ዘርአዳዊት ዘ-ኢትዮጵያ
በጥንታዊው ክርስትና፣ በጥንታውያን ሕዝቦች እና በኢትዮጵያ የማርያም መቀነት ቀለማት ላይ የሚካሄድ የቀለም አብዮት ።
ቦሊቪያ እንደ ጋና የሉሲፈራውያኑ ኮከብ ያላረፈበትን ቀለማችንን ስለመረጠች ጥንታውያኑ አ'ይ'ማራ ነዋሪዎቿ የኢትዮጵያን ሕዝቦች ስቃይ በመጋራት ላይ ናቸው ።
በጣም የሚያስገርም ዘመን ላይ እንገኛለን ፥ በርግጥ ዓለማችን ትንሽ ሆናለች ።
የኢትዮጵያን ቀለማት የያዙት ቦሊቪያውያን የሉሲፈራውያኑ ተቋም ሲ.አይ.ኤ ያካሄደውን መንፈቅለ መንግሥት በጥብቅ በመቃወም ላይ ይገኛሉ ። ሆን ተብሎ በርዕዮተ ዓለም እንድትከፋፈል የተደረገችው ደቡብ አሜሪካዋ ቦሊቪያ ልክ እንደ ቺሌና ቬኔዝዌላ ታይቶ በማይታወቅ የእርስበርስ ጦርነት ተናውጣለች ። ብዙዎች ተገድለዋል ። ሉሲፈራውያኑም በአጭር ጊዜ ውስጥ እራሳቸው ያስቀመጡትን "አብዮታዊ ዲሚክራሲያዊ"ፕሬዚደንት ኢቮ ሞራሌስን ከስልጣን እንዲወገድና እራሳቸው በመረጧት ሴት እንዲተካም አድርገዋል።
ተመሳሳይ ሁኔታም በአረንጓዴ፣ ቢጫ እና ቀይ ቀለማቱ ባለቤት በሀገረ ኢትዮጵያ በመታየት ላይ ነው።
666ቱ ገዳይ አብዮትም የዚህ መፈንቅለ ሥርዓት ልጅ ነው። የሁለቱ መፈንቅለ ሥርዓታት ዓላማም ሀገራዊ፣ ብሔራዊ፣ ክርስቲያናዊ እና የጥንት የሆነውን ነገር ሁሉ ሙሉ በሙሉ ማስወገድ ነው ። በኢትዮጵያ "ዐምሓራ እና ትግሬ" የተባሉትን ጥንታውያን ኢትዮጵያውያንን ፥ በቦሊቪያ ደግሞ ጥንታዊ የሆነውን የአ'ይ'ማራ ነገድ ከእናት ሀገራቸው ማጥፋት ነው። ልክ መለስ ዜናዊን እና ግራኝ ዐቢይ አሕመድን በኢትዮጵያ እንዳዘጋጇቸው ፥ በቦሊቪያም ከአ'ይ'ማራ ነገድ የሆነውን የቀድሞ ፕሬዚደንትን ኢቮ ሞራሌስን ሤረኛ በሆነ መልክ አዘጋጅተውታል።
በደቡብ አሜሪካዎቹ ቦሊቪያ፣ ቺሌ እና ፔሩ የሚገኙትና "PueblosIndigines / ፑዌብሎስኢንዲኺኔስ" በመባል የሚታወቁት ጥንታውያኑ የሀገሬው ሕዝቦች መጠሪያቸው "አይማራ" ነው ። 11 ሚሊየን ነዋሪዎች ባሏት ቦሊቪያ የአይማራ ሕዝብ ቁጥር 1.5 ሚሊየን ወይም 20% ይጠጋል ። አብዛኛው የቦሊቪያ ነዋሪ ከአውሮፓውያን ጋር የተካለሰ ሲሆን ለረጅም ጊዜ ስልጣኑንም የያዘው እነዚህ "ሜስቲዞስ / ክልሶች" የሚባሉት ናቸው ። ቦሊቪያን እንደ አይማራ ከመሳሰሉት ያገሬው ጥንታውያን ነዋሪዎች ለማጽዳት ዘር ከመከለስ እስከ ምግብና ውሃ መበከል ያልተሞከረ የዘር ማጥፋት ዘመቻ አልነበረም ።
