መልዕክት ለ ፕሮቴስንታቶች



በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስቅዱስ አሐዱ አምላክ ፤ ከቃሉ አንዲቷም ፈፅሞ

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ፤ከቃሉ አንዲቷም ፈፅሞ በማትታበል በአንድ አምላክ ስም

እኛ የሰው ልጆች ከታች በራሳችንና በፈለግነው መልኩ እንለያይ እንጂ እግዚአብሄር በኛ ልዩነት ተፅእኖ ስር ሆኖ አንዱን ከሌላው ለይቶ አይመለከተውም።

የአምላካችንም መልእክት ሲመጣ እንዲሁ ለሁሉ ለፈጠራቸው ልጆቹ ይሆን ዘንድ ነው። ለዛም ነው ይህ መልእክት ለእርስዎም የሆነው።
 
ይህንን የመልእክት ክፍል ለፕሮቴስታንቶች ሲፃፍ፣ እውነትን ከልባቸው ለሚፈልጉት፣ ለቲፎዞነት ሳይሆን እምነቱንም እውነተኛ አምላክን ለማወቅና ለመቅረብ ከልባቸው እየፈለጉ ብቻ ለሚከተሉትና፣ ኢየሱስ ክርስቶስን በእውነት ልባቸው ለሚወዱት፣ እንዲሁም መፅሀፍ ቅዱስ የሚለውን ለመከተል የሚተጉትን ታስቦ ነው።

እንጂ እንዲሁ ሀይማኖቱን በድፍን እንደ አምላክ ፍፁም አድርገው በንቀትና ጥላቻ ሌሎች ክርስትያኖችን ለሚመለከቱት፣ በራሱ አዳኝ የሆነውን የመፅሀፍ ቅዱስን ቃል በመተማመን ፈንታና ሌሎች ክርስትያኖችን እምነት በቅን ልቦና ለመመርመር ፈቃደኛ በመሆን ፋንታ እንዲሁ ሌሎች የሰጧቸውን ትርክት አፅንቶ በመያዝ ሳይመረምሩ በጭፍን ጥላቻ ራስን ፃድቅ በማድረግ የሚመኩትን፣ ባዕዳንን ሀገራትን ስራ በሁሉ ነገር ትክክለኛ የማድረግ ስነልቦና ውስጥ ሆነው፣ እውነትን ለማግኘት በቅን ልቦና ለመመርመር ልባቸው ፍፁም የተደፈነውን፣ ስለ እውነት ብለው መርምረውት የማያውቁትን፣ ሳይቀየር ተጠብቆ የኖረውን የጥንት ክርስትና እንዲሁም የራስ ሀገር እምነት ማንኳሰስ ቀሏቸው ራሳቸውን ለናቁ አይደለም።

ለዚህ አይነቶቹ መጀመርያም ማንም ገድ ሰጥቶት አይፅፍም።

ይልቁንስ መዳን ማለት በምድር ከተከፋፈሉት ሀይማኖቶች የአንዱ አባል ሆኖ በመመዝገብ ብቻ የሚገኝ ሳይሆን አምላክ ኢየሱስ ክርስቶስን በእውነት ልብ በመውደድ፣ የህይወት ዘመንን በሱ ፍቅር በሚደረጉ ተግባራት፣ እሱ ባቆመልን ህግጋት፣ ቃሉን ምክሩን በመከተል፣ በፍቅር የሱ የሆነውን ነገር ሁሉ በመውደድ፣ ነው ብለው ለሚያምኑ፣ የኔ ሀይማኖት ሰወች ናቸው በሚል ብቻ በሰወች ከሚባሉ ንጝሮችንና አስተሳሰቦች ይልቅ መፅሀፍ ቅዱስን ምን ጊዜም መተማመኛ ለሚያደርጉ የተፃፈ መልእክት ነው።


አጠቃላይ የዋናው መልእክት ይዘት ዛሬ ላለን ለሁላችንም ከባድ የመከራ ቀን ስለመጣ ለንሰሀና ለፀሎት ከዛሬም አሁን ተግተን እንድንነሳ የሚነግር ነው። ሌላ ጥያቄም ከቶ የለውም።

የዚህ አይነት ጥያቄ ደግሞ ከማንም ይምጣ ከማን ለጠያቂው ልፋትና ድካም ምላሽ ሊሆን የሚችል ጥቅም ወይም አንዳችም ትርፍ ሳይኖረው እንዲሁ በህዝብ በፍቅርና የሁሉ ድህነት ምኞት ብቻ ተነስቶ በብዙ ሀብትና ጊዜ መስእዋትነት የቀረበ ነው።

