨረሻ ጊዜ እንደተዘጋ እወቅ፣ ይወቁ። አይ ካሉ ደግሞ ይምጡና ይሞክሩን፣ እንደልማዳቸው ዋጋቸውን ያገኛሉ። ገና ገና መተከልን ወደ ጎጃም፣ ደራን ወደ ሸዋ አማራ ሳንመልስ ከእንግዲህ እንቅልፍና ረፍት የለንም። በል ደህና ሁንልን። የመዝጊያ መልእክቴ ወይ አዲስ አበባ!!! ይሆናል። የካቲት ፲፰ ፪ሺ፲፫ ዓ ም ዕለተ ሐሙስ የእግዚአብሔር ቃል በስውራን አማካኝነት ወደኔ እንዲህ ሲል መጣ። "አምኃ ኢየሱስ ስለምንም ነገር አትጠራጠር፥ እመን። ኦሮሞዎቹ አዲስ አበባን ተቆጣጥረናል ይላሉ። ለማጥፋት፣ ለጥፋት። ደግሞም ያጠፏታል ትጠፋለች። ግን ጠፍታ ደሞ ትነሣለች። እስከ ስሟ አዲስ አበባ ተብላ ትጠራለች። እነሱም ይጠፋሉ ይህ የሚሆነው እንክርዳድ ከስንዴ፣ እሾህ ከገብስ እስኪለይ ነው። በተጨማሪም ጠላቶችህ አይለዋል በዝተዋል ያነፈንፋሉ፤ ጋኔሎቹ ተንቀዥቅዠዋል፣ ሁሉም በአደባባይ ወጥተው አፋቸውን ይከፍቱብሃል። ቱቦ አልክ አይደል? አዎ እነሱ ቱቦውን እስከ ሽታው ይከፍቱብሃል፣ ከማፈር ይልቅ ብሶባቸው ደንድነዋል፣ ነውራቸውም በአደባባይ ቢጠቀስም ምንም እንዳልተፈጠረ ደስተኛ ሆነው ያለከልካይ ይግማማሉ። አንተ ግን ደጋግመን እንደነገርንህ ዝም ብለህ መጨረሻቸውን በትእግስት ጠብቅ"። እናማ የአዲስ አበባ ነዋሪ ሁሉ ደጋግሜ እንደነገርኳችሁ እባካችሁን ምንጊዜም ቢሆን አትዘናጉ፣ ራሳችሁን በተጠንቀቅ ጠብቁ። ያበቃና ያለቀ ጊዜ ነውና። በቀደም በድንገተኛ መልእክቴ ተናግሬዋለሁ፣ አሁንም ልድገመውና ንጉሡና ጳጳሱ እስኪመጡ ድረስ በኢትዮጵያ ምድር ላይ ሰላም የለም፣ አይኖርምም። ለማንኛውም በቁጥር ሁለት መልእክቴ ላይ ስለ አዲስ አበባ ጥፋት በግጥም የተናገርኩትን መልእክት ወደኋላ ተመለሱና በደንብ አዳምጡ። እኔ ግን የመድኃኒዓለም የቁጣ ፍርድ በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ በቅርቡ ሊፈጸም በመሆኑ ደስታየ ወሰን የለውም። በእኛ ላይ እያንዳንድህ እንደቀለድክብንና እንደሰደብከን አትቀርምና። ስለዚህ ዋጋህን ስታገኝ ደስ ይለናል። ከድካማችን ሁሉ እናርፋለንና። የረሳሁት ነገር፦ ለአቅመ አዳምና ለአቅመ ሔዋን የደረሳችሁና ከዛ በላይ የሆናችሁ ክርስቲያኖች ሁሉ፣ በተለይ ደግሞ ወዳጆቼ የሆናችሁ ሁሉ ለቁርባን ሳትቸኩሉና ሳታውቁ እሳት ውስጥ እንዳትገቡ ቅድሚያ ኃጢአታችሁን ሁሉ ሳትደብቁ፣ ሳትቀንሱ፣ እያስታወሳችሁ በቃላችሁ በግልጽ ተናዘዙና የቅጣት ንስሐችሁን ተቀብላችሁና ፈጽማችሁ ብትሞቱም ብትተርፉም በተጠንቀቅ ጠብቁ አደራ። ለቁርባን ግን በማንም ደናቁርትና እውራን ከንቱ ስብከት እየተመራችሁ እንዳትገቡ ነገርኩ አደራ። ሁሉም በደረጃ ነው የሚፈጸመው። እናም