ዘርአዳዊት ዘ-ኢትዮጵያ
ለማንኛውም በጉ ከፍየሎች የሚለይበት ዘመን ላይ ደርሰናልና ህዝበ ክርስቲያኑን አድንዝዞ ለእነ ግራኝ ዐቢይ አሕመድ እንዲሰግድ ያደረገውን ቡናን አንጠጣ፤ ግድ የለም፤ ለፍየሎች እንተውላቸው።
"ድርሳነ ጽዮን ማርያም" :- ተአምር 1 ላይ የተጻፈው በሙሉ ይህ ነው:-
ህዝበ ክርስቲያን ሆይ ልንገራቹ ሁላችሁም ስሙ የተጻፈ መጽሃፍ ሁሉ እኛ ልንመክርበት ተጽፏል እንዳለ ጳውሎስ ሮሜ 13:4 :ከአዳም ልጆች ወገን ሴሩህ የሚባል ሰው ነበር ለሴሩህ ስሙ ብኑ የሚባል ልጅ ተወልዶ በህጻንነቱ ሞተበት በብኑ ስም በተቀረጸው ጣኦት መመለክ ተጀምሯል በመቃብሩም ላይ ሰይጣን የሚወዳት ከሱስ የተነሳ ጾምን የምታሽር የከፋች ዕጽ በቀለች ይህውም በስንዴ መካከል እንክርዳድ የዘራ ጠላት ዲያብሎስ ካለችበት አምጥቶ ዘራት ማቴ ፲፫: ፳፰::
በብኑ ስም ቡን ተብላለች ቡና ማለት ነው: ማክሰኞ ከተፈጠሩት ዕፅዋት መልካምና ክፉ አሉ መልካም ዛፍ መልካም ፍሬን ክፉም ዛፍ ክፉ ፍሬ ያፈራል እንዳለ ማቴ ፯:፲፪
እስማኤላውያን የሚያመልኳቸው የጣኦታቸው መስዋዕት ሆነች የተንባላት አለቃ የሚሆን እስከ መሃመድም ትደርሳለች ተንባላትም ያለ እርሷ ሌላ አይሰውም ተንባላት ማለት የመሃመድ ተከታዮች ናቸው: ጣኦት የሚያመልኩ ባለዛሮችም ይህችኑ ይሰዋሉ የቡና ሱስ ያዘን ብለው ጾምን የሚሽሩ በበዓል የሚወቅጡ ራሳችንን አመመን በማለት በውስጣቸው ላደረ ለሱስ ጋኔን የሚገብሩ ብዙዎች ናቸው ወደ ቅዳሴም እንዳይሄዱ በጥዋት እሷን እየጠጡ ይህችም ዕጽ ክፉ ሁና ሰውን ስታሳስት ትኖራለች::
ተአምር ፪፦
"ሌላም የሚያስረዳና ልቡናን የሚያጸና ስሙ ልንገራችሁ የተንባላት መምህር የነበረ ስሙ መሀመድ የሚባል አንድ ሰው ከመካዱ የተነሳ ከአጋንንት ጋር ይውላል ከዕለታት አንድ ቀን ሲሰግድ በልጅነቱ ያመው የነበረው የራስ ምታት በሽታ ይነሳበታል በዚህ በሽታ እየተሰቃየ ሳለ ከዕለታት በአንዱ ቀን ዲያቢሎስ በተንኮሉ ያስተው ዘንድ ወደ እርሱ መጥቶ ወዳጄ መሀመድ ሆይ ምን ሆንክ ይለዋል የራስ ምታት በሽታ የሆነበት እርሱ ዲያቢሎስ ነው፡፡
መሐመድ መልሶ ከፍተኛ የራስ ምታት ነበረብኝ በዚህ ደዌ እጨነቃለው ይለዋል ዲያቢሎስም የራስ ምታት መድሀኒት ብነግርህ ታደርገዋለህን የልቦናዬን ፈቃድ ትፈጽመሀልን? ይለዋል መሀመድም ካዳንከኝ አዎ ያልከኝን ሁሉ አደርገዋለሁ ብሎ የመልስለታል፡፡
ከዚህ በኋላ ዲያቢሎስ፡
- ዕጸ ጌት የተባለች ጫትን፣
- ዕፀ ኩስራ የተባለችውን ቡናንና
- ዕፀ ስጥራጢስ የተባለጭውን ጥንባሆን
እነዚህን ሶስቱን ዕፅዋት ከአሉበት አምጥቶ መድሀኒት ናቸው ብሎ ይሰጠዋል ፡፡ ይህንንም ቡና ከጠጣህ ፈጥነህ ትድናለህ ለልጅ ልጅ ዘመን በመካ መዲና መስዋዕት አድርገህ ሰዋ ብሎ ቆልቶ ያሰየዋል፡፡
መሐመድም ብረት ምጣድ አግሎ ያሳየዋል እንደመልኬ ከሰል አስመስልህ አጥቁረህ ትቆላለህ ይለዋል እንዳለው አድርጎ ከሰል አስመስሎ ይቆላል ሁል ጊዜም እንደዚሁ ካላከሰልክ መድሀኒት አይሆንህም ይለዋል ራስ ምታቱም ለጊዜው የተወው ይመስለዋል ኋላ ግን ሰዓት እየጠበቀ ይነሳበታል።
በመሓመድ ሥርዓትና ሕግ የሚጓዙ " አወል ፤ ቶና ፤ በረካ " የሚባሉ ሦስት ሰዎች ለንግድ የመጡ መስለው ከአምስት ተከታዬቻቸው ጋር እነዚህን ዕፅዋት ይዘው ይመጣሉ እነዚህም «ጫት፤ ቡና ፤ ጥንባሆ» ናቸው አህዛብ ለሰይጣን የሚያቀርቡዋቸው የጣኦት መስዋዕት ናቸው። የእግዚአብሔር መስዋእት ግን፤
- ስንዴ
- ዘቢብ
- እጣን
ናቸው።
ዓርብ እና ዕሮብ ብዙ ሰዎችን እያዛጋ ከቅዳሴ የሚያስቀረው እኮ ቡና ነው ። በፆም ሰዓት ብዙ ሰዎችን በራስ ምታት የሚቀውር ቡና ነው ። ቡና ካልጠጡ ደስታቸውን የሚያጡ፣ የሚነጫነጩ፣ የሚሳደቡ፣ የሚደብራቸው ቤቱ ይቁጠራቸው ። ቡና ቁጭ ተብሎ የሰው ሥጋ በሓሜት የሚበላበት ወሬ እንቶ ፈንቶ የሚሰለቅበት ነው። ሥራ ፈቶች እስከ 3ኛ የሚያንቃርሩት … ቡና ቤተክርስትያን እስከምታወግዘው መጠበቅ የለብንም። እግዚአብሔር የሰጠንን አእምሮ መጠቀም ብቻ በቂ ነው።
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
Blogger Comment
Facebook Comment