የህሊና ቁጥጥር ሙከራ (Mind Control) ሰለባ ኢትዮጵያውያን


✍  ዘርአዳዊት ዘ-ኢትዮጵያ 

ለሲ.አይ.ኤ የህሊና ቁጥጥር ሙከራ (Mind Control Experiment) ከተጋለጡት “አባቶች” (አባትነት አይገባቸውም!) መካከል ፥ ካሁን በኋላ ሸህ አቡ ፋና a.k.a አቡነ ፋኑኤል/ አባ መላኩ የሚባሉት ወገን ይገኙበታል።

የሚናገሩትን አያውቁም፣ የሚያደርጉትንም አያውቁም። “የኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያውያን/አክሱማውያን ብሎም የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ክርስትና እምነታቸው ጠላቶች እንደሆኑ እንኳን የሚገነዘቡት አይመስለኝም” የሚል ጥርጣሬ ነበረኝ፤ አሁን ግን ሁሉም ነገር ግልጥልጥ እያለ ስለመጣ፤ እነዚህ ወገኖች አውቀውም ሆነ ሳያውቁት ዲያብሎስን ለማገልገል ወስነዋል፤ ከአህዛብ፣ ከመናፍቃን፣ ከኢ-አማንያን፣ ከግብረ-ሰዶማውያን ጎን ተሰልፈው ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊነትን እንዲሁም ኦርቶዶክስ ክርስትናን ለመወጋት ፈቃደኞች ሆነዋል። እነ አቡነ ፋኑኤል፣ አቡነ ዮሴፍ ወዘተ ለእኔ አህዛብ እንጂ ክርስቲያኖች በፍጹም አይደሉም።/አራት ነጥብ!
 
እንዲህ እየወጡ ጭንብላቸውን ያውልቁ፤ ተኩላዎቹን ወገን ይያቸው፣ እንደ ሙከራ የጊኒ አሳማዎች እያጠና እና እየታዘበ መዳን የሚፈልግ ሁሉ ይማርበታል።
 
በአንድ ወቅት ለአንዲት ልጅ ስለ አንድ መንገድ ላይ ስለተፈጠረ ክስተት ሳጫውታት፤ “ለመሆኑ ሰውየው ክርስቲያን ነው ወይስ ሙስሊም?” አለችኝ። እኔም “ዓይኖቹ የሙስሊም ዓይኖች ስለሆኑ ሙስሊም መሆን አለበት።” ስላት ፥ መልሳ፤ “ሙስሊሙን በዓይን መለየት ይቻላልን?” ስትለኝ፤ ቆጣ ብዬ፤ “እንዴ የሙስሊምና የክርስቲያን ዓይን መለየት አትችይም እንዴ፤ እኅት ዓለም? ፥ መንፈስ ቅዱስ ባረፈበትና ባላረፈበት ዓይን መካከል እኮ እጅግ በጣም ትልቅ ልዩነት አለ፤ እንኳን በዓይን በሰውየው ድምጽም፣ በአፉም፣ በጥርሱም(የዋቄዮ-አላህ ልጆች ላይ ይታያል፤ ምሳሌ፤ የጥላሁን ገሠሠ የአቴቴ ድምጽና አፉና ጥርሱ ወዘተ፤ ሙስሊሞች እኮ ወደ ሰማይ አንጋጠው እንኳን ማየት አይችሉም፤ መሐመድ ወደታች ወደምድር ዓይናቸውን ከድነው እንዲጸልዩ ነው በሃዲሳቸው ያዘዛቸው ወዘተ... በይ ቶሎ ብለሽ ቡና መጠጣት አቁሚ!” ማለቴን አስታውሳለሁ።

አዎ! ገጽታችን ብዙ ነገር ነው የሚነግረን። ሸህ አቡ ፋናም ይህን ነው የሚያንጸባርቁት። ላለፉት አስራ አምስት ዓመታት ሃሳቤን ሳልቀይር በተደጋጋሚ የማወሳውና በተለይ በባቢሎን አሜሪካ የሚገኙትን ተዋሕዶ ክርስቲያኖችን፣ ኢትዮጵያውያን በምችለው አቅም ሳስጠነቅቅ ቆይቼ ነበር።

