መልዕክት ለ ትግራይ ምድር ነዋሪዎች





በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ፤ከቃሉ አንዲቷም ፈፅሞ በማትታበል በአንድ አምላክ ስም

አምላክ ሁሉን ህዝብ ሲያይ በእኩል አይን ነው። ራሳችንን በወገንተኝነት፣ በጎጥ፣ በሀብት፣ በምን በምን ብንከፋፍል እዚሁ ለኛው ይሆናል እንጂ፣ የእግዚአብሄርን አይን ልንጋርደው ወይም ተፅእኖ ልናሳድርበት ፈፅሞ አይቻለንም።

በሚመጣው ሁሉ በእግዚአብሄር ፍርድ የሚቀሰፈውም ሆነ የሚድነው እያንዳንዱ ግለሰብ የሚመዘነው ዘመን በማይለውጠው በነበረው በሚኖረው አምላካዊ ሚዛኑ ነው እንጂ የኛ የቡድን ወይ የዘር መለያ ወይ ጎራ በሱ አይን ፊት እንደሌለ ነው የሚሆነው። አንዴ በሱ ፊት ተመዝነን ከወደቅንና ለቅጣት ከተወሰነብን ምን አለም ቢሰለፍ፣ ምን ተአምር ቢሰራ የሚያድነን ከቶ ሊኖር አይችልም፤ ደግሞ በዛው መጠን በሱ ፊት አንዴ ተመዝነን ከተመረጥን ምን እሳት ቢዘንብ፣ የእልቂት መአበል መሀል ብንገባ ከቶ የሚነካን ሊኖር አይችልም።

ዛሬ ትግራይ ተብሎ በተከለለው ክፍል የሚኖሩ ጥንት ኢትዮጵያውያን፣ ለዘመናት ፀንተው ሳይናወፁ፣ ኢትዮጵያዊነት ከነሙሉ መገለጫውና በሙሉ መልኩ የተላበሱት፣ እግዚአብሄር በሚወደው የዋህነትና ፍቅር በእምነት ልጆቹ ሆነው የሚኖሩ፣ እሱም ለክፉ ጠላት አሳልፎ ሊሰጣቸው የማይፈቅድ ለኢትዮጵያዊነት መሰረትና ምሶሶ ከሆኑት ውስጥ ዋነኞቹ ናቸው።

ከጥንት ኢትዮጵያ ልጆች ጋር “እንዲህ ያለ ኑሮ እንኑር” ብለው የሆነ ማንነት ለመያዝ አቅደው የኖሩ ሳይሆን፣ በእምነት ከፈጣሪያቸው ተዋህደው በስሩ በፍቅርና እውነተኛ እምነት የኖሩበት ባህልና አኗኗራቸው ኢትዮጵያዊነት የሚል ስም የተሰጠላቸውና እስከዛሬም በሙሉ መልኩ ልንላበሰው የምንመኘውን ማንነት የሰጡን ህዝቦች መሀል ዋነኞቹ ናቸው።

ይህንን ማንነታቸውንም ተላብሰው ሳሉ ምንም ጠላት ቢነሳባቸው አምላካቸውም አሳልፎ ላይሰጣቸው፣ እነሱም ከቶ ላይወድቁ መሆናቸውን ከኛ በላይ የተረዱት የውጪ ጠላቶችና መንፈሳዊ አለሙን መኖር ክደውለት በስውር ሚመራቸው ዲያቢሎስ ቀድመው ይህንን ሀይላችንን አውልቀው ራቁታችንን የሚያስቀሩበትን መንገድ ሲፈልጉ ቆይተዋል። ያም ውጊያቸው ብዙ ትውልድ እየተሻገረ እጅግ የበዛ ዋጋ አስከፍሎናል።

