ዘርአዳዊት ዘ-ኢትዮጵያ
ይህም ነፃ እና ገለልተኛ ፕሬስ በጣም አስፈላጊ ነው ከሚለው የሽልማት ኮሚቴው መርሆ ጋር ስለሚጻረር ትችት እየተሰነዘረበት ነው።
የኖቤል የሰላም ሽልማት በተለምዶ ዲሴምበር10 ቀን ከመካሄዱ አንድ ቀን በፊት የኖቤል የሰላም ሽልማት የዜና ስብሰባ ያካሂዳል ፡፡
ግራኝ ዐቢይ አሕመድ ከኖርዌይ ጠቅላይ ሚኒስትር ኤርና ሶልበርግ ጋር ከተገናኘ በኋላ ከጋዜጠኞች ለሚቀርብለት ጥያቄዎች ለመጠየቅ ፈቃደኛ እንዳልሆነ ከመግለጹ ሌላ በየዓመቱ በኖብል የሰላም ማእከል በሙዚየሙ ውስጥ በሚከበረው የልደት በዓል ላይና ከህፃናት ጋር በሚደረገው ዝግጅት ላይም አይሳተፍም፡፡
ግራኝ ዐቢይ አሕመድ የኖርዌይ ፖለቲከኞች እና ምሁራን ከሚሳተፉበት ሚስጥራዊ ሽልማት ኮሚቴው በኩል ያልተለመደ ትችትና ወቀሳ አግኝቷል ፡፡ "ሀሳብን የመግለጽ ነፃነት እና ነጻ ፕሬስ የሰላም ወሳኝ አካላት ናቸው ብለን እናምናለን ። ግራኝ ዐቢይ አሕመድ የዜና ጉባኤ አለመያዙ ችግር እንዳለበትና በኦስሎ በሚቆይበት ጊዜ መገናኛ ብዙኅን ጋር እንዲነጋገር በጣም ፈልገን ነበር።" ብለዋል ፡፡
ከዚህ በፊት ከመገናኛ ብዙኅን ጋር ለመነጋገር ፍራቻ ተመሳሳይ ፍራቻን አሳይቶ የነበረው በ2009 ዓ.ም ምንም ሳይሰራ ይህን ሽልማት የተረከበው የግራኝ ዐቢይ አሕመድ ሞግዚት ባራክ ሁሴን ኦባማ ነበር ።፡ ተመሳሳይ ላባ ያላቸው ወፎች አንድ ላይ ይበራሉ!
አሁንስ ምን ዓይነት ድራማ አዘጋጅተውልን ይሆን? ምንስ አስደንግጧቸው ይሆን? የኖበል ኮሜቴው ለገዳይ ግራኝ ዐቢይ አሕመድ ሽልማቱን በመስጠቱ ተጸጽቶ ይሆን? ወይንስ ዲዜምበር 10አብዮትን ሊጠብቀው የሚችለው ታላቅ የተቃውሞ ሰልፍ አስደነገጠው ። ብዙ የሚደብቀው ጉዳይ ስላለ በነፃ ከጋዜጠኞች ጋር ነፃ ቃለ መጠይቅ ማድረግ አይችልም፤ በደንብ የተዘጋጀበትና እራሱ ካዘጋጃቸው ጋዜጠኞች ውጭ በገለልተኛ ወይም ተቃዋሚ በግልጽ ሲጠየቅ ታይቶ አይታውቅም ። ለምን? ብላችሁ እራሳችሁ ጠይቁ! ለማንኛውም ኖርዌይ ለዚህ ገዳይ ይህን ሽልማት በመስጠቷ ጽንፈኛ ኦሮሞዎች እየፈጸሙት ላሉት የዘር ማጥፋት ድርጊት ከተጠያቄዎቹ መካከል አንዷ ናት ።
Blogger Comment
Facebook Comment