ዘርአዳዊት ዘ-ኢትዮጵያ
ኢትዮጵያ ላለፉት 50 ዓመታት ከገባችበት የባርነት ጉድጓድ ትወጣ ዘንድ ጠላቶቿ ከሆኑት ከአሕዛብ የዋቄዮ-አላህ ልጆች መጽዳት አለባት። ላለፉት 50 ዓመታት የምናያት ኢትዮጵያ በቁማቸው በሞቱ የስጋ ሰዎች ምናባዊ ምስል የተቀረጸችና የተፈጠረችና ዲያብሎስ የነገሰባት ኢትዮጵያ ነች። የዲያብሎስ መንግስታዊ ህግ የ "መቀላቀል" ህግ ሲሆን የእግዚአብሔር መንግስታዊ ህግ ደግሞ የ "መለየት" ህግ ነው። ይህ የተቀላቀለ ወይም የተዳቀለ ስጋዊ የሞትና ባርነት ማንነት ነው ላለፉት 50ዓመታት ኢትዮጵያን ያንኮታኮታት።
ኢትዮጵያውያን እግዚአብሔርን የህይወትና የነጻነት ኪዳን ሽረውና አፍርሰው ከአሕዛብ ማለትም ከዲያብሎስ ጋር ህብረትንና አንድነትን በመፈጸም ለሞትና ለባርነት ራሳቸውን ሲያቀርቡ ይታያሉ። የራሱ ባልሆነ በሌላ ስምና ክብር ተጠራ። የራሱ ያልሆነን ስምና ክብር የራሱ አደረገ። የራሱን ከሁሉ የሚበልጥና የሚልቅ ስምና ክብር ማወቅና መግለጥ ተስኖት ለትንሹ፣ ለርካሹና ለተናቀው እንዲሁም ለተጠላው የስጋ ዕውቀት ጥበብ ኃይል ራሱን ባሪያ አደረገ። ከዛን ጊዜ ጀመሮ ያ ነጻነትና ህይወት የነበረው ህዝብ ለአሕዛብ የስጋ ማንነትና ምንነት ባሪያ ሆነ። ሞቱንና ባርነቱንም የተቀበለው ደግሞ በአህዛብ የስጋ ዕውቀት ጥበብና ኃይል በኩል ነበር።
የደፈረሰውን በተገኘው ጥሩ አጋጣሚ እንደማጥራት ዛሬም "አንድነታችን፣ አብሮነታችን፣ መቻቻላችን...ሙሴያችን" ቅብጥርሴ እያለ መጓዙን የመረጠው እውር፣ ምኞተኛና ሞኝ ሁሉ ደም የሚያለቅስበት ጊዜ እየተቃረበ ነው።
በእስራኤል ዘመን ነቢዩ ሳሙኤል በሚያገለግልበት ጊዜ የእስራኤል ልጆች ነቢዩን ንጉሥ እንዲያ ነግስላቸው ይጠይቃሉ። ነቢዩ ግን በእስራኤል ጥያቄ ደንግጦ እግዚአብሔር ገዥያቸው እንደሆነ በመናገር ከእግዚአብሔር ውጭ ንጉሥ እንደማያስፈልጋቸው በመናገር የሕዝቡን ጥያቄ አልተቀበለም። ነገር ግን ሕዝቡ በዘመናቸው በነበረው በዙሪያቸው ያሉት ሕዝቦች ንጉሥ እንዳላቸው በመናገር አብዝተው ንጉሥን እንዲያነግስላቸው ጠየቁ። ነቢዩ ሳሙኤልም ጥያቄያቸውን ወደ እግዚአብሔር አመጣ። እግዚአብሔርም ለነቢዩ ንጉሥን ከፈለጉ እንደሚያነግስላቸው በመናገር ንጉሥ ከነገሰ ገዢያቸው እንደሚሆኑና የእነሱ ንብረት የንጉሡ እንደሚሆን ሴቶችና ወንዶች ልጆቻቸው ለንጉሡ ባሪያዎች እንደሚሆኑ ተናገረ። በእስራኤል ሕዝብ ጥያቄ መሠረት የአባቱን የጠፉ አህዮችን ፍለጋ የወጣውን ሳዖልን ንጉሥ እንዲሆን ነቢዩ በእግዚአብሔር ምሪት ቀባው።
ንጉሥ ሳዖልንም ያነገሰው የእስራኤል ልጆች ምኞት የአህዛብ መንግስት ህግና ስርዓት ነበር። ሳዖል እስራኤላውያን እንደ አህዛብ ዓይነት መንግስት ይግዛን ባሉ ጊዜ የተቀባ ንጉሥ ነበር። ሳዖል በአስራኤል ላይ የነገሠው በተለይም በአህዛብ ወታደራዊ እውቅት፣ ጥበብና ኃይል ነበር። የዲያብሎስ መንግስት የተባለውም ይህ ነው። ስለዚህም ነበር እግዚአብሔር አምላክ በነቢዩ በሳሙኤል አፍ "ለራሳችሁ ከመረጣችሁት ንጉሥ የተነሳ በመጨረሻ ትጮሃላችሁ እግዚአብሔርም አልሰማም" በማለት የተናገራቸው።
Blogger Comment
Facebook Comment