በዚህም አላማቸው መሰረት በእምነቱ ፀንቶ ኢትዮጵያዊነቱን ጠብቆ የኖረው የትግራይ ምድር ኢትዮጵያዊ ቀድሞ ኢላማ ውስጥ ገብቶ ከባድ ዋጋን ከፍሏል። ባልታሰበ መንገድ ከሱ ጋር ፈፅሞ ሊሄድ የማይችል እግዚአብሄርን በጠላ መጤ ርዕዮት እንዲመረዝ ተደርጎ፣ ባላሰበው መልኩ ድንገት ከራሱ መሀል ነፃ አውጪ በሚል ስም በውጭ መንግስታት እርዳታና ስለላ መንገድ ጠረጋ በስውር በእጅጉ የሚደገፍ የነበረ ታጣቂ ቡድን ዘረኝነትና ጥቅመኝነት ክፉኛ ያወረው ማህበር ከመሀሉ ወጥቶ፣ ልክ ዛሬ በየቦታው እንደሚታዩት ዘረኛ ቡድኖች እንደተለመደው ብሶትን በመቀስቀስና ተጎጅነትን በመስበክ ቀላል ስነልቦናዊ መንገድ ፈጣን ተከታይና ወዳጅ አፍርቶ በዛ መልካም ህዝብ ላይ ነግሶና ሰልጥኖበት እስከዛሬ እየኖረ ይገኛል። ህዝቡንም ወይ ከአምላኩ፣ ወይ ከኑሮ ደረጃውና ሀብት፣ ወይ ከሀገሩ እንዳይሆን አድርጎ በአየርላይ ተንሳፎ ያቺ ምድር ሌላ ሰው የሌላት ይመስል በባዶ እኔነኝ መድሀኒታችሁ እያለ ነግሶበት ይገኛል።

ይህም ሳይሆን ጉዳቱ፣ ዋናው ነገሩ ከዛ ምድር ነዋሪ የክፍለዘመናት ታሪክ ፈፅሞ ውጪ በሆነ መልኩ ከአምላኩ የተለየ፣ በመሪነት ራሳቸውን ያነገሱበት ሰወች የሚያደርጉት እንቅስቃሴ ስብከትና ምኞት፣ የሚዘረጉት ርዕዮትና አስተምህሮ፣ ባህል፣ እንዲሁም ተግባር ሁሉ ተተኪው ትውልድ ከልጅነቱ ጀምሮ ሰፊ፨ሙሉ ጊዜውን ውሎውና አስተዳደጉ ከክቡራን ከአባቶቹ ይልቅ በሚገባባቸው የትምህርት ተቋማትና ሚዲያዎች አማካኝነት በማሳለፉ አዲስ እንደተመሰረተ ምድር ልጆች ኢአማኒነትን የተሰበከ፣ ካባቶቹ አምላኩን ያላወቀ፣ ያባቶቹን ሳይሆን በሌላ አዲስ ማንነት የተላበሰ፣ ስነልቦናው በክርስቶስ መቅረቢያ ፍቅርና አንድነት የተሰበከ ሳይሆን ዘር ለይቶ ፉክክርና ወገንተኝነት፣ ከሌሎች ክርስትያን ወንድሞች ጋር በጠላትነት የሚያስተያይ በሆነ መልኩ የተቀረፀ፣ የህይወት ምኞቱና ግቡም አባቶቹ ከምንም በላይ አክብረውና ዋጋ ሰጥተው ባቆዩለት ፀንተው ቢኖሩባቸው እንቁ የሆኑ የአምላክ ቃልኪዳኖች የተላበሰችዋን የቃልኪዳን ምድር ሳይሆን በግንጠላና ምድራዊ ምኞት ላይ የፀናች ሲንጋፖርነትን በቁሙ የሚቃዥ፣ መዳረሻው ከአምላኩ የራቀ የሆነ እንግዳ ትውልድ እንዲፈራ ሆኗል። ከመሀል ሻል ብሎ አምላክን የሚጠራው ቢኖር እንኳን ጠዋት ማታ በሚሰበከው ዘረኝነት ተመርዞ የክርስቶስ በመሀል መገኛ መልክ የሆነው ፍቅርን አጥፍቶ አምላኩ ከመሀሉ ፈፅሞ ሊገኝ እንዳይቻለው እንደዘረኝነትና ጥላቻ አፀያፊ ነገርን እንዲላበስ ይተጋሉ።

ይህም ተፅእኖ በገጠሩ ውስጥ በሚኖሩ የዋሀን እንዲሁም ደግሞ እድሜያቸው ትልልቅ በሆኑት አማኝና ኢትዮጵያዊ አባቶችና እናቶች ላይ የደረሰ ሳይሆን፣ ከልጅነቱ ጀምሮ በህፃን አእምሮ በዚህ መልኩ ሲመረዝ ያደገ አሁን በወጣትነትና ከዛ በታች ባሉት፣ እግዚአብሄርን በማያውቁት ላይ ግን በተወሰነ መልኩ ተፅእኖው ያይላል።

በዚህም መልኩ ለዘመናት ያኖረውን ትጥቁን አምላኩን ጥሎ፣ ብረትና ባሩድን በማስጨበጥ፣ በየትኛውም ዘርፍ ለሚመጣ ጠላት ሁሉ ራቁቱን እንዲቆም ሊያደርጉት ጠላቶች ብዙ እየለፉ ኖረዋል።

