✍️ ዘርአዳዊት ዘ-ኢትዮጵያ
እኅተ ማርያም እንኳን ተፈታሽ ፥ ግን ከወሰድሻቸው አንዳንድ እርምጃዎችሽ ተመለሽ፣ የቤተ ክርስቲያንን ሥርዓትና ቀኖና አክብሪ፤ የቀን መቁጠሪያ ስርዓቶቿንም ተከተይ፣ ንግሥትነቱም”አስፈላጊ አይደለም፤ በተለይ የቤተ ክርስቲያንን የውስጥና የውጭ ጠላቶች በሕብረት ተጠናክረን መዋጋት በሚገባን በዚህ ወቅት ምዕመናኑን የሚከፋፍልና የሚያዳክም ሥራ መስራት፤ የአውሬውን አገዛዝ ማጠናከር ካለሆነ በቀር አስፈላጊም ተገቢም አይደለም።
ለማንኛውም እንኳን ተፈታሽ፤ አሁን፤ የተጠቀሱትን ከማስተካከል ጎን ባፋጣኝ ብታደርጊ ደስ የሚለኝ “የተዋሕዶ ልጆችን ፍለጋ” ብለሽ አንዱን ዘመቻሽን እንደጠራሽው ከደምቢዶሎ መካነ አዕምሮ (ዩኒቨርሲቲ) ታግተው የተሠወሩትን እህቶቻችን ጉዳይ ስራየ ብለሽ በመያዝ አሸባሪውን የዐቢይ አሕመድ ቄሮ አገዛዝ አዋክቢው።
በተረፈ፤ የመድሐኔ ዓለምና ቅድስት ድንግል ማርያም ዘ - ኢትዮጵያ ማህበር አባላት በምታድሩበት አካባቢ ባይተዋር የሆኑ የቴክኖሎጂ ድምጾችን እየተናበባችሁ ተከታትላችሁ መዝግቡ፤ በተለይ በእንቅልፍ ሰዓታችሁ ወቅት።
እውነት ለመናገር፤ ለተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ከእኅተ ማርያም ይልቅ በጣም አደገኛ ሆነው ያገኘኋቸው የሚከተሉት የአሸባሪው መናፍቅ+እስላም ግራኝ ዐቢይ አሕመድ ደጋፊዎችና የሰሜን ኢትዮጵያውያን (ተጋሩ የሚልዋቸው) ጠላቶች ናቸው፦
👉 አቡነ ፋኑኤል፤ የዋሽንግተን ዲሲ እና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ (ዐቢይ አሕመድ ሙሴያችን ነው፦)
👉 ዳንኤል ክብረት (ዐቢይ አሕመድ የኢትዮጵያ ስም ሲጠራ እንባው ዱብ ዱብ ይላል)
👉 ዘመድኩን በቀለ (ዐቢይ አሕመድ በእግዚአብሔር የተቀባ መሪ ነው)
ለእኔ ይህ ግልጽ ነው፤ በአደባባይ ካልታረሙና ይቅርታ ካልጠየቁ ፈጠነም ዘገየም ሥራቸው ለሁሉም የሚታይ ይሆናል። አሁንም ከእነዚህ በብዙዎች ዘንድ ተወዳጆቹ ከሆኑ ወገኖች ተጠንቀቁ እላለሁ፦በዚህ ዓለም የክርስቶስ ሰው ይህን ያህል ተወዳጅ አይሆንምና።
Blogger Comment
Facebook Comment