ከአሥር ዓመታት በፊት ሉሲፈራውያኑ የዓለማችን ፈላጭ ቆራጮች ለመጀመሪያ ጊዜ ከዚሁ የአይማራ ነገድ የወጣውን የሀገሪቷን መሪ "ኢቮ ሞራሌስን"ሥልጣን ላይ አወጡት። ምንም እንኳን ኢቮ ሞራሌስ የአይማራ ነገድ ይሁን እንጅ ተጠሪነቱ ግን ለሉሲፈራውያኑ ነው ። የአሜሪካ ተቀናቃኝ እንዲሆን(የሚቆጣጠሩት ተቀናቃኝ / Controlled Opposition) ብሎም የሶሺያሊስታዊ ሥርዓት አራማጅ እንዲሆን አዘዙት ። አሁን ልክ ጊዜው ሲደርስ ከስልጣን አስወገዱት፤ በከፊሉ የቦሊቪያ ሕዝብ ዘንድ ተወዳጅነትንም እንዲያተርፍ ስላደረጉት አሁን እየታየ ያለው ህውከት ሊፈጠር ቻለ።
በሀገራችንም ከዚህ የከፋ ህውከት ከመጪው ግንቦት "ምርጫ" በኋላ ሊፈጠር እንደሚችል ለማወቅ ሊቅ መሆን አይጠበቅብንም ።
ከሃያ ዓመታት በፊት በርትዕት ተዋሕዶ ክርስቲያኗ ሰርቢያ(የቀድሞዋ ዩጎዝላቪያ) የጀመረው የሉሲፈራውያኑ"የቀለም አብዮት" ጥንታውያን የተዋሕዶ ክርስቲያን በሆኑት ሕዝቦች ዘንድ እንዲቀጣጠል ነው እየተደረገ ያለው ። ከኦርቶዶክስ ሰርቢያ ወደ ኦርቶዶክስ ጆርጂያ፣ ዩክሬይን እና ሩሲያ እንዲቀጥል ተደርጓል።
አዎ! የዲያብሎስ ግብ ኢትዮጵያ ነች ። ዲያብሎስ ተዋሕዶ ክርስትናን እና ሰንደቅ ዓላማችን በጣም ይጠላቸዋል፣ ይፈራቸዋል ። ይህን በሀገራችን እያየን አይደለም?! የክርስቶስ ተቃዋሚዋ ቱርክ እንኳን የኩርድ ሕዝብን በመጨፍጨፍ ላይ ያለቸው ኩርዶች የኢትዮጵያን ቀለማት በመያዛቸው ነው ።
የሕዝብን ዘር በማጥፋት የሺህ ዓመታት ልምዱ ያላቸው ቱርኮች እና ዐረቦች ወደ ኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ወደ ቦሊቪያ እና ቬኔዝዌላም ርቀው በመጓዝ እየሠፈሩ ነው ። እነዚህ የመጥፎ ዜና እና ጥፋት መልዕክተኞች ከምዕራባውያኑ ረዳቶቻቸው ጋር በማበር የኢትዮጵያን ክርስቲያኖች ደም አፍስሰው ለዋቄዮ-አላሃቸው እንደሚገብሩት በቦሊቪያም "አ'ይ'ማራ የተሰኘውን ጥንታዊ ሕዝብ ለዚሁ ሰይጣናዊ ተግባር መፈጸሚያ ለማድረግ በመዘጋጀት ላይ ናቸው ።
የሚገርም ነው፤ በሀገራችን ዐምሓራ፤ በቦሊቪያ አ'ይ'ማራ። ሁለቱም በአሁኑ ሰዓት የተዳከሙ ሕዝቦች ናቸው ። ልዩነቱ ግን የኢትዮጵያ አማራ የደከመው ኢትዮጵያዊነቱ ስላልጠነከረ/በኢትዮጵያዊነት ስላልተጠናከረ፣ የአባቶቹን ነፍጠኛነት በመርሳቱ ሲሆን የቦሊቪያዎቹ አ'ይ'ማራዎች ግን በአ'ይ'ማራነታቸው ስላልጠነከሩ/ስላልተጠናከሩ ነው። ከዐምሓራ በፊት ኢትዮጵያ ስትቀድም ከቦሊቪያ በፊት ግን አ'ይ'ማራ ይቀድማል።
በኢትዮጵያ በዐምሓራ ላይ እየተካሄደ ያለው ጥቃት ነዋሪዎቹ "ዐምሓራ" በመሆናቸው ሳይሆን አማርኛ በመናገራቸው፣ ተዋሕዶ ክርስቲያን በመሆናቸው፣ አረንጓዴ፣ ቢጫና ቀይ ሰንደቅ ዓላማ በማውለብለባቸው፤ ባጠቃላይ ኢትዮጵያዊ በመሆናቸው ነው ። "ትግሬ" የሚባለውም በትግሬነቱ ሳይሆን ጥቃት የሚፈጸምበት በጥንታዊው ኢትዮጵያዊነቱ እንጂ ። እነዚህ ኢትዮጵያውያን ከዚህ ኢትዮጵያዊነታቸው እስካልተላቀቁ ድረስ ጥቃቱ ይቀጥላል። ስለዚህ በተቻለ መጠን ዐምሓራነት ኢትዮጵያዊ ባልሆነ ዐምሓራነት፣ ትግሬነት ኢትዮጵያዊ ባልሆነ ትግሬነት እንዲቀየሩና እንዲዳብሩ ይደረጋሉ ። ትናንትና ኤርትራ ዛሬ ደግሞ ትግራይ እና ኦሮሞ በተባሉት የኢትዮጵያ ክፍለሀገራት የተደረገው ነገር ይህ ነው ።
