ዘርአዳዊት ዘ-ኢትዮጵያ
ከ ፹፫ /83 ዓመታት በፊት በዝነኛው የደብረ ሊባኖስ ገዳም ቀደም ሲል ግራኝ አሕመድ ፈጽሞት የነበረው ዓይነት ጭፍጨፋ ሮማውያኑ ጣልያኖችም አውሬነት በተሞላበት አረመኔነት በመንፈሳውያን ኢትዮጵያውያን ላይ አካሄዱ።
ይህ በሃገራችንና በመላው ዓለም በአግባቡ የማይታወቅና ብዙ ጊዜ የማይነገርለት ክስተት ነው። ይኼ የሮማውያኑ የጣልያን ፋሽዝም ከፈጸማቸው ጆሮ ጭው የሚያደርጉ የጭካኔ ሥራዎች አንዱ ነው።
ፋሺስቶች የአቡነ ተክለ ሃይማኖት ፍልሰተ ዐጽም የተከናወነበትን በዓል ለማክበር የተሰበሰቡትን ምዕመናንንና መነኮሳትን ነበር በጭካኔ የጨፈጨፉት፡፡ በጫጋል፣ በውሻ ገደል፣ በሥጋ ወደሙ ሸለቆና በደብረ ብርሃን አጠገብ በእንግጫ በተከናወነው ጭፍጨፋ ገና ነፍስ ያላወቁ ሕጻናት የቆሎ ተማሪዎችን ጨምሮ ከ1801 እስከ 2201የሚደርሱ ምእመናንና መነኮሳት በግፍ ተረሽነዋል፡፡ አውሬ እንዲበላቸውም የትም ተወርውረው ነበር፡፡
በዚህም አላበቃም፡፡ በገዳሙ የነበሩ መጻሕፍት፣ የከበሩ ዕቃዎች፣ ንዋያተ ቅድሳት፣ ገንዘብና ሌሎች ንረቶች ተዘረፉ፡፡ ገዳሙም ነጻነት እስኪመለስ ድረስ በመከራ ውስጥ ኖረ፡፡
አስገራሚው ነገር ከ500 ዓመታት በፊት ግራኝ አሕመድ ገዳሙን ሲያቃጥል የሞቱት መነኮሳት ቁጥር 450 ነበር፡፡ ፋሽስት ኢጣልያ የጨፈጨፈቺው ከእርሱ አምስት ጊዜ እጥፍ የሚበልጥ መሆኑን ስናስበው የጭካኔውን መጠን ያመለክተናል፡፡
ሕጻናት፣ ወጣቶች፣ ጎልማሶችና አረጋውያን በሃይማኖታቸውና በኢትዮጵያዊነታቸው ምክንያት ብቻ የደረሰባቸውን ግፍ ስናስበው ልባችን በኀዘን ፍላጻ ይወጋል፡፡ በተለይ ዛሬም "ኦሮሞ ነን" የሚሉት የፋሺስት ኢጣልያ የግብር ልጆችም በዚህ ታሪካዊ ገዳም ላይ ተመሳሳይ ጥቃት ለመፈጸም ያዙን ልቀቁን እያሉ ሲፎክሩ ስንሰማ ሁሉም ዲያብሎስ ከተከለው ዛፍ የተገኙ ኢትዮጵያንና እግዚአብሔር አምላኳን የሚጠሉ ሥጋዊ ፍጥረታት መሆናቸውን እንረዳለን።
Blogger Comment
Facebook Comment