የመስቀሉ ጠላቶች

ዘርአዳዊት ዘ-ኢትዮጵያ

[የዮሐንስ ወንጌል ምዕራፍ ፲፥፲]

"ሌባው ሊሰርቅና ሊያርድ ሊያጠፋም እንጂ ስለ ሌላ አይመጣም ፤..."

የመስቀሉ ጠላቶች፣ የተዋሕዶ፣ የመስቀሉ፣ የኢትዮጵያና የይሑዳ አንበሣ ጠላቶች ፍላጎት፣ ዓላማና ተግባር ምን እንደሆነ ለሁሉም ግልጽ ነው። ስለዚህ  አሕዛብ ክርስቲያኖችን ቢያፈናቅሉ፣ ቢያርዱ፣ ዓብያተ ክርስቲያናትን፣ መስቀል አደባባይንና ጥምቀተ ባሕራቱን ቢነጥቁንና ቢያፈርሷቸው እንዲሁም ታሪክን ለመስረቅ ቢሠሩ ሊገርመን አይገባም። ሊገርመን የሚገባው አደንቋሪው የሕዝበ ክርስቲያኑና የአባቶች ዝምታ ነው። ቤተ ክህትነት የት አለች?ሰባኪያን፣ ዘማርያን የት ደረሱ? በእነ ኢሬቻ በላይ ላይ ለመፍረድ ያመነታው ግን አንድ ስህተት ያልሠራችውን እኅተ ማርያምን ለመክሰስ የቸኮለው የአዲስ አበባ ሃገረ ስብከት ምነው ዝም አለ? እህተ ማርያምን ያለማቋረጥ ከጠዋት እስከ ማታ ሲወነጅሉ፣ ሲሳደቡና ሲኮንኑ የሚውሉት "መገናኛ ብዙኅን" ለምንድን ነው ለተሠወሩት ተዋሕዶ ሴት ተማሪዎች፣ በትንሣኤ ዕለት ተመርዘው ለተገደሉት የናዝሬት ተዋሕዶ ህፃናት፣ እንዲሁም ቤቶቻቸው ለሚፈርሱባቸውና ለሚፈናቀሉት እናቶች ጠበቃ ለመቆም ይህን ያህል ተግተው የማይታዩት? ከየትኛው ወገን ቢሆኑ ነው? የትኛውንስ መንፍስ እያገለገሉ ይሆን?


Share on Google Plus

ስለ የተለጠፈበት ቀን

    Blogger Comment
    Facebook Comment