"አብን" የተባለው ፓርቲ ገና ሲቋቋም "ኡ! ኡ!ዋይ! ዋይ!" ብዬ ነበር ። በዘውግ የተደራጀ "ዐምሓራ" የተሰኘው ሕዝብ በአማራነት ከኢትዮጵያ የሚነጥል ሤር መጠንሰሱን ከውዲሁ ይታየኝ ነበር ። የደከመው ዐምሓራ ላይ ቶሎ ጥቃት የፈጸሙት፣"መሪዎች" የሚሏቸውን ልሂቃን የገደሉትን እና የአብን አመራራትን ወደ እስር ቤት የከተቱት ዐምሓራ የሚሉት ነዋሪ ተቆጭቶና ተነሳስቶ ኢትዮጵያዊነቱን እንዲተውና ኢትዮጵያን የከዳ የዐምሓራ ሀገር እንዲገነባ ነው።
"አብን" የተሰኘው ፓርቲ ሰሞኑን ከኢትዮጵያ ቀንደኛ ጠላት ከሆኑ ኦነጎች ጋር በአንድ ጠረጴዛ ዙሪያ መቀመጡ ይህን የፀረ-ኢትዮጵያ የሆነ አካሄድ ነው የሚጠቁመን ። ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ፓርቲዎች ሁሉም በፀረ-ኢትዮጵያ ኃይሎች የተደራጁና በጠላቶቻችን ባትሪ የሚሞሉ ሀገር አጥፊዎች ናቸው ። አሁን በአብን እና በኦነጎች መካከል የተፈጠረው ግኑኝነት ከሰላሳ ዓመታት በፊት በህዋሃት እና ኦነግ መካከል ተካሂዶ የነበረውን ጋብቻ ያስታውሰኛል ። ያኔም የጥፋት ኦርኬስትራውን ሲመሩ የነበሩት ምዕራባውያኑ ሉሲፈራውያን ነበሩ ፥ ዛሬም እየመሩ ያሉት እነርሱው ናቸው።
"በሠላሳ ዓመት ውስጥ ኦሮሞው እና ትግሬው ከኢትዮጵያዊነት እንዲርቅ ተደርጓል ፥ በመጭዎቹ ሰላሳ ዓመታት ደግሞ አማራው ኢትዮጵያዊነቱን እርግፍ አድርጎ እንዲተው ይደረጋል፤ ያኔ ኢትዮጵያ የምትባል ሀገር እትኖርም፣ ተዋሕዶ ትጠፋለች፣ አረንጓዴ፣ ቢጫ እና ቀይ ቀለማቱም ወደ ጥቁርነት ይቀየራሉ" የሚል ነው እቅዳቸው። ግን ብዙ መስዋዕት ያስከፍለናል እንጂ ይህ እቅዳቸው አይሳካላቸውም።
ስቃዩና ዕልቂቱ እንዲቀነሱ ግን ባፋጣኝ "ዐምሓራ"እና "ትግሬ" የተባሉት ነገዶች ልሂቃናቶቻቸው ለዘመናት ለፈጸሙባቸው በደሎች ብድር ከመመላለስ በመቆጠብና እርስበርስ ይቅር በመባባል ባፋጣኝ መተባበር ይኖርባቸዋል ። ይህ በዐምሓሮችና ትግሬዎች ላይ የመጣ የህልውና ጉዳይ ብቻ ሳይሆን፤ ከምጽዋ እስከ ሞያሌ ያሉትን ሌሎቹን "ደካማ"ኢትዮጵያውያን ነገዶችን አንስፍስፎ ከመጣው የዋቂዮ-አላህ ሠራዊት መከላከል ብሎም ኦሮምኛ ተናጋሪ ኢትዮጵያውያንን ከዚህ አውሬ ኃይል ማዳን መቻል ስለሚኖርባቸው ነው።
በሀገራችን፣ በቤተክርስቲያናችን እና በሰንደቅ ዓላማችን ቀለማት ላይ የተነሱትን የዲያብሎስ ቡችሎች ቅዱስ ሚካኤል በሰይፉ ቆራርጦ ይጣላቸው ።
Blogger Comment
Facebook Comment