በፈረንሳይ ፩ መምህር ሲገደል እና በኢትዮጵያ ሺህ ክርስቲያኖች ሲገደሉ!


✍ ዘርአዳዊት ዘ-ኢትዮጵያ 

ምን ዓይነት ልዩነት እያየን ነው? ገዳዩና ጨፍጫፊው መንፈስ አንድ ዓይነት ነው። ግን፦

👉ባለፈው ዓርብ በፈረንሳይ ፓሪክ አንድ መምህር መንገድ ላይ በመሐመዳውያኑ ባሰቃቂ መልክ እንደ ዶሮ አንገቱን ተቆርጦ ተገደለ። ይህ አሳዛኝ ግድያ በመላው ዓለም ከፍተኛ ምላሽ አግኝቷል።

👉የፓሪሱ መምህር ልክ እንደ ተገደለ የፈረንሳዩ ፕሬዚደንት ማክሮን ግድያው ወደተፈጸመበት ቦታ በማምራት መግለጫ ሰጠ፣ የተገደለውን መምህር ቤተሰቦች አጽናና።

👉የፓሪሱ ግድያ በመላው ዓለም መገናኛ ብዙኅን ዘንድ እስከ ዛሬው ዕለት ድረስ የሰበር ዜና አትኩሮትን አገኘ።

+ እስኪ ይህን የፓሪሱን ፩ ግድያ በሃገራችን ላለፉት ሦስት ዓመታት ከተፈጸመው እና በታሪካችን ተወዳዳሪ ከሌለው አስከፊ ሁኔታ ጋር እናነጻጽረው፦

👉በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ተዋሕዶ ክርስቲያኖች ባሰቃቂ መልክ ሲገደሉ፤ መቶ የሚሆኑ ዓብያተ ክርስቲያናት ሲቃጠሉ፣ በሚሊየን የሚቆጠሩ ዜጎች ሲፈናቀሉ የአሸባሪው ቄሮ አገዛዝ መሪ ግራኝ አብዮት አሕመድ እንኳን ቤተሰቦችን፣ ቤተ ክርስቲያንን እና ም ዕመናኗን ለማጽናናት ለአንዴም እንኳን ሃዘኑን ለመግለጽ ዝግኙ አልነበረም/አይደለም። ይህ በየትኛዋም የዓለማችን ሃገር ታይቶና ተሰምቶ አይታወቅም! ግን አሸባሪው ግራኝ አብዮት አሕመድ ዓሊ ምን ያህል በሕዝብ ላይ ንቀት ያለው እርኩስ፣ ጨካኝ እና አላጋኝ የሆነ አውሬ እንደሆነ እያየን ነው?! 

👉እንኳን የዓለም አቀፉ መገናኛ ብዙኅን "የራሳችንም" መገናኛ ብዙኅኖች ስለክርስቲያን ኢትዮጵያ ሰቆቃና ስቃይ መናገርና መዘገብ አይሹም። ትናንትና በኮልፌ(ካራ)"ስልጤ ሰፈር" በመስቀለ ሰላም ቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን ላይ መሐመዳውያኑ እና "ፖሊሶቻቸው" የፈጸሙትን ጽንፈኛ ተግባር አንድም መገናኛ ብዙኅን አለመዘገቡ አንዱ ምሳሌ ነው።

👉በተዋሕዷውያን ላይ ይህ ሁሉ ያላባራ ጭፍጨፋ ሲካሄድ ኢትዮጵያውያን አንዴም እንኳን ለተቃውሞ ሰልፍ በአዲስ አበባ ጎዳናዎች ላይ ሲወጡ አልታዩም። ጨፍጫፊዎቹን በዋነኝነት ያደፋፈራቸው ይህ ነው!


Share on Google Plus

ስለ የተለጠፈበት ቀን

    Blogger Comment
    Facebook Comment