ይህ እውነትም ሆነ ውሸት፣

ማንም ክርስትያን እንደሚያውቀው፣ ንሰሀ መግባት አያከስር፨አያሰክር በማንም ተጠይቆ ቢደረግና ቢደጋገም ማንንም አይጎዳም። ቢበዛ ቀድሞም በየትኛዋ ደቂቃ እንደሚወስደን ለማናውቀው ሞት ዝግጁ ቢያደርገን ነውንጂ። ቅዱስ ቃሉ ትንቢትን አትናቁ ይላልና፣ ለመልካም የሚጣራ መልእክት ሲመጣ አምላካችንን ከሚመጣው ክፉ ነገር ይጠብቀን ዘንድ ልንለምነው ይገባል።

ለሰራነው ሀጢያት በፀፀት ይቅርታና ንሰሀ ተመልሰን፣ እንደልጅ ንፁህ ልብ በመያዝ ልጆቹን በእውነት ቃሉ በሚወድ አባታችን ፊት ቆመን ከሚመጣው እንዲጠብቀን፣ ወደመልካም መንገድ እንዲመልሰን ልንጠይቀው ይገባናል።

ንሰሀ ገብተን በንፅህና ሆነን፣ ተግተን ወዳጅ አባታችንን ልንለምነው ይገባናል።

(አምላካችን ቸር ነው፣ ከክፉ ነገር ይጠብቀናል፣ ምንም አልሆንም፣ እኔ ከክፉ ነገር የተጠበቅኩኝ ነኝ…) ይህ የብዙዎቻችን መልስ ሊሆን ይችላል። ነገርግን ልክ እንደዚሁ እንዳለን ወይም ነን የምንለውን ሆነን ሳለን ነው የአምላክ ፍርድ ከፊታችን የመጣው። እኛም አማኝ ነን ባልንበት፣ ክፉውም ክፉ ነው በተባለበት፣ አሁን በያዝነው መልክ ነው የአምላክ ቁጣ ከፊታችን የሚጠብቀን፣ ከምንም በላይ እሱ ያውቀናልና።

ስለዚህም ምንም አማኝ ነን ብንልም እንኳን እስከዛሬ ከፀለይነውና ከተጋነው የበለጠ መትጋት ይኖርብናል ነው ጠቅላላ መልዕክቱ። ዛሬ ሁላችንም አሁን ካለንበት የበለጠ ወደአምላካችን ይቅርታን ለምነን ከሚመጣው ያድነን ዘንድ ምክንያት ልንሰጠው ይገባናል።

