ኮራጁ ዲያብሎስ ፀረ-ክርስቶሱም የራሱ የሆኑትን ሁሉ ለዓላማው በመላው ዓለም በጋራ ሰብስቧቸዋል

ዘርአዳዊት ዘ-ኢትዮጵያ
መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ፡ “ይሁዳዊ ወይም የግሪክ ሰው የለም፥ ባሪያ ወይም ጨዋ ሰው የለም፥ ወንድም ሴትም የለም፤ ሁላችሁ በክርስቶስ ኢየሱስ አንድ ሰው ናችሁና” ይለናል።
ኮራጁ ዲያብሎስ ፀረ-ክርስቶሱም የራሱ የሆኑትን ሁሉ ለዓላማው በመላው ዓለም በጋራ ሰብስቧቸዋል፦
ለምሳሌ ኮሙኒዝም “የዓለም ወዛደሮች ሁሉ ተባበሩ” በሚል መርሆ አመጸኞቹን ግራኞች ያስተባብራል፣ እስልምና ለ “ኡማችን / እናታችን” በሚል መርሆ በመላው ዓለም ያሉትን ግራኝ ሙስሊሞች ሁሉ ያስተባብራል፣ ዓለማዊነት/ ሴኩላሪዝም ደግሞ 'ኢ-ዓማናይ' የሆኑትን ግራኝ ልጆቹን በመላው ዓለም ያስተባብራል። ዓለማውያኑ ምዕራባውያን ሙስሊሞችን አምልኳቸውን ወደ ሀገሮቻቸው ሲያስገቡ፣ ሙስሊሞቹ ደግሞ ወደ ሀገሮቻቸው የምዕራባውያኑን አምልኮና የገበያ ማዕከላት ያስገባሉ፤ ዓብያተ ክርስትያናትን ግን ይከለክላሉ።
የኢትዮጵያ አውታር - Ethiopia Awtar ምስል
እነዚህ ሦስት ቡድኖች የተለያየ የሚመስል መንገድ ቢከተሉም ግን የሁሉም መንፈስ አንድ ዓይነት ነው፤ ሁሉም የፀረ-ክርስቶሱን ልብስ ለብሰዋልና። ምንም እንኳን ተልዕኳቸው ዓለም አቀፋዊ ባሕርይ የያዘ መስሎ ቢታይም፤ እግረ መንገዳቸውን ግን “ብሔራዊ” ማንነታቸውን በመላው ዓለም ለማሰራጨት ነው የተነሱት፦

ኮሙኒዝም እና ሴኩላሪዝም የምዕራባውያኑን ባሕል፣ ቋንቋና አምልኮት፤ እስልምና ደግሞ የዓረቡን ባሕል፣ ቋንቋና አምልኮት ለማስፋፋት ይታገላሉ።
በሀገራችን የሚታዩት ፀረ-ኢትዮጵያዊነትና ፀረ-ተዋሕዶ ዘመቻዎች የእነዚህ ሦስት ቡድኖች ወኪሎች መሆናቸው በግልጽ የሚታይ ነው። አኩሪውን ክርስቲያናዊው ኢትዮጵያዊ ማንነታችንን ለማጥፋት በክህደት ውሃ የተጠመቁት ወገኖቻችን ለዓለም አቀፋዊው የሉሲፈራዊ ሥርዓት እራሳቸውን አሳልፈው መስጠታቸው በጣም የሚያሳዝን ነው። ያውም ለጊዚያዊ ጥቅም ሲሉ!
የዓረቡ፣ የህንዱ፣ የሱዳኑ፣ የሶማሌውና የቻይናው መጉረፍ፣ ጎረቤት ሀገሮች እየፈራረሱ ስደተኞች ወደ ኢትዮጵያ እንዲገቡ መደረጉ፣ እንዲሁም የጠንቋዩ፣ የቃልቻው፣ የዕጹ፣ የሺሻው፣ የቡናው ወዘተ ባህል መስፋፋት በኢትዮጲያዊነት ላይ የተጠነሰሰ ሤራ መኖሩን ይጠቁመናል። ኢትዮጵያዊነት = ክርስትና!
እህቶቻችንን ወደ ዓረብ ሀገር በመላክ በጋኔን እንዲሞሉና ወደ ኢትዮጵያም ተመልሰው ቡናውን ለሰዎች በየቦታው እንዲያጠጡ ይደረጋሉ፣ ሰይጣናዊውን የኢሬቻ በዓል ብሔራዊ በዓል ለማድረግ ይሞከራል፣ (መስቀልን ለመተካት … በመስቀል ክብረ በዓል ማግስት) ፣ የተዋሕዶ ወጣቶችን በእናት ቤተክርስቲያናቸው መንፈሳዊ መዝሙሮችን እንዳይዘምሩ ሲተናኮሏቸው፤ የራያ ጨፋሪዎች ግን በየቤተክርስቲያኑ ሰተት ብለው እንዲገቡና ባሕላቸውን እንዲያስተዋውቁ ይታዘዛሉ።
ይህን ከባድ የፈተና ጊዜ የመወጣቱ ኃላፊነት ያለብን እኛ እያንዳንዳችን ነን፤ በግላችን፡ ከታች ወደላይ ማድረግ የሚገባንን ሁሉ ማድረግ ከቻልን የጠላቶቻችንና ተባባሪዎቻቸው ሤራ ብዙም ሊያሳስበን አይገባም።
Share on Google Plus

ስለ የተለጠፈበት ቀን

    Blogger Comment
    Facebook Comment