በኢትዮጵያውያን ላይ የታቀደው ሴራ


ዘርአዳዊት ዘ-ኢትዮጵያ

"ዓለም ዛሬ 6.8 ቢሊዮን ሰዎች አሏት፡፡ ያ ወደ ዘጠኝ ቢሊዮን ያህል እየመራ ነው ፡፡ አሁን በአዳዲስ ክትባቶች ፣ የጤና እንክብካቤ እና የመራቢያ ጤና አገልግሎቶች ላይ ትልቅ ስራ የምንሰራ ከሆነ ምናልባት ምናልባት ቁጥሩን በ10 ወይም በ 15 በመቶ ዝቅ ማድረግ እንችላለን፡፡"-ቢል ጌትስ

"The world today has 6.8 billion people. That's heading up to about nine billion. Now if we do a really great job on new vaccines, health care & reproductive health services, we could LOWER that by perhaps 10 or 15 percent." -Bill Gates

ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሓኖምን ገና ሲመረጧቸው፤ "ያለ ምክኒያት አለመረጧቸውም!" ብየ ነበር። ኢትዮጵያን ለዚህ ዘመን በደንብ አዘጋጅተዋታል። አውሬው ሕዝቦቿን በነገድ ከከፋፈለ በኋላ በአውሬው መታወቂያና ፓስፖርት ላይ የነገድ ስም ብሎም የየትኛው እምነት ተከታይ እንደሆነ ቁልጭ ብሎ እንዲቀመጥ አድርጓል። ይህ ደግሞ በቀበሌ ሥርዓት የተዋቀሩትን የኢትዮጵያ ከተሞችና መንደሮች ዲያብሎሳዊ ሥራቸውን ለመስራት ትልቅ እድል ሰጥቷቸዋል። ለእነ ግራኝ ዐቢይ አሕመድና  ታከለ ኡማ የየትኛውን ነገድ/ብሔር ነዋሪዎች መከተብ፣ መመረዝና መግደል እንደሚችሉ በጣም አመቺ የሆነ ሁኔታ ፈጥሮላቸዋል።

የተማረው ያልተማረው ወገን ገዳዮቹን "መሪዎቹን" በማወደስ እድሜውን ሲገፋና በማይረቡ ነገሮች እርስበርስ እየተነታረክ ጊዜውን በከንቱ ሲያጠፋ፤ ገዳዮቹ "ልሂቃን" ግን እርሱንና ዘሩን ለማጥፋት ሌት ተቀን ተግተው በመስራት ላይ ናቸው። የአውሬ ምሣ የሆነው ሰጎን በድንጋጤ አንገቱን አሸዋ ውስጥ ይቀብራል፤ የዘመኑ ትውልድ ግን በግድየለሽነት አንገቱን አሸዋ ውስጥ ለመቅበር የሚፈልግ ይመስላል።

"ወደ አገራችን በረቀቀ መልክና በድብቅ የገባው ይህ የፀረ–ህይወት እንቅስቃሴ ከ1970ዎቹ ዓመታት ጀምሮ በትጋት እየሠራ እንደሆነ ባለሙያዎች ይናገራሉ። ከኢትዮጵያ ሌላ፡ ይህ የቤተሰብ አጥፊ ፕላን በጥቁር አፍሪቃውያን ላይ ብቻ ነው እየተካሄደ ያለው። ከሦስት ወራት በፊት ለንደን ከተማ ውስጥ ይህን አስመልክቶ እነ ቢል ጌትስ አዘጋጅተውት በነበረው ስብሰባ ላይ ተገኝተው የነበሩት ከሳሃራ በረሃ በታች የሚገኙት አፍሪቃ አገሮች ሲሆኑ፤ የሰሜን አፍሪቃና ዓረብ አገሮች ጭራሹን አልተሳተፉም።85 ሚሊየን ሕዝብ የሚኖሩባት በረሃማዋ ግብጽ የሕዝብ ቁጥርሽን ቀንሽ የሚል ሃሳብ ቀርቦላት አይታወቅም፡ እንዲያውም ምዕራባውያኑ የእርዳታ ገንዘቡን ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ በደስታ ይሰጧታል፤ የኢትዮጵያንም ውሃና አፈር በነፃ ታገኛለች፡ ጦረኛ የሆኑ ልጆችን መፈልፈሏንም ያለምንም ተቃውሞ ትቀጥልበታለች። ከ 1ቢሊየን በላይ የሕዝብ ቁጥር ያላት ህንድ እንደ ዶፖ ፕሮቬራ የመሳሰሉትን የወሊድ መከላከያ መርፌዎች ከልክላለች (እ.አ.አ በ 2002 ዓ.ም)

አዎ! የዲያብሎስ ሠራዊት ኢትዮጵያውያንን በረሃብ፣ በበሽታና በእርስ በርስ ጦርነቶች እንዳሰበው/እንዳቀደው ለማጥፋት አልተቻለውም፤ ታዲያ አውሬው አሁን ውስጥ ሠርጎ በመግባት መርፌንና፤ ("መድኃኒት" አልለውም)መርዛማ'ቅመሞችን'በነፃ በማደል መጠራጠር የተሳነውን ወገናችንን ወደ ወጥመዱ ለማስገባት እየሞከረ ነው።

ወገን፤ እህቶቻችን፣ እናቶቻችን፣ ጓደኞቻችንና ሚስቶቻችን እንደ ዓይጥ ተቆጥረው የህክምና ሙከራ ሲደረግባቸው እያየን እንዴት ዝም እንላለን? ይህን ይህን መሰሉን አስከፊ ሥራ ለማጋለጥ ካልተነሳሳን ከእንስሳ በምን ነው የምንሻለው?

የሚከተሉትን መረጃዎች ለሚመለከታቸው ወገኖች ሁሉ በሚያስቆጣ መልክ የማስተላለፉ ተግባር የያንዳንዳችን ብሔራዊና ሰብዓዊ ግዴታ መሆን ይኖርበታል።

ለምሳሌ፤ በውጭ ኃይሎች 'ግፊት'ኢትዮጵያ ውስጥ ከተቋቋሙት ድርጅቶች መካከል "DKT Ethiopia (DKT/E)" የተባለውን የፀረ–ህይወት ዘመቻ አራማጅ ድርጅት ብንመለከት፤ ሥራውና ዓላማው ምን እንደሆነ በደንብ ለመረዳት እንችላለን። ድርጅቱ የሚናገረው ሌላ..." 
Share on Google Plus

ስለ የተለጠፈበት ቀን

    Blogger Comment
    Facebook Comment