የአውሬው መንግስት በሚቀጥሉት በዓላት በዶሮ እና ዳቦ በኩል መሥዋዕቱንና ቅዱስ ቍርባኑን ለማስቀረት ይሻል!


✍ ዘርአዳዊት ዘ-ኢትዮጵያ 

የሐበሻ ዶሮ እና እንቋላል ወዲያ! የፈረንጅ" የተባለው ዘራቸው ያልታወቀ ዶሮዎችና እንቁላሎች ወዲህ!

የአውሬው አህዛብ መንግስት ያለምክኒያት አይደለም በድብቅ ተቀምመው የተጋገሩ ዳቦዎችን እና ዘራቸው የማይታወቁትን ዶሮዎችን ለገበያ በማቅረብ ላይ ያለው።


መሥዋዕቱንና ቍርባኑን ለማስቀረት መሞከር ከፍተኛ ወንጀልና የሚያስፈርድ ኃጢአት ነው።

የክርስቶስ ተቃዋሚው መሥዋዕቱንና ቍርባኑን ለማስቀረት ከሚጠቀምባቸው ምስጢራዊ መንገዶች አንዱ፦

ጥሬ / እህል


ዶሮ


እንቁላል /ስጋ

[የሉቃስ ወንጌል ምዕራፍ ፳፪፥፲፱]

"እንጀራንም አንሥቶ አመሰገነ ቆርሶም ሰጣቸውና። ስለ እናንተ የሚሰጠው ሥጋዬ ይህ ነው፤ ይህን ለመታሰቢያዬ አድርጉት አለ።"

[የማርቆስ ወንጌል ምዕራፍ ፪፥፳፭፡፳፮]

"እርሱም። ዳዊት ባስፈለገውና በተራበ ጊዜ፥ እርሱ አብረውት ከነበሩት ጋር ያደረገውን፥ አብያተር ሊቀ ካህናት በነበረ ጊዜ ወደ እግዚአብሔር ቤት እንደ ገባ፥ ከካህናት በቀር መብላት ያልተፈቀደውን የመሥዋዕትን እንጀራ እንደ በላ፥ ከእርሱም ጋር ለነበሩት እንደ ሰጣቸው ከቶ አላነበባችሁምን? አላቸው።"

[ትንቢተ ሚልክያ ምዕራፍ ፩፥ ፲፡፲፩]

"በመሠዊያዬ ላይ እሳትን በከንቱ እንዳታቃጥሉ ከእናንተ ዘንድ ደጅ የሚዘጋ ሰው ምነው በተገኘ! በእናንተ ደስ አይለኝም፥ ቍርባንንም ከእጃችሁ አልቀበልም፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር። ከፀሐይ መውጫ ጀምሮ እስከ መግቢያዋ ድረስ ስሜ በአሕዛብ ዘንድ ታላቅ ይሆናልና፤ በየስፍራውም ለስሜ ዕጣን ያጥናሉ፥ ንጹሕም ቍርባን ያቀርባሉ፤ ስሜ በአሕዛብ ዘንድ ታላቅ ይሆናልና፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።"

[ትንቢተ ዳንኤል ምዕራፍ ፱፥፳፯]

"እርሱም ከብዙ ሰዎች ጋር ጽኑ ቃል ኪዳን ለአንድ ሱባዔ ያደርጋል፤ በሱባዔውም እኵሌታ መሥዋዕቱንና ቍርባኑን ያስቀራል፤ በርኵሰትም ጫፍ ላይ አጥፊው ይመጣል፤ እስከ ተቈረጠውም ፍጻሜ ድረስ መቅሠፍት በአጥፊው ላይ ይፈስሳል።"

አዎን! ዶሮን ሲያታልሏት በመጫኛ ጣሏት!

አቤቱ ጌታዬ የሰይጣንን ሠራዊት ከእኛ አርቅ፣ በወጥመዱም እንዳንገባ ጠብቀን፡ ክንፉንም ሁሉ ከእኛ አስወግድልን፡ በአንተ ታምነናልና።


Share on Google Plus

ስለ የተለጠፈበት ቀን

    Blogger Comment
    Facebook Comment