ዘርአዳዊት ዘ-ኢትዮጵያ
[የማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ ፳፬፥፴፯፡፴፱]
"የኖኅ ዘመን እንደ ነበረ የሰው ልጅ መምጣት እንዲሁ ይሆናልና። በዚያች ወራት ከጥፋት ውኃ በፊት፥ ኖኅ ወደ መርከብ እስከገባበት ቀን ድረስ፥ ሲበሉና ሲጠጡ ሲያገቡና ሲጋቡም እንደ ነበሩ፥ የጥፋት ውኃም መጥቶ ሁሉን እስከ ወሰደ ድረስ እንዳላወቁ፥ የሰው ልጅ መምጣት ደግሞ እንዲሁ ይሆናል።"
ወረራ እያካሄዱ ያሉት እነማን እንደሆኑ እያየናቸው ነው፤ አዎ! ይህም የቍራ ወረራ ቀላል ነገር አይመስለኝም፤ ቍራዎች በየሃገሩ በዝተዋል፣ ሌሊት ሁሉ ሳይቀር ሲጮሁ ይሰማሉ።
በመጽሐፍ ቅዱስ መጀመሪያ የተጠቀሰችው ወፍ ቍራ ስትሆን ቀጥሎም ርግብ ናት። ከተዓምረኛው የማርያም መቀነት ክስተት ጋር በተያያዘ ሰሞኑን አባታችን ኖህን እያስታወስነው ነው።
[ኦሪት ዘፍጥረት ምዕራፍ ፰፥]
፯ ቁራንም ሰደደው፤ እርሱም ወጣ፤ ውኃው ከምድር ላይ እስኪደርቅ ድረስ ወዲያና ወዲህ ይበር ነበር።
፰ ርግብንም ውኃው ከምድር ፊት ቀልሎ እንደ ሆነ እንድታይ ከእርሱ ዘንድ ሰደዳት።
Blogger Comment
Facebook Comment