"አማልክቶቻቸው ብዙ ለሆኑ፡ አጋንንቶቻቸውም እንዲሁ ብዙ ናቸው።"


✍️ አሐዱ ዓለም ኢትዮጵያዊ

☞ እነዚህም ሰዎች፡ በእጆቻቸው መስቀልና መቁጠሪያ ይዘው በተሣሉ በቅዱሳን አባቶች ሥዕል ሥር ተንበርክከው የሚሰግዱላቸው፡ ነገር ግን፡ በእጃቸው በያዙት መስቀልና መቁጠሪያ አጋንንትን እየቀጠቀጡ ወደሲዖል የሚሸኙትን አባቶች የሚቃወሙት ናቸው።

☞ እነዚህም ሰዎች፡ ተአምር ሲሠሩ በዓይናቸው ያላዩአቸውን አማልክት የሚወድዱ፡ ነገር ግን፡ ተአምር ሲሠሩ በዓይናቸው የሚያዩዋቸውን አማልክት የሚጠሉ፡ ጣዖት አምላኪዎች ናቸው።

☞ ስለእነዚህም ሰዎች በወንጌል፦ "እናንተ፡ በሥራ ለማታውቁት አምላክ ትሰግዳላችሁ፥ እኛ ግን፡ በሥራ ለምናውቀው አምላክ እንሰግዳለን" ሲል፡ የሕግ መምሕሩ የተናገረላቸው የሩቅ ምስል አምላኪዎች ናቸው።

☞ እነዚህም ሰዎች፡ የራሳቸው ኢየሱስ ክርስቶስ፥ የራሳቸው ድንግል ማርያም፥ የራሳቸው ቅዱሳን መላእክት፥ የራሳቸው ቅዱሳን አባቶች ያላቸው፡ የኦርቶዶክስ ክርስቲያን አማኞች ናቸው።

Share on Google Plus

ስለ የተለጠፈበት ቀን

    Blogger Comment
    Facebook Comment