የፈጣሪን መኖር ፈፅሞ ካልካዱ በስተቀረ፤ ያ ሀያል ፈጣሪ መኖሩ እየታወቀ፣ ፈጣሪ በሰራው አለም ላይ ሆኖ ያለ ሀያሉ እርሱ አካልነት ማቀድና ያለ እሱ መነፅርነት ነገሮችን ማየት ምን ያህል የበታችነትና ውድቀት መሆኑ ላንተም የሚጠፋህ አይመስለኝም። ምን ጠላት ቢነሳ፣ ምን ክፉ ቀን ቢመጣ እግዚአብሄር አብሮ ካለ ሌላው ጠላጥ ምን ቢል፣ ምን ቢለፋ፣ ከቶ ምን ዋጋ ሊኖረው፧

አንተም አምላክህን ከሁሉ ይልቅ አስቀድመህ መያዥን አትዘንጋ፣ የመጀመርያ ሀሳብህም፣ ቅድሚያ የምታየውም የመጀመርያ መተማመኛህ እሱ ይሁን።

ፈፅመህ ዘር የቆጠረ፣ የሰውልጆችን በማይቀይሩት ማንነታቸው ካንተ የሚለይ ክፉ አደረጃጀትን በማንውኛም መንገድ አትቅረበው፣ ከልጆጭ አእምሮም ፈጥነህ አፅዳ። ከሌሎች ድሀ ኢትዮጵያውያን ጋር በአንድነት የአምላክህ ልጅ የምትሆንበትን፣ አምላክ ከመሀልህ የሚገኝበትን የአንድነት መንገድን ብቻ የምትከተል ሁን። በየትኛውም የመቃቋም ማህበርህም ሆነ ድርጅጥ ዘርን ቆጣሪ ሳይሆን የሰው ልጅን በቀና አስተሳሰቡ ብቻ አቃፊ ሁን፣ ድልም የሚከተልህ ያ ሲሆን ብቻ ነው። እውነት ግን ፃድቁ አቡነተክለሀይማኖትን ወይ ክርስቶስ ሰምራ እንኳን እንደው ሊቀላቀሉህ ቢመጡ አሻፈረኝ ልትላቸው ድረስ የሚነግርህን የዘር አደረጃጀትን ይዘህ ልትረክስ ቀላል ሆነልህ፧ ለመሆኑ ክርስቶሽ ቢመጣ የየትኛው ዘር ብለህ ልታስጠጋው ኖሯል፧ ትመልሰዋለህንጂ። እንዲህ ባለ ፍፁም እብደት መሆንንስ በየትኛውም መንገድ አርቀው፣ እኩይ ድንበሮችን አልፈህ በህብረት ከሌሎች የእግዚአብሄር ልጆች ጋር መዋሀድን ምርጫህ አድርገው። ከዛ ውጪ የሚመራህ ለፍፁም ጥፋጥና ለሞጥ ካልሆነ የትም መዳረሻ ሊኖረው በተፈጥሮው አይቻለውምና።

ከፊታችን የሚጠብቀን መከራና መቅሰፍት ሁሉ ድንገት የመጡና በኛ ባሰብናቸው መሹለክለኮች ልንወጣቸው የምንችላቸው ያጋጣሚ ክስተቶች ሳይሆኑ ከዘመናት በፊት ቀድመው የታወቁ፣ ክፉኛ የሰፋ እልቂታቸውና ውጤታቸው የተፃፉ፣ ከኛ ይልቅ በአባቶጭ ከነዛሬ ሁኔታችን በድነብ የታወቁና ለሁላችንም ልጆቻቸው እንድንባቸው ዘንድ የተፃፉልን፣ ካለአምላካችን ፈቃድ ማንኛችንም ቢሆን በእጅስራችንና መፍጨርጨራችን አንዳችንም ልንሻገራቸው የማንችላቸው በመሆናቸው ነው።

እጅግ አስከፊ የሚያደርገውም፣ ከእውነተኛው የዘመናት ተግባሮቻችን በተቃራኒ መንፈሳዊ አይናችንን ከድነንና ዘግተን የምናደርጋቸው የለተለት መፍጨርጨሮች እያባሱብን፣ ከግርፋታችን ቀድመው ይበልጥ አምላካችንን አርቀው ራቁታችንን እያስቀሩን በመሆናቸው አንተም ከዚህ ራቅ።

