ዘርአዳዊት ዘ-ኢትዮጵያ
1400 ዓመታት በዘለቀው የእስልምና ታሪክ ይህ ለመጀመሪያ ጊዜ ሳይሆን አይቀርም፤ አስከፊ በነበረውና 50 ሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎች በሞቱበት የ 1918ቱ ዓ.ም የስፔን ጉንፋን እንኳን ወደ መካና መዲና ሃጅ አልተከለከለም ነበር። ዋው! “ቅዱስ” የምትባላዋ የኢራን ከተማ ቆም በቫይረሱ መጠቃቷ አስደንግጧቸዋል።
በቫይረሱ የተጠቃቸው የኢራኗ ምክትል ፕሬዚደንት፡ በአውሮፓውያኑ 1979 ዓ.ም ላይ በኢራን በሚገኘው የአሜሪካ ኢምባሲ 52 አሜሪካውያን ለአንድ ዓመት ያህል ታግተው በነበሩበት ወቅት የኢራን መንግስት የእንግሊዝኛ ቋንቋ ቃል አቀባይ ካድሬ ሆና ስታገለግል ነበር። አሁን አራት የኢራን ከፍተኛ ባለስልጣናት በቫይረሱ ተጠቅተዋል።
በስፔን፣ ባርሴሎና መካሄድ የነበረበትም ዓመታዊው የዓለም ሞባይል መድረክም በቫይረሱ ፍራቻ አሁን ተሠርዟል።
Blogger Comment
Facebook Comment