ኢትዮጵያዊ አሁንም ንቃ!

የHeran Tamirat ምስል


የቀድሞዋ የእስራኤል ጠቅላይ ሚንስትር ጎልዳ ማይር የሚከተለውን ተናግረው ነበር፦

ልጆቻችንን በመግደላቸው አረቦችን ይቅር ማለት እንችላለን ፡፡ ልጆቻቸውን እንድንገድል ስለሚያስገድዱን እነሱን ይቅር ማለት አንችልም፡፡ ከዓረቦች ጋር ሰላምን የምናመጣው እኛን ከሚጠሉን ይልቅ ልጆቻቸውን አብልጠው ሲወዱ ብቻ ነው ፡፡

“We can forgive the Arabs for killing our children. We cannot forgive them for forcing us to kill their children. We will only have peace with the Arabs when they love their children more than they hate us”

ኢትዮጵያ አሁን ለምትገኝበት አሳዛኝ ሁኔታ ተጠያቂዎቹ በቅድሚያ ሰሜን ኢትዮጵያውያን ናቸው። በተለይ የትግራይ እና የዐምሓራ ልሂቃን የተባሉት ይህችን የእግዚአብሔር ሃገር ለጠላቶቿ በሰፊ ሰፌድ በማስረከብ ላይ በመሆናቸው ትውልድ ይወቅሳቸዋል፤ በእግዚአብሔር ፊትም ይጠየቃሉ።

በተለይ "የዐምሓራ አክቲቪስት ነን" የሚሉት በይበልጥ አሳፋሪዎች ናቸው፤ በዋቄዮ-አላህ መንፈስ ሥር የወደቁ ይመስላሉ፤ ሁሌ ከማይሆን ጠላት ጋር አብሮ መሰለፍ፣ ከራሳቸውን ቤተሰብ ይልቅ የማያውቁትን ቡዳ ሲያቀርቡ፣ ሲደግፉ፣ ሲያደንቁና ሲያሞካሹ መታየታቸው የተለመደ ነገር ሆኗል።

እስኪ ከሰሞኑ እንኩን የአቶ ልደቱ አያሌውን እና የእህተ ማርያምን ጉዳይ አስመልክቶ "ዐምሓራ ነን" የሚሉ ግለሰቦችና መገናኛ ብዙሃን ያለማቋረጥ የሚያካሂዱትን የስድብና የጥላቻ ዘመቻ ተከታተሉት፤ በጣም አሳዛኝና አሳፋሪ ነገር እያየንና እየሰማን ነው። ልጆቻቸውን ለሚገድሉት በእነ ግራኝ ዐቢይ አሕመድ፣ ለማ መገርሳና ጃዋር መሐመድ ላይ ያላሳዩትን ያህል ቁጣና ወኔ ነው በአቶ ልደቱና እኅተ ማርያም ላይ በማሳየት ላይ የሚገኙት።

በእኔ በኩል፤ ዘውገኛ የሆኑትን "ዐምሓራ ሜዲያ"፣ "ትግሬ ሜዲያ" ቅብርጥሴ የተባሉትን መገናኛ ብዙሃን ገብቼ ማየት መንፈሴን ያውከዋል፤ ግን ሰሞኑን እስኪ ልታዘብ፣ ነገሮችን ሞኒተር ላድርጋቸው በሚል ወኔ ስገባ በተለይ "ዐምሓራ" የተባሉ መገናኛ ብዙሃን ለእኅተ ማርያምን ጉዳይ በጣም ሰፊ ሽፋን ሰጥተውት ይታያሉ፤ ያውም በሚያሳዝንና በሚቀፍ መልክ። "ትግሬ" የተባሉት መገናኛ ብዙሃን ግን አንድም ነገር ስለ እኅተ ማርያም ሲዘግብ አላየሁም፤ ያውም እኅተ ማርያም በትግሬ ኢትዮጵያውያን ላይ ነበር ጠንከር ያለ፤ ጽላተ-ሙሴን ከአክሱም ለመንጠቅ እስከ መሻት ድረስ የደረስ ነቀፋና ትችት ስትሰጥ የነበረው።

ምን እየተካሄድ እንደሆነ እያየን ነው? ታዲያ “ዐምሓራ" ነኝ የሚለው ኢትዮጵያዊ ምን ዓይነት የሞራልና የመንፈሳዊ ውድቀት ውስጥ እንደገባ እያየን አይደልምን? ለዚህ ምክኒያቱስ ምንድን ነው?

ወገን፤ ለሃገራችን ኢትዮጵያና ልጆቿ፣ ለቤተ ክርስቲያናችን እንደነ ግራኝ ዐቢይ አሕመድ፣ ብርሃኑ ነጋ፣ ሽመልስ አብዲሳ፣ ለማ መገርሳና ታከለ ኡማ ክምንዜውም የከፋ ጭካኔ፣ ውድቀትና ውርደት ያመጣ መንጋ የለም። የታመቀውን ቁጭትህን በእነ ልደቱ አያሌው እና እኅተ ማርያም ላይ ማውጣቱ ግብዝነትና ጨቅላነት ነው። እነ ግራኝ ዐቢይ አሕመድ ናቸው እናቶችህን ከየቤታቸው የሚያፈናቅሉት፣ ወጣት ሴት ተማሪዎችህን የሚያግቱት፣ ጡታቸውን የሚቆርጡትና የሚገድሉት። ሕፃናቶችህ እኮ ኦሮሚያ በተሰኘው ሲዖል እየተበከሉብህ፣ እየተመረዙብህና እየታረዱብህ ነው፣ መንፈሳዊ አባቶችህም እንደ እብድ ውሻ ታድነው እየተደፉብህ ነው። ሰሞኑን እንኳን መምህር ምህረተአብ የትውልድ ከተማ በመቱ የሽመልስ አብዲሳ አውሬ ፖሊሶች የተዋሕዶ ልጆችህን ማህተብ በምላጭ እየበጠሱባቸው ነው፣ ሃይማኖታቸውን እንዲቀይሩ እያስገደዷቸው ነው። መሐንዲሶችህ፣ ሐኪሞችህ፣ የጦር መሪዎችህ ዓይንህ እያየ እየተረሸኑ ነው ፥ ልጆችህ፣ ሴቶችህ፣ አየርህ፣ ውሃህ፣ ወንዞችህ፣ አፈርህ፣ እህልህ፣ ጤፍህ፣ ዘይትህ፣ ዶሮዎችህ፣ በጎችህ ፍራፍሬህ፣ አየር መንገድህ፣ ባንክህ፣ ቴሌህ ፥ ባጠቃላይ ሃገርህ ለባዕዳውያኑ የታሪክ ጠላቶችህ እየተሸጡብህ ነው፤ አይኖችህ እያዩ ጆሮዎችህ እየሰሙ።

የምድር ሲዖል ባደረጓትና በተሰረቀችው ክልላቸው በተዋሕዶ ልጆች ላይ የሚካሄደውን ጭፍጨፋና የታገቱትን ሴት ተማሪዎች ጉዳይ አስመልክቶ ግን ቁጣህንና ወኔህን ከማሳየት ተቆጥብሃል፣ ለተቃውሞ ሰልፍ መውጣት እንኳን ፈርተሃል።

Share on Google Plus

ስለ የተለጠፈበት ቀን

    Blogger Comment
    Facebook Comment