ዘርአዳዊት ዘ-ኢትዮጵያ
በቤተክርስቲያን ፍቅር ተውጠው፣ ቤታችን አናድርም እናስቀድስ ብለው በትንሣኤው ዋዜማ ማምሻውን ከመኖሪያ ቤታቸው ወጥተው ህይወታቸውን ያጡት ስድስት ሴት እህቶች እና አንድ ታዳጊ ወጣት የሰንበት ትምህርት ቤት ተተኪ አባላት በናዝሬት ወረዳ የዲቢቢሳና ዋጩላፋ ቀበሌ ገበሬ ማህበር ልጆች መሆናቸው ታውቋል፡፡ ልብ በሉ፤ መጀመሪያ ላይ ስድስት ወንዶች እና አንዲት ሴት ተብሎ ነበር።
ግድያውን የፈጸሙትም ልክ ቃል እንደገቡት ቤተ ክርስቲያን ውስጥ፣ እንደተመኙት በብርሃነ ትንሣኤ ዕለት(በጨለማው ረመዳን መግቢያ)እንደለመዱት ጨለማን ተገን አድርገው፣ እንዳቀዱት በሴት ህፃናት የተዋሕዶ ልጆች ላይ። የለመዱትን የማጭበርበሪያ ዘዴ በመከተል "የጄነሬተር ጭስ፣ መጀመሪያ 6ወንዶች አንዲት ሴት ፤ ከዚያም 6ሴቶች እና አንድ ወንድ(የደምቢዶሎውን ድራማ እናስታውሳለን?) አሉን ፥ ብዙም ሳይቆዩ ፣ በበነገታው፤ ይህ የግድያ ተግባራቸው ቁጣ እንዳይቀሰቅስና ጉዳዩን ከኦሮሚያ ሲዖል ቶሎ አውጥቶ ጉዳዩን ለማስቀየስ "በደቡብ ኢትዮጵያ9 ኢትዮጵያውያን ህጻናት በታጣቂዎች ታግተው ተወሰዱ" የሚል ዜና እንዲሠራጭ ተደረገ።
አትኩሮታቸው ሁሉ የህብረተሰቡ ምሰሶዎች በሆኑት ሴቶችና ሕፃናት ላይ ነው።
በሴት ሕፃናቶቻችን ላይ እየተፈጸመ ያለውና በታሪካችን አይተነውም ሰምተነውም ለማናውቀው አሰቃቂ ወንጀል ሁሉ የሚከተሉት ግለሰቦች በጥብቅ ተጠያቂዎች ናቸው፤ ኢትዮጵያውያን ስሞቻቸውን መዝግቡ፦
ዐቢይ አሕመድ ፣ ለማ መገርሳ ፣ ታከለ ኡማ ፣ ሽመልስ አብዲሳ ፣ ጃዋር መሀመድ ፣ በቀለ ገርባ ፣ ህዝቄል ገቢሳ ፣ ዳውድ ኢብሳ ፣ አምቦ አርጌ ፣ ፀጋዬ አራርሳ ፣ አደነች አቤቤ ፣ ሞፈሪያት ካሜል ፣ መአዛ አሸናፊ ፣ ሳህለወርቅ ዘውዴ ፣ ብርቱካን ሚደግሳ ፣ ታዬ ደንደአ ፣ ሌንጮ ባቲ ፣ ሌንጮ ለታ ፣ ዳንኤል ክብረት ፣ ብርሀኑ ነጋ ፣ ገዱ አንዳርጋቸው ፣ ደመቀ መኮንን ፣ አንዳርጋቸው ፅጌ ፣ አንዱዓለም አንዳርጌ ፣ ታማኝ በየነ ፣ አበበ ገላው
Blogger Comment
Facebook Comment