አምላክህን ያዝ እንጂ፣ እሱ በመሀልህ እንዲገኝ ዘር መልክ ሳትለይ ፍቅርን አንግሰህ በየዋህነት ፈጣሪህ በመሀልህ እንዲገኝ ጋብዘው እንጂ፣ አምላክ አንተን ሊያጠፋ የመጣብህ ጠላት ዘሩ፣ ቀለሙ፣ ምድሩ ለሱ አይታየውም። የሰይጣን መንፈስ ግብር ይዞ የተነሳብህ ጠላጥ ካንተም መሀል ይሁን ከሌላው እኩል አንድላይ ከስሞ፣ ይጠፋል።

ራሽን ከሌላው ኢትዮጵያዊ ሳትለይ ፍቅርና ክርስቶስ ብቻ የጋራ ማእከልህ ሊሆን ከሚችለው ከየትኛውም ጋር በአንድነት ቁም። በታሪክህ አሳፍሮህ የማያውቅ፣ እውነተኛው ትጥቅ የሆነውን እግዚአብሄር በመሀልህ እንዲገኝ ትጋ፣ ንብ በአበባ መአዛ እንዲገኝ ክርስቶስም እምነትና ጥንት ተላብሰኸው የኖርከው የዋህ ወንድማዊ ፍቅር ባለበት ነውና የሚገኘው ያንን ተላብሰህ በመሀልህ ጋብዘው።


ከዘረኛ በላይ ክፉና እጅግ ወንድሙን የሚጠላ የዲያቢሎስ ፈረስ የለም። ዘረኛ በነገሰበት በትኝውም የሀገራችንም ሆነ የአለም ስፍራ ፍቅር ሰላም ተዋህዶ እምነት ምልክታቸውም አይኖሩም። ይህ የሚታየው ሀቅ ነው።



ከየትኛውም ዘር ብትሆን፣ ምንም ምክንያትም ብትሰጠው ይህንን የተላበስከው ዕለት የደነበረ ፈረስ ላይ የታሰረን ገመድ በአንገጥ ፈቅደህ እንዳስገባኸው እወቀው። የእግዚአብሄርም ቁጣ ዘራቸውን ሳይጠይቅ ዘረኞችን ሁሉ ይመታል።

ጠላጥ ይሄ ነው የሚሉህን ፈፅመህ አጽማቸው። ደግፈህ አትሰለፍላቸው። በእግዚአብሄር መንገድ ብቻ ሆነህ ቁም፣ ከየትኛውም ቢሆን የዲያቢሎስ ፈረስ አንተን ጠላት አድርጎህ ቢነሳብህ ግን ከዚህ ፀድተህ አምላክህን እስከያዝከው ድረስ ፈጣሪ አምላክ ፍፁም ድልን ያለብስሀል።

አዲስ ማንነት፣ አዲስ ሀገር ቅዠት ውስጥ ገብተው ሊማግዱህ የሚርመሰመሱትን በሙሉ ለአምላክ ስጣቸው። እውነት ሊቀየር አይችልምና።

የትግራይ ምድር ነዋሪ ሁሉ ከኢትዮጵያዊነት ከፍያለም ከኢትዮጵያዊነት ዝቅም ያለ ማንነት አልነበረውም፣ የለውም።

ቆይ ግን ለመሆኑ፣ ማንነት ማለት ራሱ ምን ማለት ነው፧ እንዲሁ እንደፈለጉ በየጊዜው የሚቀያየር ነገር ነውንዴ፧ ትላንት የነበርከው ዛሬም የሆንከው ነገም የምትሆነው ፅኑ አንተነጥ ነውንጂ፧ ካልሆነማ እንዴት ነው ራሱ ማንነት የሚሆነው፧

የትግራይ ምድር ነዋሪ ከኢዛና ከ ሳይዛና ቡሀላም ከአብርሀ ወ አፅብሀ፣ የተለየ ማንነት አለውን፧ ከቅዱስ ያሬድ የተለየ ማንነት አለውን፧ ከ አቡነ አረጋዊ የተለየ ማንነት አለውን፧ ማንስ ተነስቶ ይህንን አጥፍቶ አዲስ ሌላ የሚያለብሰው፧ እንደው ከነዚህ የከበረ ማንነጽ እንዴት ብሎ ይሆን ሊሰጣቸው የሚሰብከው፧

