ዘርአዳዊት ዘ-ኢትዮጵያ
የግራኝ ዐቢይ አሕመድ ፖሊስ፣ አስቸኳይ ዐዋጁን በማስፈጸም ሰበብ እናቶችንና አረጋውያንን በመገፍተር እና በመደብደብ፣ የተመደቡ ልዑካን እንዳይገቡ በመከልከል፣ አልፎም የቤተ ክርስቲያኒቱን ሥርዐተ አምልኮ በማጥላላትና በኢትዮጵያ ተዋሕዶ ቤተክርስትያን ላይ ጥላቻው እየገለጠ ነው።
ስለዚህ የቤተ ክርስቲያን ተቀዳሚ ዓላማና ተግባር ሊሆን የሚገባው ይህን የአሕዛብ ስጋዊ መንፈስ በግልጽ መዋጋት ብቸኛ አማራጭ ነው። ተለሳላሽነት ወይም ለብ ለብነት ብልህነት አይደልም። "የግራኝ አሕመድ መንግስት ኢትዮጵያን በስጋ ህግ የሚገዛ የአሕዛብ መንግስት ነው፣ የመንፈሳዊ ኢትዮጵያ ቀንደኛ ጠላት ነው፤ ምድሪቱን ለሞትና ባርነት እንዲሁም ለጠላት አሳልፎ በመስጠት ላይ ያለ ጠላት ነው።" የሚለው መርሆ የእያንዳንዱ ተዋሕዶ ልጅ መርሆ መሆን አለበት። በሀገር እግዚአብሔር አሕዛብ ባለሥልጣን መሆን የለባቸውም! እውነቱን እውነት ፥ ሀሰትን ሀሰት ፥ ብርኃንን ብርኃን ፥ ጨለማን ጨለማ ፥ ጥቁሩን ጥቁር ፥ ነጩን ነጭ ማለት የክርስቲያኖች ግዴታ ነው፤ ሌላ "ቆዮ" እየተባለ ጊዜን በስፍና ለመግዛት ወለም ዘለም ማለት አያስፈልግም።
አውሬው የአሕዛብ መንግስት እና አጋሮቹ ፀረ-ተዋሕዶ የሆነውን ዘመቻቸውን ቀስ በቀስ፣ አንድ በአንድና በቅደም ተከተል ነው እያካሄዱ ያሉት። ዓላማቸውን በተግባር ሲፈጽሙ በግልጽ አሳይተውናል። ማታ ላይ ቤተ ክርስቲያን ገብተው ይገድላሉ (አዲስ አበባ 22 + ናዝሬት)ቀን ቀን ደግሞ "ሰይጣን ከቤተ ክርስቲያን አይረቅም" የሚለውን አባባል በማስመስከርና ዓብያተ ክርስቲያናትን በመክበብ ተዋሕዷውያንን ይተናኮላሉ፣ ይሳደባሉ፣ ያንቋሽሻሉ። ጥፋቱ የቤተ ክህነት፣ የመምህራን እና የምዕመናን ነው። ሁሉም ተለሳልሰው ቀጥተኛና ተባዕታይ የነበረችውን ቤተ ክርስቲያን አነስታይ አድርገዋታልና።
Blogger Comment
Facebook Comment