ዘርአዳዊት ዘ-ኢትዮጵያ
በኮሮና ተጠቅተው የነበሩት ሁለት የቻይና ዶክተሮች ከማገገሚያ አልጋቸው ሲነቁ ቢጫው ቆዳቸው ሙሉ በሙሉ ጠቁሮባቸው ተገኘ።
ኮሮና ጋኔን ናት ፥ ዘረኝነት የጋኔን አንዱ መገለጫ ነው!
እንግዲህ የእነዚህ ሁለት ዶክተሮች መጥቆር ሰሞኑን ቻይናውያን በጥቁር ሰዎች ላይ እያራገፉት ያለውን የዘረኝነትን ጋኔን "ዋ! ዋ!ዊ! ዋ!" እያሉ እራሳቸውን በመስተዋት እንዲያዩት ይረዳቸው ይሆናል።
በጣም የሚገርም ዘመን እኮ ነው፡ ጃል! ግን የዘረኝነትን ውጤቶች እያየን ነው? ነጮቹ ቻይናን በኮሮና ቫይረስ ከበከሏት በኋላ ሌት ተቀን ይኮንኗታል ፥ ቻይና ግን በሚሊየን ለሚቆጠሩ ቻይናውያን የአገሮቻቸውን በሮች ብርግድ አድርገው የከፈቱትን ጥቁሮችን ታጠቃለች። ታዲያ የምዕራብ እና ምስራቅ ኢ-አህማንያን ሁሉም አብረው በአንድነት እየሠሩ እንደሆነ አይነግረንምን? የተገለባበጠባት ዓለም።
እግዚአብሐር አምላክ ከሦስት ሺህ ሦስት መቶ ዓመታት በፊት ያስተማረን ይህን ነበር፤ የሰው ልጅ ግን ተምሮ ለመለወጥ ሰንፏል።
[ኦሪት ዘኍልቍ ምዕራፍ ፲፪፥]
፩ ሙሴም ኢትዮጵያይቱን አግብቶአልና ባገባት በኢትዮጵያይቱ ምክንያት ማርያምና አሮን በእርሱ ላይ ተናገሩ።
፪ እነርሱም። በውኑ እግዚአብሔር በሙሴ ብቻ ተናግሮአልን? በእኛስ ደግሞ የተናገረ አይደለምን? አሉ፤ እግዚአብሔርም ሰማ።
፫ ሙሴም በምድር ላይ ካሉት ሰዎች ሁሉ ይልቅ እጅግ ትሑት ሰው ነበረ።
፬ እግዚአብሔርም ወዲያው ሙሴንና አሮንን ማርያምንም። ሦስታችሁ ወደ መገኛኛው ድንኳን ውጡ ብሎ ተናገረ፤ ሦስቱም ወጡ።
፭ እግዚአብሔርም በደመና ዓምድ ወረደ፥ በድንኳኑም ደጃፍ ቆመ፤ አሮንንና ማርያምን ጠራ፥ ሁለቱም ወጡ።
፮ እርሱም። ቃሌን ስሙ፤ በመካከላችሁ ነቢይ ቢኖር፥ እኔ እግዚአብሔር በራእይ እገለጥለታለሁ፥ ወይም በሕልም እናገረዋለሁ።
፯ ባሪያዬ ሙሴ ግን እንዲህ አይደለም፤ እርሱ በቤቴ ሁሉ የታመነ ነው።
፰ እኔ አፍ ለአፍ በግልጥ እናገረዋለሁ፥ በምሳሌ አይደለም፤ የእግዚአብሔርንም መልክ ያያል፤ በባሪያዬ በሙሴ ላይ ትናገሩ ዘንድ ስለ ምን አልፈራችሁም? አለ።
፱ እግዚአብሔርም ተቈጥቶባቸው ሄደ።
፲ ደመናውም ከድንኳኑ ተነሣ፤ እነሆም፥ ማርያም ለምጻም ሆነች፥ እንደ አመዳይም ነጭ ሆነች፤ አሮንም ማርያምን ተመለከተ፥ እነሆም፥ ለምጻም ሆና ነበር።
Blogger Comment
Facebook Comment