ከነዚህና ሌሎችም ታላላቅ የምድራችን ምሶሶዎች የራቀ ማንነት የለውም።

ይህንንም ስለሚያውቁት ይመስላል በአዲሱ ትውልድ ያልበሰለ ልቦና ላይ ያተኮሩት፣ ለአማኙም ህዝብ መደለያ ብለው ብለው የፈጠሩት፣ ለራሳቸው የማያምኑበትን እምነት እንደ ፕሮፓጋንዳ ለመጠቀም፣ ዕትግራይ ናት ኢትዮጵያ የምትባለው፣ ይህቺ ምድር ናት ባለቃልኪዳኗ።።።፣ ተገንጥለን እኛ ነን ባለተስፋዋ ምድር።።።ዕ የሚል በእሳት የመጫወት አይነት ክፉ መንገድን ከመጓዝ ወደኋላ አላሉም። የዚህ አይነት እምነት የጎደለው የክፋት ዘመቻ አራማጆችን ሞታቸው ከደጃቸው ፊት ስለቆመ ለነሱ ጆሮ ቢሰጧቸውም አይጠቀሙም። ጣራቸው ቢበዛ እንጂ እነዛ ሁሉ የኢትዮጵያ ቅዱሳን ያፈለቀችን ምድር ሳያካትቱ ቆርጠው ምን አይነት ኢትዮጵያ ይሆን ሊፈጥሩ የሚናገሩት፧ የኢትዮጵያ ምድር የተባረከችው በቅዱስ ዑራኤል አይደለምን፧ ክርስቶስ በስደት ጊዜ ድንግል ማርያምን ርስት ሀገርሽ ብሎ አዙሮ ያሳያት ምድር አይደለችምንዴ ኢትዮጵያ ማለት፧ ቅዱስ ዑራኤል ይህ ምድር የቅዱሳን መፍለቂያ ይሆናል ብሎ ትንቢት የተናገረባቸው ቦታዎች ካልያዘች ምኗ ነው ኢትዮጵያ፧ ቅድስት ማርያም በመከራ በስደት ጊዜ ያረፈችባቸው፣ የአስራት ቦታዎቿን ያልያዘች ስለየትኛዋ የቃልኪዳኗ ኢትዮጵያ ይሆን የሚያወሩት፧ ተክለሀይማኖት በየአቅጣጫው ዞረው ማስተማራቸው ምን ይሆን ትርጉሙ፧ በደቡብ ከወላይታ ባሻገር ሩቅ አልፈው የሰበኩባቸው ቦታዎችን ያልያዘች ኢትዮጵያ የትኛዋ ነች፧ አክሱም ፅዮንን፣ ደብረሊባኖስን፣ ላሊበላን፣ ዋልድባን ያልያዘች አንድ ኢትዮጵያ ስለየትኛዋ ኢትዮጵያ ነው የሚያወሩት፧

አብርሀ አፅብሀ በሀገሬ እምነት ላቅና ብለው ቢነሱ በገዛ ምድራቸው በጎዣም መርጡለማርያምን አላቆሙም፧ ኦሪትን ከሀዲስ አስማምተው፣ እንደንጉስ ሶሎሞን እንደዳዊት አምላክ በህልምና ራእይ እየተገለጠላቸው በሀገራቸው እየተዟዟሩ የእግዚአብሄርን መቅደስ፣ ገዳማቱን አልመሰረቱም፧ እነሱ ሀገሬ ብለው የለፉበትን ምድር ርስታቸውን ለማን ትተኸው ነው አንተ ሌላ ማንነትን የምትላበሰው፧ ያባቶጭን ምድር የሚጠየፍና ሌላ የሚል በአዲስ ማንነት ሰፍቶ ሸሽቶ ጠባብ ቅፅር ይዞ ሊያጠብህ የሚኮላተፍ ክፉ ዘረኛ የደከመ መንፈስ እንዴት ልትቀበለው ይቻልሀል፧



ሁሉ በፍቅር ተቀብለውት በኢትዮጵያ ምድር ከአፅናፍ እስከአፅናፍ ዜማው እንደጊጊዮን ዥረት ዘመን ሳይሽረው የሚፈሰው የአክሱሙ ጥኡመ ዜማ ቅዱስ ያሬድ ማንነት አይደለምንዴ ያንተ እውነተኛ ማንነት፧ የአክሱሙን ንጉስ አሰናብቱኝ ብሎ ሙሉ እድሜውን ሊያሳልፍባት፣ ለድጓው መድረሻ በምኞት የመረጥኳት ሀገሬ ብሎ የሄደባት፣ እንዳትከለክለኝ ማልልኝ ብሎ ንጉሱን አስምሎ ጥሎ የሄደባት ርስቱ ጣና አይደለችምንዴ፧ ከሱ የተለየ ምን ማንነት ይዘህ ይህችን ምድር የኔ አይደለችም ልትላት ይቻልሀል፧