አሜሪካዎቹ ከመልከዓ ምድር አቀማመጥ አንጻር ጥንታውያን ሕዝቦች እንዳይሰፍሩበት የተደረገው እኮ ያለምክኒያት አልነበረም፤ አሜሪካዎች እና ሩቅ ምስራቆች አቀማመጥ እኮ እግዚአብሔር የሰውን ልጅ በገነት ካኖረበት (ከኢትዮጵያ እስከ እስራኤል) ክልል እና ምድረን ለሁለት ከሚከፍላት ኬንትሮስ/longitude መስመር በጣም እርቀው ነው የሚገኙት።

ከዚህ በተጨማሪ ሰሜን አሜሪካ በተለይ የዋሽንግተን፣ ቪርጂኒያ፣ ሜሪላንድ አካባቢ በሉሲፈራውያን ነፃ ግንበኞች/Freemasons የተመሰረቱ ግዛቶች የሚገኙበት አካባቢ ነው። በተለይ በ ዋሽንግተን ዲሲ እያንዳንዱ ሕንጻ፣ እያንዳንዱ ጎዳና እና ፓርክ በሉሲፈራውያኑ ባለ አምስት ማዕዘን ኮከብ (Pentagram) ጨረረ ተነድፈው ነው የተገነቡት/የተሠሩት።

በሌላ በኩል፤ አንድ የሚደንቅ ክስተት፤ ልክ በኢትዮጵያ እንደሚታየው(ሲዳማ)፤ በአሜሪካም ከሁለት ሳምንታት በፊት የአሜሪካ ተወካዮች ምክር ቤት ዋና ከተማዋን ዋሺንግተን ዲሲን (ዲስትሪክት ኦፍ ኮሎምቢያ)፶፩/51 ኛ ግዛት ለማድረግ ለማድረግ ቢል አፀደቀ ፣ የሴኔት መሰናክሎች እንደቀጠሉ ቢሆኑም)።

በተለይ በዋሺንግተን እና አካባቢዋ እንዲሁም በሚነሶታ ካሊፎርኒያ አላስካ እና ሌሎች ግዛቶች የሚኖሩ ትውልደ ኢትዮጵያውያን ለሉሲፈራውያን ነፃ ግንበኞች የህሊና ቁጥጥር ሙከራ (Mind Control Experiment) እጅግ በጣም አመቺዎች ሰለሆኑ ብዙዎች ሰለባ እንደሆኑ እያየናቸው ነው። በተለይ ተዋሕዶ ክርስቲያኖች ተጋድሮ ለሚወዱት ነጮች የህሊና ቁጥጥር ፕሮግራሞች በጣም ይፈለጋሉ/ይወደዳሉ። በፈረንጆቹ ሚሌኒየም መግቢያ አካባቢ የጉግል ተቋም አንድ የዓለምን ሃገራትና ሕዝቦቻቸውን ባሕርይ የሚገልጽ የዓለም ካርታ አውጥቶ ነበር። በዚህ ካርታ ለኢትዮጵያ/ ኢትዮጵያውያን የተሰጠው መገለጫ፤ “ተለዋዋጭ ያልሆነ የተረጋጋ ባህሪ” የሚል ነበር። አዎ! ይህ የትክክለኛዎቹና ለህሊና ቁጥጥር ሙከራዎች ያልተጋለጡትን ኢትዮጵያውያንን ይገልጻል።
እስኪ አሁን አሜሪካ ያሉትን፤ በተለይ ዋሺንግተን ዲሲ አካባቢ ያሉትን “አባቶችን”፣ ሜዲያዎችን፣ ዩቲውበሮችን እንመልከት፤ እስኪ እንመልከት ምን ያህል ተለዋዋጭ ባህሪ እንዳላቸው! ዛሬ የሚሉትን ነገ የማይደግሙት፤ አንዴ ከግራኝ አብዮት አህመድ ጋር ይደመራሉ፤ ሌላ ጊዜ ተቃዋሚው ሆነው ሲለፍፉ ይሰማሉ። ዛሬ የአቡነ ማትያስ ደጋፊዎች ሆነው የሚሰሙት መርኽ-አልባዎቹ የኢትዮ360ቹ እነ ኃብታሙ አያሌው፤ ዘወር ብለው እነ ሸህ አቡ ፋና a.k.a አቡነ ፋኑኤል/ አባ መላኩን ሲከላከሏቸው ይታያሉ። ዛሬ የአቡነ ማትያስን ቃለ መጠይቅ ለመደገፍ 
የወሰኑት እነ ዘመድኩን በቀለ፤ ዘወር ብለው አቡነ ማትያስን ካፈኗቸው ከሃዲዎች መካከል ዋንኛው የሆነውን መሰሪውን ጋንኤል ክስረትን ሲሟገቱለት ይሰማሉ። ሉሲፈራውያኑ በዋሺንግተን ሲሲ ሸህ አቡ ፋና a.k.a አቡነ ፋኑኤልን “ውጡ እና ተናገሩ እንጂ” ባሉበት ማግስት በአዲስ አበባ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስን አስተናገደ።
 
