የመለስ ዜናዊ ስንክሳር በቤተ ክርስትያን?


ዘርአዳዊት ዘ-ኢትዮጵያ

የኢትዮጵያ ተዋሕዶ ቤተክርስትያን በኢ-አማኝ የምዕራባውያን ተላላኪዎች ኮሚኒስቶች ቁጥጥር ሥር ከወደቀች ፵፭ ዓመታት ተቆጥረዋል። እነዚኽ የዘንዶው አውሬ ዕቅድ አስፈጻሚዎች ሀገረ እግዚአብሔር ኢትዮጵያ ለማጥፋት መሰረትዋ የሆነቺው ቅድስት ርትዕት ተዋሕዶ ሃይማኖት ማጥፋት ዋነኛው ስራቸው ነው። "የተዋሕዶ ቤተክርስትያን አከርካሪ ሰብረናል!" ብለው በአደባባይ ለመናገር የደፈሩትም በዚኽ ምክንያት ነው። 

የኢሕአዴግ መንግስሥት ቅድስት ርትዕት ተዋሕዶ ቤተክርስትያን በዘረጋው መዋቅር ሥር በማድረግ እስከ አሁን በቁጥጥሩ በማድረግ የዓላማው አስፈጻሚ አድርጓታል። ይህንን ሰይጣናዊ ሥራ ከፈጸሙት መሪዎችም ነፍስሔር መለስ ዜናዊ አንደኛው ነው። ዕድሜልኩ በኮሚኒስታዊ አስተሳሰብ ጸረ-ኢትዮጵያ ሲንቀሳቀስ የነበረው መለስ ዜናዊን የሚዘክር የስንክሳር መጽሐፍ በዓቢይ ዓዲ ለሚገኝ ቤተክርስትያን እንደተሰጠ አንብበናል ሰምተናል። ይህ የሚያመላክተን የደረስንበት መንፈሳዊ ዝቅጠትና ቤተክርስትያን በዘንደው ቁጥጥር ሥር ሙሉበሙሉ መውደቋ ነው። “ኢ–አማንያን አብዮተኞችን” ካፈራው የጄነራል ዊንጌት ትምህርት ቤት የተመረቀው መለስ ዜናዊ የቤተ ክርስትያን ጸር እንጂ ባለ ውለታ የሚሆን አይመስለኝም። አንገታቸውን ለኢትዮጵያ በመስጠት "የተዋሕዶ የቁርጥ ቀን!" ልጅ የሚል ስያሜ ያገኙት አባታችን አጼ ዩሐንስ ፬ኛ እንኳን ይህንን ክብር ያገኙት አይመስለኝም።
Share on Google Plus

ስለ የተለጠፈበት ቀን

    Blogger Comment
    Facebook Comment