ዘርአዳዊት ዘ-ኢትዮጵያ
‹‹መልካሙን ገድል ተጋድያለሁ፤ ሩጫዬን ጨርሻለሁ፤ ሃይማኖቴንም ጠብቄያለሁ፤ ወደ ፊት የጽድቅ አክሊል ተዘጋጅቶልኛል፤ ይህም ጻድቅ ፈራጅ የሆነው ጌታ ያን ቀን ለእኔ ያስረክባል፤ ደግሞም መገለጡን ለሚወዱ ሁሉ እንጂ ለእኔ ብቻ አይደለም፡፡››
--- ( 2ኛ ጢሞ 4፥7-8)
አባ ዘወንጌል ዐርፈዋል! ተለይተውናል! ያየነውን እንመሰክራለን-አባ ዘወንጌል ባሉበት ገዳም ዙሪያውን ከሰማይ የብርሃን ዓምድ ሲያርፍበት በአካል ተገኝተን በዐይናችን አይተናል። በካሜራችንም ቀርጸነዋል። አባ ዘወንጌልን ስውራን ቅዱሳን እየመጡ ይጎበኟቸው እንደነበርም እዛው እያለን ተነግሮናል። እሳቸውም አንዳንድ ጊዜ በሰንበት ቀን እየተሰወሩ ይጠፉና እንደገና በአዘቦት ቀን ተመልሰው መጥተው በአካል ከቦታቸው ላይ ይገኛሉ። አባ ዘወንጌል ከሳልሣዊው ቴዎድሮስ ጋር የሚገናኝ ትልቅ ታሪክ ያለውን የመስቀለ ክርስቶስን ገዳም ሕንፃ አሠርተው ከጨረሱ በኃላ እንደሚያርፉ የተናገሩት ነገር ይኸው ተፈጸመ፣ እርሳቸው ትናንት በሥጋ ዐረፉ።
"ኢትዮጵያን በዚህ ወቅት እያስተዳደሯት ያሉት ጠላቶቿ ናቸው" የምንለው ዛሬ ላይ የኢትዮጵያ ስምና ፊደል ከመኪና ላይ ስለተፋቀ አይደለም። በፌዴራል ፖሊሱ አማካኝነት መንግሥትም በመንግሥትነቱ ባንዲራዋን መሬት ላይ ከቆሻሻ ላይ እየጣለ ሲረግጥና ሲያስረግጥ ኢትዮጵያን በአደባባይ ሲያዋርድ ካየነው ገና ወር አልሞላውምኮ! በ7 ቀን ልዩነት የተከበሩት የመስቀል በዓልና የኢሬቻ በዓል ሁሉንም ነገር ግልጽ አድርገውት አልፈዋልኮ።
በ7 ቀናት ልዩነት ውስጥ ፌዴራል ፖሊስ ኢትዮጵያን በአደባባይ አዋርዶ በተቃራኒው ደግሞ ኦነግን አንግሦ በተግባር አሳይቶናል አይደል እንዴ!? እና ዛሬ ምን የተለየ ነገር ተገኝቶ ነው የኢትዮጵያ ስምና ፊደል ከመኪና ላይ ስለተፋቀ የምንደነቀው???
ወዳጄ ወደድክም ጠላህም፣ አመንክበትም አላመንክበትም ለመጨረሻ ጊዜ አንድ ነገር ደግሜ ልንገርህ-በዚህ ወቅት ሥልጣን ላይ ያሉትም ሆኑ ከእነርሱ በፊት የነበሩት ሁሉም የኢትዮጵያና የኦርቶዶክስ ጠላቶች ናቸው። በዲዮቅልጥያኖስ ላይ አድሮ የነበረ ሰይጣን ዛሬ ላይ ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ እዚሁ ዙፋን ላይ ተቀምጦ ሥራውን እየሠራ እንደሆነ ደጋግሜ ጽፌልሃለሁ። ቅድስት ኢትዮጵያን ላለፉት 40 ዓመታት የገዟትና አሁንም እየገዟት ያሉት የኦርቶዶክስም የኢትዮጵያም ጠላቶች ናቸው። ይህ ዛሬ ላይ ካልገባህ ወደፊት ወደፊት ኢትዮጵያዊነትና ተዋሕዶ ሲጠፉ ስታይ ያኔ ይገባሃል። ዛሬ ላይ መርዝ በተሞላ አፉ "ተደመር" እያለ በሥራው ደግሞ ኢትዮጵያዊነትና ተዋሕዶነትን እየቀነሰና እያጠፋ መጨረሻ ላይ በአሕዛብ ሰይፍና በምንፍቅና ሲያስበላህ ያኔ ይገባሃል።
እውነተኛ ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን በተለይም ኦርቶዶክሳውያን ወገኖቼ ወደፊት ማድረግ የሚገባንን ተደራጅተን እንምከር! ስለ ኢትዮጵያና ስለ ተዋሕዶ ሃይማኖታችን እናልቅስ፣ እንጸልይ፣ እንጹም!!! እውነተኞቹ የጸሎት አባቶቾ እንደነ አባ ዘወንጌል ያሉት ደጋግ ባለጸጋ አባቶቻችንም ሞተ ዕረፍታቸውን እየለመኑ ወደ ፈጣሪያቸው መሄዳቸውን ስናስብ ስለነገው ጭንቀታችን ጨምሯል።