በመላው ምድሯ በኢትዮጵያዊነትና በእምነት ከሚኖሩ፣ ያባቶቻችን ልጆች ሆነው ባንድነት ክርስቶስን የሚያፈቅሩ እንቁ ወንድሞጭ ጋር በምንህ ትለያለህ፧ ከመሀልህ ተነስቶ በስምህ ተንኩሶ አሁንም ጠላት አድርጎ የሚስልብህን ቡድን ተሻግረህ በማህበር ከክርስቶስ ወንድሞጭ ጋር በአንድነት ቁም። በአንድነት ከሚመጣው ከፋትና ጥፋት እንዲሁም መከራ ሁሉ ያድንህ ዘንድ በመሀልም ይገኝ ዘንድ በፍቅር ሆነህ በአንድነት በፀሎት ተግተህ አምላክን ተማፀን።

በትግል በወደቁ የትግራይ ምድር ታጋዮች ስም ብሶት በመቀስቀስና ዘወትር ደጋግሞ በማላዘን ልብህንና ትውልድህን ዘላለም ልግዛህ የሚልህን ክፉ ዘረኛ ቡድን እጅህን አጽጠው። ከጥንት ወንድምህ የኢትዮጵያ ልጅ እንዲለይህ አትፍቀድለት። መሞቱንማ ማንስ ያልሞተው አለ፧ አንተን በብሶት አሳቦ ሊገዛህ ተነሳብህ እንጂ።

ዛሬ የጎንደር ገንዘብ የውጪዎች እስኪመስል ድረስ በደርግ ግፍ በውጪ በስደትና ሞት ተገፍቶ የተበተነው፣ “የዛሬን ማርልኝ የነገን አልወልድም” ተብሎ እስኪለቀስ ወጣቱን ሲጨርስ አልኖረምን፧

ባድመ ተወረረች፣ የሰሜን ኢትዮጵያውያን ጠላት ተነሳባቸው ሲባል ሀገሬ ብሎ፣ ወንድሜ ብሎ፣ ለገበያ እንደወጣ ጭምር ከቤቱ ሳይመለስ በዛው ሄዶ የወደቀው የአማራ ምድር ኢትዮጵያዊ አልነበርምን፧

በደቡብ በምስራቅ ጠላት ኢትዮጵያውያንን እየገደለ ኦጋዴንን ያዘ ቢባል፣ ያለመደበኛ ቅጥር ተነስቶ የዘመተ ነፍጠኛ የገበሬ ልጅና ሚሊሻ፣ በዛውም ላይመለስ የወደቀ ማን መታሰቢያ እንኳን አደረገለት፧

ወገንህን ብቻ ሟች አድርጎ ብሶት እየቀሰቀሰ በሞጥ ተንተርሶ ለዳግም ሞት ሲጋብዥ፣ አንዳች ገድ የማይሰጠው ነፍሽን እቃው ሊያደርግ ሲያሴር አንተም አብረኸው አትደግፈው። እድል አያገኝምንጂ፣ ከቤጥ ግርግዳ ላይ የተለጠፈው ጭቃ እንኳን ከጥንት ጠላት በየቦታው በመጣ ቁጥር፣ ድንበር በተገፋ ቁጥር እየሄደ ሲሞት የነበረው የስንት የአማራ ምድር ኢትዮጵያዊ ደምና አጥንት አርሶት እንደኖረ በመሰከረ ነበር። የጎንደርንም አፈር ዘግነው ቢጠይቁት ደርቡሽ ሲነሳባት ሄዶ የተሰዋ የስንት የትግራይ ምድር ኢትዮጵያዊ ደም እንደያዘ በመሰከረ ነበር። በአድዋ ያለን ዛፍ ችለህ ብትጠይቀው ጠላት ትግራይ ምድርን መንካቱ ሲሰማ ልጆቻቸውን ጥለው ለወንድማቸው የመጡ የስንት የአማራና ሌሎችም ወገኖች አጥንት በስሩ እየዳበሰ እንደሆነ በነገረህ ነበር።

ሌላው ያልወደቀ ይመስል ከቶ ያንተን ብቻ ለይቶ በገዛ ደምህ ባሪያው እንዲያደርግህ፣ ከእግዚአብሄር እንዲያርቕ ስለምን ትፈቅድለታለህ፧ ያለፈው ደም ሳይደርቅ ለአዲስ እልቂት በዘረኝነትና በክፋት ሲያቀልምህ እሺ እንዳትለው፣ በታጋይነት ጀብዱ ትእቢት፣ በዘረኝነት ተሞልተው አምላክን አርቀው ክፉ መንፈስን የተላበሱ ክፉዎችን ተዋቸው፣ ልጆጭን መልስ።