በቻልነው መንገድ ሁሉ ራሳችንን በመፈተሽ ወደአምላካችን ለመቅረብ እጅግ መጣር ይኖርብናል። እምነታችን በቁስና ለስጋ ተገዥነት ወድቀን በንጝር ብቻ ለስሙ እንደምእራባውያን የምንይዘው ሳይሆን በቻልነው መንገድ ሁሉ ከህይወታችን ጋር በማቆራኘት፣ በፍቅር ፆምና በስግደት ስጋዊ ምቾታችን በጥቂቱም ቢሆን በመሰዋት ራሳችንን በጥትና ማስገዛትን እየተለማመድን የምናመልክ ካልሆነ ላልተን ላልተን እንደነሱ ቅዱስ ጳስሎው ስለመጨረሻው ዘመን ሰወች ሲናገር ዕየአምልኮት መልክ አላቸው ኃይሉን ግን ክደዋል” እንደተባሉት ልንሆን ነውን፧ ሀይማኖት ህጉን አፅንቶ እንደማህበረሰብ በጋራ የእለተለት ህይወታችን ላይ ገብቶ ተፅእኖ ከሌለው ክርስቶስ እራሱ ሲናገር “ጌታ ሆይ፥ ጌታ ሆይ፥ የሚለኝ ሁሉ መንግሥተ ሰማያት የሚገባ አይደለም።” እንዳለው ወደፊትም በእምነት ኖረን ብለን ተሸውደን ለፍርድ ቀን ግን “በስምህ ትንቢት አልተናገርንምን፥ በስምህስ አጋንንትን አላወጣንምን፥ በስምህስ ብዙ ተአምራትን አላደረግንምን፧ ይሉኛል። የዚያን ጊዜም። ከቶ አላወቅኋችሁም፤ እናንተ ዓመፀኞች፥ ከእኔ ራቁ ብዬ እመሰክርባቸዋለሁ።” ብሎ እንዳስጠነቀቀው እንዳንሆን ልንጠነቀቅ ይገባናል። መፅሀፍ በዚህ መልኩ ሳይታወቀን፣ በመልካም ምግባርና ሀይማኖት የቆምን መስሎን በባዶነት እንዳንኖር በክርስትና ስም ካሉ የበዙ መንገዶችን ከእውነተኛው ለይቶ ማወቁ ከባድ ነውና ይህንን ለዚህ ይረዳን ዘንድ መፅሀፍ ሲጠቁመን ስብከታቸውን ወይ ጌታ ጌታ ማለታቸውን ወይ የአምልኮት መልክ መያዛቸውን ሳይሆን ከሱ ይልቅ የሚለያቸው የመጨረሻዋ ፍሬያቸው እንደሆነች ይነግረናል። መፅሀፍ ሲነግረን “ከፍሬያቸው ታውቋቸዋላችሁ። ከእሾህ ወይን ከኩርንችጽ በለስ ይለቀማልን፧” ብሎ ከሁሉ የከበረውን መስፈርት ይጠቁመናል። በኢንተርኔት ከአለም አንደኛ ክርስትያን ሀገር ብለን ብናሽ ቁጥር አንድ ላይ አሜሪካን ያመጣልናል ሆንም ግን የአለም አዲሲቷ ሰዶምና ገሞራነትን የተላበሰችና ለሌላው የምትሰብክ፣ ምድራዊነትና የስጋዊነት ከየትኛውም ቦታ ከየትኛውም ዘመን በላይ የነገሰባት፣ ህፃናት የወደፊት ፆታቸውን እንድመርጡ የሚበረታቱባት፣ ቁሳዊነትና ዘማዊነት ባጠቃላይ ክርስቶስ የሚፀየፋቸው ነገሮች የነገሱባት የምድራችን ክፍል መሆኗን ሁላችንም የምናውቀው ነው። ታዲያ ክርስትና በሰፊው ቢስፋፋና በብዛት ቢሰፍን ፍሬው ይህ ነውን፧ ከፍሬያቸው ታውውቋቸዋቅላችሁ ብሎ በተናገረው ምን ልንላቸው ይሆን፧ እንደዚህ ካሉት የላሉ ቢበዙ እንኳን ማህበረሰብን ክርስቶስ በነገረን መልኩ የማይገነቡ፣ ባዶ ሆነው ሳለ፣ ነገር ግን ወደፊት “በስምህስ ብዙ ተአምራትን አላደረግንምን፧” ብለው ይጠይቁኛል፣ አላውቃችሁምም እላቸዋለሁ ካላቸው መንገዶች ልንጠበቅ በቻልነውም መጠን ክርስቶስን በፍቅርና ተግባር ከኑሯችን ያዋሀደን መንገድ ልንከተል ይገባናል።



በዚህ የሰፈረው ትንቢት ማብራርያ በመፅሀፍ ቅዱስ በነብዩ ኢሳያስ፣ ሕዝቅኤል፣ ዳንኤል፣ ወንጌላዊ ማቴዎስ… በብዙዎቹ ቅዱሳን የተነገረ ቢሆንም በዚህ ሲቀርብ ግን ተተርጉሞና ተጠንቶ፣ ተጠብቆ እንዲሁም በብዙ የኢትዮጵያዋ ቤተክርስትያን ባሉ ቅዱሳት መፅሀፍት በብዛት በመገኘቱና፣ ብዙዎቹም ለቅዱሳን አባቶቻችን በመላእክት አንደበት ስለተነገሩም በመልአክት ድርሳን መፅሀፍት፣ ለቅዱሳን በራዕይ ተገልፀው የተፃፉም ብዙ በመኖራቸው በገድላት እንዲሁም በራዕይ መፅሀፍት የተቀመጡ፣ በ ጥንት ኢትዮጵያ ቤተክርስትያን ሊቃውንትና አባቶች በልዩ መልክ ተጠንተውና ተላልፈው የደረሱን በመሆናቸው ምክንያት ብቻ የቤተክርስትያኗ ጭፍን ተቃውሞ እንዲሁም አንዳንዶችም ላይ ባለ ህቡዕ ጥላቻ ምክንያት ለመካድና፣ ላለመቀበል የሚወስኑ ብዙ ናቸው።

