ኮሮና ጋኔን ናት ፥ ዘረኝነት ደግሞ የጋኔን አንዱ መገለጫ ነው፦

People wait for a distribution of masks and food in the Harlem neighborhood of New York City.

ቢጫ ጥቁርን ይጠላል ነጭን ይወዳል
ነጭ ቢጫን እና ጥቁርን ይጠላል
ጥቁር ነጭን + ቢጫን ይወዳል


ሰሞኑን በጀርመን አገር ያሉ ምግብ ቤቶች የመንግስት የኮሮና ቫይረስ ክልከላዎችን አብቅተው እፎይ በማለት እንደገና እንዲከፈቱ ሲፈቀድላቸው፤ የአንድ ታዋቂ ምግብ ቤት ፈረንሳዊ ኮከብ ምግብ አዘጋጅ፡ “ቻይናዎችን እዚህ አንፈልግም!” በማለት ቢጫ ሰዎችን ወደ ሬስቶራንቱ እንዳይገቡ በመከልከሉና ብዙዎችን በማስቆጣቱ ከማዕረጉ ላይ አንድ ኮከብ ቀነሰ።

ቀደም ሲል በቻይና ብዙ ጥቁሮች የዘረኝነት አድሎና ጥቃት እየደረሰባቸው ነበር። በአን ወቅት አንዲት ቻይና የቆየች ኢትዮጵያዊት ዲፕሎማት ወደ ገበያ ማዕከል መግባት ስትከለከል አብራት የነበረችዋ ነጯ ሴት ግን መግባት ተፈቅዶላት እንደነበር አይተናል። ብዙም ሳይቆይ በዘመነ ኦሪት እግዚአብሔር አምላክ በኢትዮጵያዊቷ ሲፖራ ምክኒያት የነብዩ ሙሴንና አሮንን እህት ማርያምን በዘረኝነቷ ገስጾ ለምጻም እንዳደረጋት በዘመነ ኮሮናም ቻይናውያን ኢትዮጵያዊቷን ዲፕሎማት በማግለላቸው ይመስላል ሁለት ቻይናውያን ዶክተሮቻቸው ከእንቅልፋቸው ሲነቁ ጠቁረው ተገኙ ፤ ኮሮና ሁሉንም ፩ ገጽታ ሰጠቻቸው ማለት ነው።

ኮሮና ሁሉንም ፩ አደረገቻቸው| ዘረኞቹ ቢጫ ቻይናውያን ጥቁሮች ሆነው ከእንቅልፋቸው ነቁ።

በኮሮና ተጠቅተው የነበሩት ሁለት የቻይና ዶክተሮች ከማገገሚያ አልጋቸው ሲነቁ ቢጫው ቆዳቸው ሙሉ በሙሉ ጠቁሮባቸው ተገኘ።

እንግዲህ የእነዚህ ሁለት ዶክተሮች መጥቆር ሰሞኑን ቻይናውያን በጥቁር ሰዎች ላይ እያራገፉት ያለውን የዘረኝነትን ጋኔን “ዋ! ዋ!ዊ! ዋ!” እያሉ እራሳቸውን በመስተዋት እንዲያዩት ረድቷቸው ይሆናል።

በጣም የሚገርም ዘመን እኮ ነው፡ ጃል! ግን የዘረኝነትን ውጤቶች እያየን ነው? ነጮቹ ቻይናን በኮሮና ቫይረስ ከበከሏት በኋላ ሌት ተቀን ይኮንኗታል ፥ ቻይና ግን በሚሊየን ለሚቆጠሩ ቻይናውያን የአገሮቻቸውን በሮች ብርግድ አድርገው በከፈቱላት ጥቁር አፍሪቃውያን ላይ የዘረኝነትን መርዝ ትተፋለች። ለነገሩማ የምዕራብ እና ምስራቅ ኢ-አማንያን ሁሉም አብረው በአንድነት እየሠሩ ነው። ሁሉም ጥቁር አፍሪቃውያንን ከአህጉራቸው አስወግደው በአፍሪቃ ወይ ነጭንና ቢጫን ብቻ ለማስፈር ይሠራሉ ወይም ደግሞ አፍሪቃ የዱር አራዊቶችና ማዕድኖች መኖሪያ ብቻ እንድትሆን ይሻሉ። የተገለባበጠባት እርኩስ ዓለም።

እግዚአብሐር አምላክ ከሦስት ሺህ ሦስት መቶ ዓመታት በፊት ያስተማረን ይህን ነበር፤ የሰው ልጅ ግን ተምሮ ለመለወጥ ሰንፏል።
Share on Google Plus

ስለ የተለጠፈበት ቀን

    Blogger Comment
    Facebook Comment