በአንተም ሆነ በሌላውም በኩል የአማራም ሆነ የኦሮሞ የየትኛውም ዘረኞች እንዲሁ በአንድላይ ይከስማሉ። በፍቅርና ኢትዮጵያዊነት ሆነህ አምላክህን ብቻ ያዝ።

ካንተም መሀል ይሁን ከነሱ ዘርን መርጠው ፍቅርን አጠልሽተው የተነሱ ሁሉ በአንድነት ያልቃሉ። ክፉ የሆነ ከወንድማማቾች መሀል አንዱን ሌላ አንዱን ዘሬ በማለት የተለየ ጥቅመኝነትን የሚሰብኩ ሁሉ የያዙት ዘር ከየትኛው ይሁን ከየትኛው ያ በአምላክ ፊት አይታይም፣ በአንድነት ይጠፋሉ። ኢትዮጵያዊነቱን ተፀይፎ የቆመ በአንድላይ ይወድቃል። አንተም በቅዱሳን ቃልኪዳን የቆመውን ኢትዮጵያዊነትና ኢትዮጵያ ላይ ጠላት አድርገህ ራሽን አታስቀምጥ፣ በታሪክ ጥሩ መጨረሻ ኖሮት አያውቅምና።

ዘረኞች ዘሬ ብለው ከያዙት ዘር ሳይሆን መዝሙረኛው “ኢትዮጵያውያን በፊቱ ይመራሉ” ብሎ የተናገረላቸው ዥንጉርጉር የፍቅር ህዝብ ተለይተው ምንም ሳይሆኑ በእሳት ወላፈን መሀል ቆመው ይታያሉ። ሌላው አልቆ እነሱ ይቆማሉ። ቀኑ ቅርብ ነውና ከነሱ መሀል ራሽን አትጣው። ልጆጭንም አስተምራቸው።

የመፅሀፍ ቅዱሱ ቃል ወይ እውነት ወይ ሀሰት ነው። ከሁለቱ ውጪ የለውም። ሀሰት ወይ እውነት እንደምትል እምነጥን አንተው ታውቀዋለህ። ይሄም የዳዊት ትንቢታዊ ቃል ሳይፈፀም የሚቀር አይሆንም።

ጥንት በክፋት ተጠምደው የነበሩ የኔፍሊም ልጆች የነቢዩን ማስጠንቀቂያና የንሰሀ ጥሪ ችላ ብለው በርኩሰታቸው ቢቀጥሉ “ቅዱስ ገብርኤል ሰይፉን ሰጣቸው” ተብሎ እንደተፃፈና እርስበርስም ፍፁም ቅድቀት እንደተበላሉ ሁሉ፣ ጎራ ጎራ ይዘው በጥላቻም ሆነ በራስወዳድነት የተሰለፉ የዛሬ ዘረኞች ከየትኛውም ዘር ይሁኑ እርስበርሳቸው እንዲሁ ፍፁም መተላለቅን ይቋደሳሉ፣ የእሳት ሰይፉን ይዘው መራራውን የመከራ ሞት ፀዋ አንዱ ለሌላው ይጋታሉ።

በንግርትም ጭምር በሱ ዘመን እንኳን የሰው የእንጨት ጠማማ አይጠብቀውም እንደተባለው ክፉ ዘረኞችም ሆኑ የሀጢያት ሰወች ከትንሳኤው በፊት በሚበላው እሳት ከስመው ይቀራሉ።



“ማንነት” ማለት ምን ማለት ነው፧ እንዲሁ እንደፈለጉ በየጊዜው የሚቀያየር ነገር ነውንዴ፧ ትላንት የሆንከው ዛሬም የሆነው ነገም የምትሆነው ፅኑ ነገር ነውንጂ፧ ካልሆነማ እንዴት ማንነት ይሆናል፧



እግዚአብሄርን የረሱ ስልጣን እጅግ ያፈቀሩ ታጣቂዎች በቅድስና እምነትና በመልካም ሰብአዊ ፍቅር ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያን መሀል በደረቅ መሬት አጥብበው ከፍለው “ትግራይ ክልል” የተባልክ መሆንህን አትርሳ፦ የትግራይ ክልል ኢትዮጵያዊ መሆንህን አትርሳ ፦ ትግራይ ክልል ተብለው ከኢትዮጵያውያን መሀል የተከለሉ ኢትዮጵያውያን፦

