መጽሐፍ ቅዱስ፦ አንድ ዓለም ሥርዓት ለመመስረት የሚጣደፉት ፍየል አምላኪዎች የሚፈሩት መጽሐፍ



ዘርአዳዊት ዘ-ኢትዮጵያ

እባክዎን ይህንን ልብ ይበሉ ከፍየል አምላኪዎች ጋር የሚደረግ ውጊያ ሥጋዊ አይደለም። ምክንያቱም አለቃቸው ሰይጣን ነው። ስይጣንም መንፈስ እንጂ ሥጋ አይደለም። ፍየል አምላኪዎችና አለቃቸው ሰይጣንን ሊያሸነፍ የሚችለው ማን ነው፧ የእግዚአብሔር ቃል ነው።…… ኢየሱስ ክርስቶስ ያንን እባብ ቀድሞውን አሸንፎታል።

[፪ኛ ቆሮንቶስ  ፲፥  ፫፡፭]

በሰው ልማድ ምንም እንኳ የምንመላለስ ብንሆን እንደ በሰው ልማድ ፈቃድ አንዋጋም፤

የጦር ዕቃችን ሥጋዊ አይደለምና ምሽግን ለመስበር ግን በእግዚአብሔር ፊት ብርቱ ነው፤

የሰውንም ዐሳብ በእግዚአብሔርም እውቀት ላይ የሚነሣውን ከፍ ያለውን ነገር ሁሉ እናፈርሳለን ለክርስቶስም ለመታዘዝ አእምሮን ሁሉ እንማርካለን።

[ኤፌሶን  ፮፥ ፲፪]
መጋደላችን ከደምና ከሥጋ ጋር አይደለምና ከአለቆችና ከሥልጣናት ጋራ ከዚህም ከጨለማ ዓለም ገዢዎች ጋራ በሰማያዊው ስፍራ ካለ ከክፋት መንፈሳውያን ሰራዊት ጋራ ነው እንጂ።

[ዕብራውያን  ፬፥ ፲፪፡፲፫]

የእግዚአብሔር ቃል ሕያው ነውና የሚሠራም ኹለትም አፍ ካለው ሰይፍ ኹሉ ይልቅ የተሳለ ነው፥ ነፍስንና መንፈስንም  ዥማትንና ቅልጥምንም  እስኪለይ  ድረስ  ይወጋል የልብንም  ስሜትና  ዐሳብ ይመረመራል።

[ዩሐንስ ራዕይ  ፩፥፫]

ዘመኑ ቀርቧልና የሚያነበው የትንቢቱን ቃል የሚሰሙትና በውስጡ የተጻፈዉን የሚጠብቁት ብፁዓን ናቸው።

[ዮሐንስ ራዕይ ምዕራፍ ፲፫፥፲፭]

“የአውሬው ምስል ሊናገር እንኳ ለአውሬውም ምስል የማይሰግዱለትን ሁሉ ሊያስገድላቸው፥ ለአውሬው ምስል ትንፋሽ እንዲሰጠው ተሰጠው።”
እግዚአብሔር ሁላችንንም ይጠብቀን፣ ሁሉንም ይጠብቃቸው። የፍጻሜ ዘመን ላይ ደርሰናል፤ የመጽሐፍ ቅዱስ ትንቢታዊ ምስክርነት የፍጻሜ ዘመን ቃጭል እንደሆነ እያየን ነው።

የኮሮና ቫይራስ ክስተት ባስከተለው ስጋት በቻይና፣ በደቡብ ኮሪያ፣ በጣልያን ዓብያተ ክርስቲያናት በሮቻቸውን ዘግተዋል፤ የተለመደውን የሰንበት አገልግሎት ሁሉ ከመስጠት ተቆጥበዋል።

ቅዱስ ዮሐንስ “መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሐ ግቡ፡፡” ፣ “ከእኔ በኋላ የሚመጣው በመንፈስ ቅዱስ እና በእሳት ያጠምቃችኋል”፣ “የዓለምን ኃጢአት የሚያስወግድ የእግዚአብሔር በግ እነሆ” እያለ ምሥጢራትን / ምስጢረ ጥምቀት፣ ምስጢረ ንስሐን እና ምስጢረ ቁርባንን / እንድንካፈል ያስተምረናል፡፡

ጥምቀት፣ ቁርባን፣ ንስሐ ስንት መንፈሳዊ ሀብትና ጸጋ እንደሁም ከፍ ያለ የእግዚአብሔር ልጆች ክብር ስለሚሰጡን በተለይ በአሁኑ ጊዜ ተቀዳሚዎቹ የዲያብሎስ ጥቃት ዒላማዎች ናቸው። ባሕረ ጥምቀተን በመከልከል፣ የጥምቀት በዓልን በመተናኮል፣ ፀበላቱንና የሕይወት ህብስትን በመመረዝ፣ ብሎም ለንስሐ የተዘጋጁትን የክርስቶስ ልጆች ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ገብቶ በመግደል በፀረ-ቤተ ክርስቲያን ዘመቻው ዲያብሎስ ምን ያህል ርቆ ለመሄድ እንደበቃ ዓይናችን እያየው ጆሮአችንም እየሰማው ነው።

በድጋሚ እግዚአብሔር ይጠብቀን እንጂ በቀጣዩና በቅርቡ ዲያብሎስ አውሬው በሃገራችን ሊፈጽመው ያቀደው ክስተት እርሱን የማይቀበለውንና ለእርሱ የማይሰግድለትን ሕዝበ ክርስቲያኑን ከቤተ ክርስቲያን ማራቅ ለዚህም እንደ ኮሮና ቫይረስ የመሳሰሉትን ተላላፊ በሽታዎች ከማሰራጨት ጋር የተያያዘ ነው። ልክ ዛሬ በቻይና፣ ደቡብ ኮርያ እና ጣልያን እንደሆነው በሃገራችንም ዓብያተ ክርስቲያናት በሮቻቸውን የሚዘጉበት፣ የሰንበት ቅዳሴዎች የሚቋረጡበት ጊዜ ሩቅ አይደለም። እግዚአብሔር እስከፈቀደልን ድረስ እንዲህ በትጋት እንቀጥልበታለን፤ ነገር ግን ለሁሉም ነገር አስቀድመን ብንዘጋጅ ጥሩ ነው!

2012 – የኢትዮጵያ ግመሎች – ሳውዲ ዓረቢያ – ኮሮና ቫይረስ

በነገራችን ላይ፤ ኮሮና ቫይረስ አሁን ሁላችንም እንደሰማነው በቻይና መቀስቀሱን ነው። ይህም ሆን ተብሎ የተደረገ ነው። ነገር ግን ኮሮና ቫይረስ የጀመረው ከሰባት ዓመታት በፊት፡በአውሮፓውያኑ 2012 ዓ.ም ላይ በሳውዲ ዓረቢያ ነው (ከኢትዮጵያ ወደ ሳውዲ የተላኩ ግመሎች ያመጡት ፤ “MERS‐CoV / መርስ-ኮሮና-ቫይረስ”)። በፈረንጁም በኛም 2012 ብዙ ነገሮች ያየንበት / የምናይበት ቁልፍ ዓመት ነው።


Share on Google Plus

ስለ የተለጠፈበት ቀን

    Blogger Comment
    Facebook Comment