የኢትዮጵያ ጠላቶች የኢትዮጵያን ሕዝብ ምን ያህል እንደናቁት እያየን ነው!?



ዘርአዳዊት ዘ-ኢትዮጵያ

በ ግራኝ ዐቢይ አሕመድ የሚመራው የኦሮሞ ጂሃድ በምዕራባውያኑ እና ዓረቦቹ የሚደገፍ መሆኑንና ኢትዮጵያን ለማጥፋት እንደሚጣደፍ ማወቅ የተሳነው ኢትዮጵያዊ ዛሬም መኖሩ በጣም ያሳዝናል።

እነዚህ የኢትዮጵያ ጠላቶች የኢትዮጵያን ሕዝብ ምን ያህል እንደናቁት እያየን ነው!?

[መጽሐፈ መክብብ ፲፥፭]

" ከፀሐይ በታች ያየሁት ክፉ ነገር አለ፥ እርሱም ከገዢ የሚወጣ ስሕተት ነው "

ታዲያ የዛሬዎቹ ገዥዎች ፋሺስት ጣሊያን ከሠራው የከፋ ወንጀል በመፈጸም ላይ ናቸው። የዛሬዎቹ ገዢዎች፦

+ በባዕድ ርዕዮት የብሔር ፌደራሊዝም በዘረኝነት ከፋፈሉን 

+ እርሰበርስ አፋጅን

+ የቅድስ ኪዳን ምልክታችን ሰንደቅ ዓላማ አስወገድ 

+ ርትዕት ተዋሕዶ ቤተክርስትያናችን አቃጠሉ 

+ የክርስቶስ ልጆችን የድንግል ልጆችን ገደሉ፣ አረድ ፣  አቃጠሉ ።

ከ ፵፭ ዓመታት በፊት ጀምሮ የመጡ ገዢዎች ፀረ ቅድስት ሀገር ኢትዮጵያ ናቸው ወገኔ!

ዛሬ ወገን ንስሐ ከመግባት ይልቅ የዘመኑን ዳታኖች ገዢዎች፣ አጭበርባሪዎች፣ ትዕቢተኞች፣ ዘረኞች፣ ጨፍጫፊዎች የሚነዙልህን ውሸትና ዲስኩር እያደመጥክ፣ ሆድህን በወሬ እየሞላህ በሙሉ ልትጠረግ ደርሰሃል፤ እየሞትክም የእነርሱን የተቀመመ ፍደሣ (propoganda)አሁንም ታዳምጣለህ፤ ሁለት እግር አለኝ ብለህ ሁለት ዛፍ ላይ ለመውጣት ትታገላለህ፤ ወዲህ አንዳንዴም የእግዚአብሔርን ቃል ልትሰማ ትፈልጋለህ ፥ ወዲያ ደግሞ ሕይወትህንም ኑሮህንም እነርሱ ናቸው ብለህ አምነህ የዘመኑን ፈርዖኖች፣ የዘመኑን ዳታኖች፣ የዘመኑን ሆድ–አደሮች፣ የዘመኑን ጨካኞች ዘረኞች ታምነህ ትሠማራለሁ፣ ትውጣለህ ትወርዳለህ።

ሕዝቡ በፈቃዱ ታሳሪ ሆኗል ፥ ከፈጣሪው የተጋጨ፣ የረከሰ፣ በምንዝርና፣ በሰዶምነት፣ በጠጭነት የተበከለ፣ ሰውነቱ ሁሉ የተልፈሰፈሰ ትውልድ ፈጥረው እንዳሻቸው እየፈጩት፣ እየነዱት ይገኛል፤ ልብ ላለው ሰው ይህ የሚያየው የየዕለቱ ተግባር ነው። የዛሬው ትውልድ የሆንከው ወገኔ ለምን የገዢዎች ፍደሣ (propoganda) ቀለብተኛ ትሆናለህ?! ለምንስ እራስህን ለሞት አሳልፈህ ትሰጣለህ?! በምድርም ውዳቂ፣ በሰማይም የሲዖል እራት፤ የገሃነም ወራሽ ለምን ትሆናለህ?! ለምን የፈጣሪህን ቃል ሰምተህ ተፀፅተህ ከጠፋህበት ተመልሰህ ወደ ፈጣሪ ጉያ አትሰበሰብም?! ፈጣሪ በተለያዮ መልኮች የማስጠንቀቅያ ደወሉ እየደወለ ነው ። አንተ ግን በፖለቲካው ፍደሣ (propoganda) ታስረኽ አሁንም ስጋኽ አሸንፎኽ በግራ መጋባት ውስጥ ትገኛለኽ ። አንተ ህዝብ በእውነት አንጀቴ ትበለዋለኽ ፡ ስለአንተ ሳስብ እንባየ ይመጣል ። እረኛ እንዳጣ መንጋ ተበትነኻል ፡ ግራ ገብቶኻል ።

የዘመናችን ደግሞ አባቶች፣ መምህራን ነን የሚሉ ሁሉ ሕዝቡን በወኔ አያስታጥቁትም፣ በእግዚአብሔር ቃል አያስታጥቁትም፣ ስለ ሀገር፣ ስለ ወገን፣ ስለ እምነት፣ ስለ ሰንደቅ፣ ስለ እርስተ ድንግል፣ ስለ እውነት መዋጋት ወንጀል አድርገው ይሰብካሉ ያስተምራሉ፤ ያ ደግሞ ለጠላት ከፍተኛ መሣሪያ ሆኖ አገልግሏል፤ ይህ ግን ስሕተት ነው። ወገኔ፤ እንግዲያውስ ኃጥያቱ ያለመዋጋቱ፣ ሀገር ሲጠፋ፣ ሃይማኖት ሲፈርስ፣ ሀገር ሲቆራረስ ሰንደቅ ሲረክስ ሲናቅ ዝም ብሎ ማየት ነው፤ የሚያስጠይቅ፡ አባቶቻችን የሄዱበት እውነት ላይ አለመሄድ ነው። ይህ ደግሞ ትልቁ ጥፋታችን ነው።
Share on Google Plus

ስለ የተለጠፈበት ቀን

    Blogger Comment
    Facebook Comment