ብዙ የፕሮቴስታንት ሰወች እንዲሁም ሰባኪዎች እነዚህን ፕሮቴስታንታዊ ከተባለው አምልኮ በመንገዱ ለየት ባለ መልኩ እና ስርአት ክርስቶስን የሚያፈቅሩ የኢትዮጵያ ክርስቶሳውያን ክርስትያኖች እንደ አህዛብ፣ ክርስቶስን እንደማያውቁ አዛብቶ የመመልከትና የመናገር፣ እንዲሁም በሰባክያን ዘንድ ከክርስቶስ ማዕከላዊነት ይልቅ እኛ፨እነሱ በሚል አስተሳሰብን ማዕከል በማድረግ ለምዕመናን አዛብቶ የመናገር ችግር በብዙ ፕሮቴስታንቶች ስላለ ማለት ነው።

የኢትዮጵያ ቤተክርስትያን በምታደርጋቸው ነገሮች፣ ከክርስቶስ በታች በምታከብራቸው ቅዱሳን የተነሳ የዚህ አይነት ምልከታና ስብከት በአንዳንድ ፕሮቴስታንት ላይ የተዛባ ተፅእኖ አሳድሯል። ይህ ፅሁፍ የተፃፈው መሰል የቡድን ልዩነት ወሬዎችን ሳይሆን መፅሀፍ ቅዱስን በመከተል እውነተኛውን በክርስቶስ ፍቅር ላይ የተመስሰረቱ ተግባራትንና ያቀፈ ህይወትን ለመኖር ችለን ከሚመጣው እንድን ዘንድ ነው።

እውነት የማይፈልጉትን ተዋቸው።

አንተ ግን ይህንን ትድንበት ዘንድ የቀረበልህን ትንቢት ጨምሮ ይህች የጥንት ኢትዮጵያዊ ቤተክርስትያን የያዘቻቸውን ነገር ሁሉ በጭፍን ጥላቻ አይን ለማየት አትቸኩል። አምላክም ቢሆን “ትንቢትን ሁሉ አትናቁ” ብሎ ተናግሯልና።

ግን እነሱ እንደሚሉት የትኛው ነው ከክርስቶስ የሚያርቀው፧

ድንግል ማርያምን ማክበር፧

እንዴት ሆኖ፧

አንድ በእግዚአብሄር አምሳል የተፈጠረ ከቡር የሰው ልጅ አንድን ግኡዝ ቁስ “ይህ ቁስ እጅግ የከበረ ነው እኔ በጄ ልነካው የሚገባኝ አይደለሁም” ሲል ምን ያህል ከባድ ነገር ነው፧

ታላቁ መጥምቁ ቅዱስ ዮሐንስ ሲናገር ከኔ በሁዋላ የሚመጣው የጫማውን ጠፍር እንኳን ልፈታ የማይገባኝ ብሎ ነበረ ኢየሱስ ክርስቶስን የገለፀው።

የእግሩ መርገጫ የሆነውን ጫማ በእኔ እጅ ሊነካ የማይገባው ብሎ አክብሮ በማወደስ የክርስቶስን ክብር እጅግ እጅግ ከፍ አድርጎ ገለፀው።

ታዲያ የክርስቶስ መርገጫ በመሆኗ ምክንያት ጫማው እንዲህ ከከበረች፣ ታዲያ የወለደችው እንደልጅ እናቴ ብሎ ሚወዳት እሷማ እንዴት ያለ ክብር ይሰጣት፦ አምላካችን የሆነ ክርስቶስ የግሩ መረገጫ በመሆኗ ምክንያት በጫማው ላይ ያለች ጠፍር “በቅዱስ ዮሐንስ ለመነካት የምትከብር” እስከመባል ክብርና ውዳሴ ከተሰጣትና የሷ በክብር መታየት ለክርስቶስ ክብር መግለጫ ከሆነና ይህም ከተገባት ፤ ታዲያ ኢየሱስ እራሱ አክብሮ “እናቴ” ብሎ የሚጠራት፣ ከእቅፏ ሆኖ በእናት ፍቅር አይኗን እያየ፣ ጠረኗን እየናፈቀ ፣ ሰማያዊ አምላክ ሆኖ ሳለ እንደልጅ አቅፏት ጡቷንም ጠብቶ ያደገውን፣ የሚወዳትን በአሳዳጅ ገዳዮች መሀል በስጋት እያነባች በበርሀ ለበርሀ በስደት በእናት ፍቅር ስትደክምለት የተመለከታትን፣ ሲያያት እናቴ ብሎ እንደልጅነቱ በናፍቆት ሮጦ ሲያቅፋት ያደገ እናቱ፣ ከእናትም የራሷ ቤት እንኳን የሌላት እጅግ የድሀ ድሀ ሆና ያሳደገችው እንዴት ያለ ክብር ልንሰጣት ይቻለን ይሆን፧ ታዲያ ይህንን አስባ በክርስቶስ ፍቅር በተዋቀሩ ተግባራትና ህግጋት በዘመናት ርዝመት የደረጀች ቤተክርስትያንን ማንቃሸሹ ምን ይሆን ትርጉሙ፧

