እ.አ.አ ከ 1837 እስከ 1843 ዓ.ም ባለው ጊዜ ፕሮቴስታንቱ ጀርመናዊ ዮኻን ክራፕፍ ኦሮሚያ የተባለውን ግዛት ለመመሥረት የተነሳሳው ክርስትናን ለማስፋፋት ሳይሆን ፡ እንደ አንድ ፕሮቴስታንት የኢትዮጵያ ቀጥተኛ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያንን ለመዋጋት ነው ። ለዚህም በወራሪነት ባሕርይ ከጀርመኖች ጋር ይስማማሉ በሚል ሃሳብ "ጋላ" ተብለው ሲጠሩ የነበሩትን ጎሳዎች ለማደራጀት የተነሳሳው ። ተልዕኮው የክርስቶስ ተቃዋሚ ተልዕኮ ነው።
በርሊን የክርስቶስ ተቃዋሚው መቀመጫ ከሆኑት ዋና ከተሞች መካከል አንዷ ናት።
- + የፖለቲካ መናኸሪያ በርሊን፣
- + የኤኮኖሚ ለንድን እና ኒው ዮርክ፣
- + የመንፈሳዊ ቫቲካን እና መካ ናቸው።
የራዕይ ዮሐንስ ላይ ከተጠቀሱት ሰባት ዓብያተ ክርስቲያናት(ሁሉም ያሁኗ ቱርክ ውስጥ ነው የሚገኙት) መካከል አንዷ፤ ፐርጋሞን ናት፤ ይህችም የሰይጣን ዙፋን የሚገኝባት ቦታ እንደሆነች ቅዱስ ዮሐንስ ጠቁሞናል ።
ታዲያ ከ ፐርጋሞን የተወሰደው የሰይጣን ኃውልት አሁን የሚገኘው በበርሊን ከተማ ነው ። እነ ሂትለር፣ ቡሽ፣ ኦባማና ሂላሪ ክሊንተን ሁሉም ይህን ኃውልት ለመሳለም ወደ በርሊን ጎራ ብለው ነበር ። ሚሊየን ሙስሊም ወራሪዎችን ወደ ጀርመን ሀገር ያስገባችው ወይዘሮ አንጌላ ሜርከልም ከዚሁ ኃውልት ፊት ለፊት ነው የምትኖረው ፤ ለዚህም ይመስላል ሰላማዊ እና ንጹህ በሆነቸው ጀርመን ላለፉት ጥቂት አመታት ታይቶ የማይታወቅ ቅሌታማ ተግባር ተከላካይ በሌላቸው ጀርመናውያን ህፃናትና ሴቶች ላይ እየተፈጸመ ያለው ።
በየዕለቱ አሰቃቂ ድርጊቶች ይከሰታሉ፣ ሁሉም ውረጅ፡ አንፈልግሽም ይላታል፡ ሆኖም ሴትየዋ ያው 15 ዓመት ሞላት ሥልጣን ላይ ከወጣች፤ ከሥልጣን ለመውረድ ፈቃደኛ አይደለችም፤ በኢትዮጵያ ላይ ተንኮል በመሥራት ላይ ያለቸውን ጀርመን ታጠፋ ዘንድ የተቀመጠች የዘመኑ ኤሊዛቤል ነችና ።
እ.አ.አ. በ 1871 ዓ.ም የተዋሀደችው የጽንፈኛው ማርቲን ሉተሯ ጀርመን (ሁሉም ጀርመን አንድ አይደለም) የፐርጋሞንን የሰይጣን ኃውልት ወደ ሀገሯ በማስገባት ኢትዮጵያን መተናኮል ከጀመረችበት ጊዜ አንስቶ በየጊዜው ስትቀጣ ቆይታለች ።
ጀርመን ቅኝ ግዛቶቿን አጣች፣ የአንደኛውንና ሁለተኛውን የዓለም ጦርነቶች በመቀስቀስ ዜጎቿ ብዙ ተሰቃዩ፣ ለመሰደድ ተገደዱ ፤ የመሰማማት ህልም ነበራት ግን የራሷ ግዛቶች ተቆራረሰው በጎረቤት ሀገራት ተወሰዱ። አሁን ከምስራቁ የጀርመን ክፍል ጋር ከተዋህደችበት ጊዜ አንስቶ እንደገና የወራሪነትና የመስፋፋት መንፈሷ ተቀስቅሷል፤ በዚህም ምናልባት ለሦስተኛው የዓለም ጦርነት እንደገና መንስኤ ልትሆን ትችላለች ። እኔ እንኳን በአቅሜ፡ "ከቀውስ መዳን የምትሹ ከሆነ ከኢትዮጵያ ላይ እጃችሁን አንሱ፣ ፐርጋሞንን ወደ ቱርክ መልሱ" በማለት በተለያዮ ጊዜያት እያሥጠነቀኩኝ ነው ።
Blogger Comment
Facebook Comment