የትግራይ ክልል ኢትዮጵያዊ ፦፦

ነኝ ብለህ ልትናገረው የሚገባህ ቀድሞን የነበርከው ያ ነው ያንተ መጠሪያ። ከዚያ አታጥብበው። ትግራይ ምድር ላይ ቤቱን የሰራ ኢትዮጵያዊ፣ ለልጁ “ተመልከት ያንተን ንብረት” ብሎ የላሊበላን ውቅር አብያተክርስትያናት የሚጠቁም፣ “ተመልከት ያንተን ሀብት“ ብሎ ጣናን፣ አባይን የሚጠቁም፣ ተመልከት የርስጥን ጫፍ” ብሎ ከካርታ ላይ ኦጋዴንን የሚያሳይ፣ እሱራሱ እንዲህ ተብሎ ከአባቶቹ የተረከበውን እንዳባቶቹ ታግሎ ጠብቆ ለሚወደው ልጁ ሙሉ መብትና ባለቤትነትን የሚሰጥ ነህ። አባቶቹ ደማቸውን ከፍለው የገዙትለትን ጥሎ የሚሸሽ ሳይሆን ወደፊትም ኢትዮጵያን የሚያድነው ኢትዮጵያዊ እንዳትሆን ከቶ ምን ያንስሀል፧

አንተ ራሽን ሁን፣ ለአምላክ ክልሉ ተከፍሎ አይታየውምና በሌላም ያሉ የኢትዮጵያ ጠላቶች፣ ባንተም መሀል ያሉ የኢትዮጵያ ጠላቶች በሙሉ በዚህ ተለይተው ይጠፋሉ። የትኛውንም ዘር ይልበሱ፣ በክፋት ለይተው ያንን አግንነው ለአቃፊ ክርስቶሳዊና ወንድማማቻዊ ፍቅር ኢትዮጵያዊነት ጠንቅ የሆኑት በሙሉ ይፈረድባቸዋል ለጥላቻና ጥፋት የጋለባቸውም አጋንንት የዚኛውን ባሪያውን ሙት ትቶ ለአላማው ሌላ ፍለጋ ይሄዳል።

አንተ የነበርከውን መጀመርያም ያንተ ማንነጥ የሆነውን ና ወንድሙን በከንቱ ለይቶ የማይጠላ ክርስቶስ በመሀል ለመገኛነት የሚመርጠውን በዥንጉርጉርነት መሀል ክርስቶስ፨ፍቅር ያስተሳሰረው ኢትዮጵያዊነትን ተላበስ። በንሰሀና ፀሎት ከአምላክህ ተግተህ ቅረብ። ጠላቶጭም በሙሉ በፅኑ ይወድቃሉ። እውነት የአምላክ እግዚአብሄርን መኖር ያመንክ ከሆንክ እሱ የወደደውን የዳዊት ስብእና ተላበስ፣ የአባቶጭ አምላክን ይዘህ በእሳት ማእበል ውስጥ ከፀጉርህ አንዲንም ሳይነካት ተጠብቀህ ኑር። መመኪያህን በስጋ ጀግንነት፣ በመሳሪያ ታጣቂነት፣ በወገን ሳይሆን በእግዚአብሄር አድርግ።



የተተነበየው የሚመጣው መከራና እልቂት አሻፈረኝ ብለው በተነሱ ዘረኞች መሀል እንዲቀር፣ የነሱ ጉዳይ ይሆን ዘንድ፣ አንተ ራሽን አንፃ አድን። ሀገርን ለማዳን በከንቱ ምድራዊ ፖለቲካ ልፊያ ላይ ሳይሆን በእግዚአብሄርና በሱ መንገድ ላይ ትጋ። እውነትም አለና፣ እንደ ልጁ፣ እጄን ያዘኝ በለው። ድህነት ከሀጢያት ለነፁት እንጂ የሆነ ፖለቲካ አቋም ለያዙት አይደለምና፣ በንሰሀ ታጥበህ ራሽን ከሀጢያት ጠብቀህ ዘወትር ድህነቱንና ይቅርታውን በመለመን ተዘጋጅተህ ኑር። ስለዘራቸው፣ ስለ ፖለቲካቸው ሳይሆን ስለ ፍቅርና እግዚአብሄር ልጅነታቸው ከሚተርፉ ጥቂቶች መሀከል ሁን።


Share on Google Plus

ስለ የተለጠፈበት ቀን

    Blogger Comment
    Facebook Comment