ሚረግጣት ጫማውን እንደዛ ያከበሩ ቅዱሳንስ የሚወዳትን እናቱን ምን ብለው ሊናገሩላት፣ አወድሰውስ ይጠግቡ ይሆን፧

በሉቃስ ወንጌል እራሷ “ትውልድ ሁሉ ብፅእት ይሉኛል” ብላ የሚከተሉትን እውነተኛ ክርስትያኖችን ትውልድ ተናግራ ነበር። ከጥንት ጀምሮ በዚህች ጥንታዊት ቤተክርስትያን ብፅእት ብለው ማርያምን እያወደሱ በመንፈስ ቅዱስ የተነገረውን ያንን ቅዱስ ትውልድ መሆን ነው “ክርስቶስን የማያውቁ” እንዲሉ ያደረጋቸው፧ ከራሱ ክርስቶስ እናት በላይ ስለ ክርስቶስ መከተል እናውቃለን እያሉን ነው፧

ይልቁንስ የኢትዮጵያ ቤተክርስትያን ድንግል ማርያምን አክብራ በመያዟ በታሪክ ለሺዎች አመታት በሀገሩ ምንጊዜም ክርክርም፣ ጥያቄም፣ አልፎ ስድብም፣ ቢመጣ እንኳን በድንግል ማርያም ዙሪያ ያርፋል እንጂ አልፎ የመዳን መሰረት በሆነው የክርስቶስ አምላክነትና አዳኝነት ላይ ሳያርፍ እንዲቆይ አድርጎታል። በዚህም መልኩ በፍፁም እምነት የተቀበሉት የክርስቶስ አዳኝነት፣ አምላክነት ለጥያቄ ሳይቀርብ፣ ያንን በልባቸው ቀርፀው አልፈው በውዳሴ ላይ ይገኙ ነበር፣ የሱ የሆነውን ሁሉ ማክበርና ማወደስ፣ ያለወንድ ዘር ሙሉ በሙሉ ስጋዋን የለበሰ እናቱንም ጨምሮ። አባቶች በጥበብ ለዋናው ቤት እንደ አጥር በር አድርገው የማርያምን ክብር አቁመውት ነበርና። ከቶ ማን አጥሩን በር ሳያፈርስ የዋናውን ቤት ሊቆረቁር ይቻለዋል፧ የክርስቶስን አምላክነት ፍፁም አምኖ ተቀብሎ፣ በልብ አፅንቶ ከዛ ተሻግሮ በፍቅር የሱ የሆነውን ሁሉ ወደመውደድና ማክበር የተሻገረ ወደኋላ ለመመለስ ብዙ ይፈጅበታልና። ሲጀመር ሀይማኖት ጥቅሙ ይህ አይደል፧ የኢየሱስ ክርስቶስን አምልኮ የሚያፀኑ የአኗኗር ስልቶችና ህግጋት ስብስብ፣ ምእመኑን ለድነት በሚመራ መልኩ የተቀረፁ በዘመን የደረጁ ስርአቶችና ህግጋት ስብስብ መሆኑ አይደል፧

