ዛሬ ከ፪ሺ፲፪ ዓመታት በኋላ በዕለተ ስቅለት ዝናብ እና ደመና በሌለበት የቅድስት እናቱን መቀነት አሳየን።


ዘርአዳዊት ዘ-ኢትዮጵያ

ጌታችን ሲሰቀል ፀሐይ ጨለመች፣ ጨረቃ ደም ኾነች፤ ክዋክብትም ረገፉ ፥ ዛሬ ከ፪ሺ፲፪ ዓመታት በኋላ በዕለተ ስቅለት ዝናብ እና ደመና በሌለበት የቅድስት እናቱን መቀነት አሳየን። ታዲያ ይህ ድንቅ ተዓምር አይደለምን?! ነው እንጂ!

አዎ! አውሬው በእመቤታችን የአሥራት ሀገር ሊነግሥና የልጇን ደምና ስጋ ለመከልከል ሲቃጣና ሲደፍር ይታያል። ኢትዮጵያውያንን አግቶ ሲሳለቅ፣ ኢትዮጵያውያንን ከእስማኤላውያን ሀገራት አምጥቶ እንደ ከብት አውቶብስ ውስጥ እየጫነ በንቀት ከአዲስ አበባ ሲጠርፍ ፣ ለሁለት ወር ሲጾሙና ሲሰግዱ የቆዩትን ኢትዮጵያውያንን በፋሲካ ዋዜማ ከስራቸው ሲያባርር እና እናቶችን ቤት-አልባ አድርጎ ወደ መንገድ ሲጥላቸው፤ እግዚአብሔር አምላክ መልሱን በሰማይ ሰጠ። 

ትክክለኛዋና ብቸኛዋ የእግዚአብሔር ሃይማኖት በተዓምር፣ በማርያም መቀነት / በቀስተ ደመና የታጀበች እምዬ ርትዕት ተዋሕዶ ፥ ዓድዋ ዘምታ ጊዮርጊስ ድል ያደረገላት፣ መከላከያ ሚንስትሯ ጊዮርጊስ የሆነ፣ ጳጳሳቷ ለሀገር የሞቱ፣ አንድነት የምትሰብክ፣ የድኾች መጠጊያ፣ ፀበሏ የሚፈውስ፣ እምነቷ የሚፈውስ፣ ደመራዋ የሚያምር፣ ጥምቀቷ የሚያምር፣ አፅዋማቷ የሚያምሩ፣ ሥርዓቷ፣ መጻሕፍቷ፣ ገዳማቷ፣ ውቅር ዓብያተክርስቲያናቷ፣ የካህናቱ ዝማሬው፣ ቅኔው፣ ማሕሌቱ፣ ቅዳሴው፣ አለባበሳችን ፥ ሁሉ ነገራችን እንደ ርትዕት ተዋሕዶ የሚያምርና የሚያስገርም የለም። አውሬው ግን በዚህ ይቀናል፣ ይበሳጫል ፥ ስለዚህ በተፈቀደለት በዚህ አጭር ዘመን ይህን የእግዚአብሔር ስጦታ ለመንጠቅ ሌት ተቀን በመወራጨት ላይ ይገኛል። አንድ የዝሆን እርምጃ ወደፊት ሲራመድ እግዚአብሔር ማስጠንቀቂያውን ይሰጠዋል።

ይህ የማርያም መቀነት ኃይለኛ ምልክት ነው!ተመሳሳይ የማስጠንቀቂያ ምልክት ለቅሌታሙ የግብረ-ሰዶማውያን ልዑክ ለባራክ ሁሴን ኦባማም ከአምስት ዓመታት በፊት ልክ የኢትዮጵያን ምድር ሲረግጥ ተሰጥቶት ነበር።

Share on Google Plus

ስለ የተለጠፈበት ቀን

    Blogger Comment
    Facebook Comment