ቱርክ በሀገራችን ላይ አሁንም እየፈጸመች ያለችው ወንጀል

የኢትዮጵያ አውታር - Ethiopia Awtar ምስል

ዘርአዳዊት ዘ-ኢትዮጵያ

ሀገር ቤትም ሆነ ውጭ ያሉት ፖለቲከኞች ሁሉ የፖለቲካ እንተ ፈንቶ ትተው በእግዚአብሔር ሥርዓት ውስጥ ቢሆኑ ኖሮ ማንንም ምንንም ባልፈሩና የነጮችና ዓረቦች ባርያ ባልሆኑ ነበር።
በተለይ ፀረ-ክርስቶሷ ታሪካዊ ጠላታችን ቱርክ ባሀገራችን ላይ አሁንም እየፈጸመች ያለችው ወንጀል ደም እንባ የሚያስለቅስ ነው፣ አባቶቻችንና እናቶቻችንን ከመቃብር የሚያስነሳ ነው። ከዓረቦች ጋር ሆና ውሃውን፣ ጤፉን፣ ዱቄቱን፣ ከብቱን፣ ዘይቱንና ስኳሩን እየመረዘች ነው። ምዕራባውያኑ በኪኒን፣ መርፌና ቴክኖሎጂው፣ እስማኤላውያኑ ደግሞ በሕዝብ መሐል ሰርገው ገብተው በምግባችን፣ መጠጣችን እና ልብሳችን ላይ ዘምተዋል።
በተጨማሪ ቱርክ የጦር ሠራዊቷን በሶማሊያ እና ሱዳን በማከማቸት ላይ ትገኛለች፤ ግብጽን እና ሳዑዲ አረቢያን እንደቀድሞው ለመቆጣጠር ስለምታልም፤ ዋናው ትኩረቷ ዓባይና ጣና ሃይቅ ላይ ነው። በጣና ሃይቅ የታየው አረም በቱርኮች የተዘራ ነው ቢሉን አይድነቀን፤ ወደ አዲስ አበባ የሚበረው የቱርክ አየር መንገድም ልክ በጣና ሃይቅ ሰማይ በኩል ነው በየቀኑ የሚያልፈው።
ቤተመንግስት ውስጥ የገባው አንዱ ዘንዶም ከጣልያን ወረራና ወረራው ካስከተለው የአፄ ኃይለ ሥላሴ የእንግሊዝ ሀገር የስደት ኑሮ ጋር የተያያዘ ነው።
ደጋግሜ የምለው ነው፤ ኢትዮጵያ የሁሉም ኢትዮጵያውያን ሀገር ናት፤ እግዚአብሔር በሰጠን ሀገር ሌላ ሕዝብ ወይም የውጭ ኃይል ዕጣዋን የመወሰን መብት የለውም።
Share on Google Plus

ስለ የተለጠፈበት ቀን

    Blogger Comment
    Facebook Comment