ዶክተር አብይ የእኛ እና የአሜሪካን ፋላጎት ነው የሚያስፈጽመው ሲሉ በአውሮፓ ህብረት የምስራቅ አፍሪካ ተወካይ ተናገሩ

በአውሮፓ ህብረት  የምስራቅ አፍሪካ ተወካይ የሆኑት አምባሳደር አሌክስ ሮንዶስ ዶክተር አብይ የኛን  እና የአሜሪካ ሃሳብና ፍላጎት ነው እያስፈፀመ ያለው ሲሉ ተናገረዋል፡፡

አምባሳደሩ በንግግራቸው  ነገር ግን አንዳንዴ ስለራሳችን ፍላጎት ብቻ ስናስብ አጠቃላይ የአከባቢው የፀጥታ ሁኔታ ቀጣይ እጣ ፋንታ ያሳስበኛል በማለት ተናገረዋል፡፡
አምባሳደር አሌክስ ሮንዶስ ትውልዳቸው ግሪካዊ ሲሆኑ በውሮፓ ህብረት የምስራቅ አፍሪካ ተወካይ ናቸው፡፡
ታዲያ አምባሳደሩ ከአለም አቀፉ ተቋም ውድረው ዊልሰን ሴንትር ጋር ባደረጉት ቆይታ በኢትዮጰያ ጉዳይ ተጠይቀው  ዶክተር አብይ ለአውሮፓ ህብረት እና ለአሜሪካ ሃሳቦች አስፈጻሚ ነው ያሉ ሲሆን ፤ አሁን ላይ ግን የኢትዮጵ ጉዳይ እያሳሳባቸው እንደመጣ ተናገረዋል፡፡
አምባሳደሩ በንግግራቸው ኢትዮጵያ እንደ ዩጎዝላቪያ አይደለደችም ሲሉ ተናገረዋል፡፡ ኢትዮጵያ እንደ ግድብ ነች ስትፈርስ የአከባቢው ሀገራትም ይጎዳሉ በማለት በአጽንኦት ተናገረዋል፡፡
እ.ኤ.አ  በ1968  በአሜሪካን ሀገር  በ ዋሽንግተን ዲሲ የተቋቋመው የፕሬዚደንት ውድረው ዊልሰን ማሰታወሻ የጥናት ማእከል በተለያዩ ጊዚያት መሪዎችና የተለያዩ ባለሞያዎች እንዲሁም አለም አቀፍ ፖለቲካ ተንታኞችን  በመጋበዝ   በአለማችን አነጋጋሪ ናቸው ብሎ ባመነባቸው ሀሳቦች ላይ አስተያይታቸውን  የሚቀርቡበት አለማቀፍ ድርጀት ነው፡፡
ታዲያ ሰሞኑን አማባሳደር  አሌክስ ሮንዶስን በምስራቅ አፍሪከ እና በኢትዮጵያ ጉዳይ ያነጋገራቸው ሲሆን ኢትዮጵያ አሳሳቢ በሆነ ሁኔታ ውስጥ እንዳለች አስረድተዋል፡፡
ኢትዮጵያ በዚህ ሰአት ውሳኔዎችዋ ሁሉ አጅግ ጥንቃቄ የሚሹ ናቸው፣ በተለይም ፀጥታዋን በማሰከበር በኩል ብዙ ስራ መሰራት እንዳለበት ነው ያስረዱት፡፡   ቀጣይ የኢትዮጵያ የቤት ስራም ሀገሪቷ ወደ ውስጧ መመልከት ይኖርባታል በማለትም አምባሳደሩ ተናገረዋል፡፡
በተመሳሳይ ፕሬዚዳንት ትራምፕ  የኖቤል ሽልማቱን በተመለከተ ባደረጉት ንግግ አሜሪካ እና እራሳቸው ትራምፕ  ኢትዮጵያን ከጦርነት እንደታደጓት ገልጠው ነበር፡፡
ምንጭ፦ አዉሎ ሚድያ ጥር 12/2012 ዓ.ም
Share on Google Plus

ስለ የተለጠፈበት ቀን

    Blogger Comment
    Facebook Comment