በወንጌል ደላላዎች ስብከት እየተመራችሁ ከባድ ፈተና ላይ እንዳትገቡና መውጫው እንዳይጠፋባችሁ አደራ። ሥጋየን ያልበላ ደሜንም ያልጠጣ የዘላለም ሕይወት የለውም። የበላና የጠጣ ግን የዘላለም ሕይወት አለው ይላልሳ ጌታ በቃሉ? እንደምትሉኝ ሁሉንም ነገር ጠንቅቄ አውቃለሁ። ትምህርቱን ከኔም ሆነ ከአዋቂ ሊቃውንቶች በትክክል እስክታገኙ ድረስ በንስሐ ኑዛዜ ብቻ ቆዩ፣ ጸንታችሁ ኑሩ። ንስሐው ራሱ ገነት መንግሥተ ሰማያት የሚያስገባ ነውና በምነግራችሁ ቃሌ ሁሉ አትጠራጠሩ፣ ማንም የወንጌል ደላላ ቁረቡ ቁረቡ እያለ በለፈለፈ አትጨነቁ፣ አትረበሹ አይዟችሁ። ምንኩስናና ቁርባን አያስቸኩልም። መቸኮልና መፍጠን ለኑዛዜና ለቅጣት ነው። ቆርበውስ መንኩሰውስ ወደ ሲዖል የሚገባው ስንቱ ነው? መአት እልፍ አእላፍ ነዋ። እስቲ ወደ ሲዖል ሒዱና ስንትና ስንት ዲያቆን፣ ቄስ፣ መነኩሴ፣ ጳጳስ፣ ፓትርያሪክ፣ ምእመን እንደሞላ ለማየት ሞክሩ ከቻላችሁ። ወስጄ ላሳያችሁ እንዴ? ኧረ ይቅርባችሁ። እናማ ተናዞ ሲያበቁ ከኑዛዜና ከቅጣት በኋላ በንጽህና ጸንታችሁ ለመኖር መታገል ነው ያለባችሁ። ከኑዛዜ በኋላ ተመልሳችሁ ብትወድቁ እንኳን እንደገና ተመልሳችሁ በንስሐ ኑዛዜ መነሳት ነውና አይዟችሁ አትጨነቁ። ለቁርባን የሚያደፋፍሯችሁና የሚገፋፏችሁ ሁሉ በቂ የሆነ ትምህርትና የጌታ ጸጋ የሌላቸው ከንቱዎች ናቸውና ተጠንቀቁ። ከዚህ በፊት በመልእክቴ አማካኝነት የቆረባችሁ ካላችሁም አይዟችሁ በርቱ፣ ፈተናውን ሁሉ ታገሉት፣ ታገሱት፣ ለምን ቆረብኩ ብላችሁ አትጸጸቱ አትጨነቁ፣ ጠብቃችሁ ያዙት ቁርባኑን። እኔም ስመጣና ስንገናኝ፣ ስንማማር ትጸናላችሁና አይዟችሁ። ዲያብሎስንና ክፉ ሥራውን ሁሉ ከእግራችሁ በታች ፈጣሪ ይጣልላችሁ። ይህንን የተናገርኩት ግን ለወጣቶችና ለጎልማሳዎች እንጅ ለአሮጊቶችና ለሽማግሌ አዛውንቶች አለመሆኑን በደንብ ይታወቅልኝ። እናንተማ ቁርባን ይቅርና ምንኩስናም ይገባችኋል። የዓለም ደስታ አይበቃችሁም እንዴ???? ኧረ ጉድ ነው። እናንተ ካልጠገባችሁና ካልተዋችሁትማ ወጣቱና ጎልማሳውስ ምን ሊሆን ነው?? አሮጊቶችና አዛውንቶች ሆይ፣ ኧረ ልብ ግዙ በቃችሁ ቀዝቅዙ ብረዱ። ለወጣቶችና ለጎልማሶች ፈተና ጸልዩላቸው። በሉ መልእክቴን ሁሉ ተቀበለውም አልተቀበለውም ለሁሉም የኢትዮጵያ ሕዝበ ክርስቲያን ለክፉውም ለደጉም ሁሉ በትኑልኝ አድርሱልኝ (ሼር አድርጉልኝ)። 

ተጻፈ፦ ከአምኃ ኢየሱስ ገብረ ዮሐንስ። 

የካቲት ፳፭ ፪ሺ፲፫ ዓ ም ተፈጸመ ኩሉ በወንጌል ዘሀሎ። 

አላሁ አክበር !!!!!
Share on Google Plus

ስለ የተለጠፈበት ቀን

    Blogger Comment
    Facebook Comment