እንግዲህ ይህ ሁሉ በጥቂት ሰዓታት እና ቀናት ልዩነት ነው እየተካሄደ ያለው። እንግዲህ ይህ ሁሉ የሚያሳያን እነዚህ ወገኖች ለሲ.አይ.ኤ እና ኤን.ኤስ.ኤ የህሊና ቁጥጥር ፕሮግራሞች የተጋለጡ መሆናቸውን ነው።
 
በስልሳዎቹ ዓመታት ላይ ሲ.አይ.ኤ ኤም.ኬ.ኡልትራ/“MKULTRA” በተሰኘው ፕሮግራሙ በ ለጥቁር አሜሪካውያን አእምሮን የሚቆጣጠሩ መድኃኒቶችን እየሰጠ በጣም እየወፋፈሩ እንዲመጡና አሁን ለደረሱበት እጅግ በጣም አሳዛኝ መንፈሳዊ ሁኔታ እንዲበቁ አድርጓቸዋል። ይህ ፕሮግራም ዛሬ ካሉት ፕሮግራሞች ጋር ሲነጻጸር የያኔው ፕሮግራም የስድስተኛ ክፍል የቤተ ሙክራ እቃ እቃ ነው። ዛሬ የማይታዩ ጨረሮች ከሁሉም አቅጣጫ ስራዎቻቸውን መስራት ይችላሉ።

ለማንኛውም በተለይ በዋሺንግተን ዲሲ ከሚገኙት “አባቶች”፣ ሜዲያዎች እና ዩቲውበሮች እንጠንቀቅ።

                                             ኮሚኒስታዊ የሰይጣን አምልኮ ሰንቅደ ዓላማ
 
ዘረኛ የህወሓት ፖለቲካ ሰለባ የሆናቹ “ትግራዋይ ነን” የምትሉ ወገኖቼ የዋሺንግተን ዲሲ ሉሲፈራውያኑ ነፃ ግንበኞች የሰጧችሁንና ባለ አምስት ማዕዘን ኮከብ ያረፈበትን ባለ “ሁለት ቀለም ብቻ”(ፀረ-ሥላሴ/Antitrinitarian፣ ሁለትዮሽ/Dualistic) ሰንደቅ ዓላማ ከማውለብለብ ተቆጠቡ፤ ይህ በጣም ቁልፍ የሆነ መለኮታዊ ጉዳይ ነው። ሁለት ተቃራኒ ቀለሞች ፣ ሁለትዮሽን ይወክላሉ። Luciferianism /ሉሲፊሪያኒዝም/ ሉሲፈራዊነት/= Dualism/ሁለትዮሽ/ዱአሊዝም።

ይህ አምልኮ ደግሞ ከአዲሱ ዘመን እንቅስቃሴ ፣ ከፍሪሜሶናዊነት/ከነጻ ግንበኝነት ፣ ከተባበሩት መንግስታት እና ከቴክኖክራሲ በስተጀርባ ያለ የ “ልሂቃኑ/ምርጦች/ቁንጮዎች” ድብቅ ሃይማኖት/አምልኮ ነው። ዛሬ ድብቅ እንዳልሆነ እያየነው ነው!


                                     መለኮታዊየ ኪዳነ ኖህ መገለጫ የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ
 
የተሟሉ የቀለም ጥንዶች የሆኑት “ቀይ፣ ቢጫ፣ አረንጓዴ” ግን፤ ቅድስት ሥላሴን እና ተዋሕዶን ይወክላሉ (ትክክለኛው የኢትዮጵያ/አክሱም ሰንደቅ ቀይ ከላይ ፣ በመኻል ቢጫ እና አረንጓዲ ከታች፤ ጽዮን ማርያም መኻል ላይ ያለችበት ነው)

ታህሳስ ፳፻፲፫ ዓመተ ምሕረት



Share on Google Plus

ስለ የተለጠፈበት ቀን

    Blogger Comment
    Facebook Comment