አባ ዘወንጌልን እግዚአብሔር ፈቅዶልን ከ2 ዓመት በፊት በአካል አግኝተናቸው ባርከውናል። እኛም በዐይናችን እንዳየነው ብርሃን ከሰማይ የሚወርድበትንና ከሳልሣዊው ቴዎድሮስ ጋር የሚገናኝ ትልቅ ታሪክ ያለውን የመስቀለ ክርስቶስን ገዳም ሕንፃ አሠርተው ከጨረሱ በኃላ እንደሚያርፉ ይናገሩ ነበር። ያው ያሉት ደርሶ የማዕቢኖ መስቀለ ክርስቶስ ገዳም በመስከረም 18,ቀን 2012 ዓ.ም ተመርቋል። መስከረም 18/1/7512 የመከራው ዘመን የጭንቁ ጊዜ የረሀብና የቸነፈሩ ወቅት መጀመሪያ ነው። ከዚህ ቀን ጀምሮ ለ3 ዓመት ችግሩ ይጸናል። ከዚያ በኃላ ነው ሳልሣዊ ቴዎድሮስ የሚነግሠውና የኢትዮጵያ ትንሣኤ የሚመጣው።
አባ ዘ ዘወንጌል ብዙ ታላቅ ምሥጢር የተቸራቸው ደገኛ አባት ሲሆኑ የኢትዮጵያን ትንሣኤ ያዉጃሉ ተብለው የሚጠበቁ ነበሩ። ብዙ ትንቢታዊ ትምህርት ያስተማሩና በርካታ ድንቅ ድንቅ ተአምራትን ሠርተዋል። አሁን ግን የቅድስት ሀገር ኢትዮጵያንና የኦ ተዋሕዶን ጥፋትና መከራ ሳያዩ አምላክ አሳርፏቸዋል።
እሳቸው ያሉበት ገዳም ዙሪያውን ከሰማይ የብርሃን ዓምድ ሲያርፍበት በአካል ተገኝተን በዐይናችን አይተናል። በካሜራችንም ቀርጸነዋል። አባ ዘወንጌልን ስውራን ቅዱሳን እየመጡ ይጎበኟቸው እንደነበርም እዛው እያለን ተነግሮናል። እሳቸውም አንዳንድ ጊዜ በሰንበት ቀን እየተሰወሩ ይጠፉና እንደገና በአዘቦት ቀን ተመልሰው መጥተው በአካል ከቦታቸው ላይ ይገኛሉ። ብርሃናዊውን ግራ እጃቸውን ማንም ሰው አይቶት አያውቅም። እግዚአብሔር ኃይሉን በግራ እጃቸው መዳፍ አትሞ እንዳስቀመጠና ግራ እጃቸው ላይ ያለው ብርሃን እንዳይታወቅባቸው በጨርቅ ከጠቀለሉት ዓመታት ተቆጥረዋል። በሰው ውስጥ የተሰወረውን ኃጥአት ጭምር የማወቅ ጸጋ ስላላቸው ያለ ንስሓ እርሳቸው ጋር መቅረብ አይቻልም ነበር።
ስለ ዕድሜያቸው ጉዳይ (600 ነው፣ 300 ነው፣ 200 ነው...) እየተባለ ብዙ የተለያዩ ሀሳቦች ቢሰጡም "ዕድሜያቸው አይታወቅም" የሚለው ለእኔ ሚዛን ይደፋብኛል። እርሳቸውም ዕድሜያቸውን ተናግረው አያውቁም። የቅዱሳን ገድላቸው የሚነገረው በሕይወት እያሉ ሳይሆን ካረፉ በኃላ ነውና ይኸው ዛሬ ለመመስከር በቃን።
አባ ዘወንጌል ከሳልሣዊው ቴዎድሮስ ጋር የሚገናኝ ትልቅ ታሪክ ያለውን የመስቀለ ክርስቶስን ገዳም ሕንፃ አሠርተው ከጨረሱ በኃላ እንደሚያርፉ የተናገሩት ነገር ይኸው ተፈጽሟል። ቤተመቅደሱ ተመረ እርሳቸውም ዐረፉ። እርሳቸው እንዳሉት ከዚህ በኃላ የኢትዮጵያ የትንሣኤ ምጧ ይጀምራል ዛሬ የጀመረዉ የቅድስት ኢትዮጵያ የጭንቅ ምጥ ከሦስት ዓመት በኋላ ያልፋል።
የተዋህዶ ልጆች እኅት ወንድሞቼ ሆይ! ደግሜ ላስታውሳችሁ-ንስሓ እንግባ! ስለ ኢትዮጵያና ስለ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖታችን እናልቅስ፣ እንጸልይ፣ እንጹም!!! ለብዙ ነገር መሥዋዕት ለመሆን እንዘጋጅ። የአረቦች ሰይፍ የአውሮፓውያን ባሩድ ከኢትዮጵያውያን ደም ጋር ይዋሐዳል። ይህ ክፉ መንፈስ በየቤታችን ይገባና የምንወዳቸው ሰዎችን ሳይቀር ይወስድብናል።
ጆሮ ያለው መስማትን ይስማ!
Blogger Comment
Facebook Comment