በመፅሀፍ ቅዱስ እንደተፃፈው፣ አብርሀም ሳራ በሞተችበት ጊዜ ለረዱት ለኪጤ ሰወች እንደሰገደ፣ በለዓም ለመልአኩ በግንባሩ ወድቆ እንደሰገደ፣ ኢያሱም ወደምድር በግንባሩ ወድቆ ለ ሊቀመልአኩ እንደሰገደ፣ ሩትም በግንባሯ ወድቃ ለቦዔዝ እንደሰገደች… ሁሉ ዘርዝረን አንጨርሰውምንጂ እነዚህ ሁሉ የአምልኮ ሳይሆን የክብር ስግደት ሰግደው እንዳሳዩ፣ ያውም የአምላክና የጌታችን የሚወዳት ቅድስት እናቱ ለሆነችው ለክብሯ መስገድ ምኑ ይሆን ርክስና፧ የአምላካችንን ወላጅ እናት ከነዚህ ሁሉ አሳነሷትን፧

በስጋ አይን እንኳን ብናየው፣ በማህበረሰባዊ እሴት ግንባታ፣ በኢትዮጵያ አንድ ታላቅ ወንድ ካህን በአደባባይ ተንበርክኮ በግንባሩ ተደፍቶ ለቅድስት ድንግል ማርያም ለክብሯ ሲሰግድ ማየት ለሴቶች ምን ትርጉም ነው ያለው፧ ለሴቶች ክብር አንዲት አርማ የሆነች ካህናቱ ሊቃውንቱ ለክብሯ የሚሰግዱላት መኖሯ ለ ማህበረሰባዊ ስነልቦና ምን ይሆን ትርጉሙ፧ ክርስቶስ በጥንት በጥፋቷ በታወቀችው ሄዋን በኩል መድሀኒት ሆኖ መምጣቱስ ምንን ሊያስተካክል ነው፧ በዚህ ደረጃ እንኳን ለሺዎች ዘመናት በዚህ መልኩ የታነፀች እምነት መኖሯ ምን ያህል ስጦታ ነበር ለኛ ዛሬ ላለነው፧

የሰው ልጅ አእምሮ ሀያል ነውና፣ ታውረን ይህንን ልንንቅ ካልሆነ በስተቀር፣ ሆመቼም ፵ አመት እስከሚፈጁ ትምህርቶች ተምረው፣ ሳይንሳቸውም፤ ድላቸውም፤ ምርምራቸውም ሆኖ የእግዚአብሄር ነገርን በመመራመር፣ በፍቅርና ናፍቆት ተሞልተው በመሻት፣ በዚህ መልኩ ለሺ ዘመናት የኖሩበትን ውጤት እንዲሁ ከምድር ተነስተን የምንቅ ከሆነ ከባድ ግርዶሽ ውስጥ ነን ማለት ነው።

ለክርስቶስ ክብር የሚሆኑ ምስጋናዎችን በቅኔ፣ በቅዳሴ፣ በማህሌት፣ በድጓ… እስከ ፵ በላይ በሚፈጁ ትምህርቶች እየተማሩ አርቅቀው በትጋት እየኖሩ፣ ለሱ ካላቸው ፍቅራቸው የተነሳ ብሎም የሱ ወገን ለሆኑትም ክብራቸውን ቢገልፁ፣ የሱ የሆነችውን እናቱን ቢያከብሩ፣ ምኑ ይሆን ግራ የሚያጋባው፧

እውነት የማይፈልጉት ልባቸው የጠመመው በራሳቸው መንገድ ይሂዱ። አንተ ግን ይልቅ ሰዎችን ሳይሆን መፅሀፍ ቅዱስንና በክርስቶስ ፍቅር ተነሳስተው የሚደረጉ የተቀረፁ ተግባራትን ተከተል።

አንተ ግን ይህንን ትድንበት ዘንድ የቀረበልህን ትንቢት ጨምሮ ይህች የጥንት ኢትዮጵያዊ ቤተክርስትያን የያዘቻቸውን ጥልቅ ነገሮች ሁሉ አንዲትም ሳይመረምሩ እንዲሁ በጭፍን ጥላቻ አይን ለማየት የምትቸኩል አትሁን፣ በመፅሀፍ ቅዱስ መንገድ ክርስቶስን በፍፁም ፍቅር የሚያምኑ ሁሉ ከክርስቶስ ልጅነት የሚከለክላቸው የለምና። አምላክም ቢሆን “ትንቢትን ሁሉ አትናቁ” ብሎ ተናግሯልና።

ሌላስ እነሱ እንደሚሉት የትኛው ይሆን ከክርስቶስ የሚያርቀው፧

ለመላእክት የአምልኮ ሳይሆን የክብር ስግደት መስገዱን ነው፧

ምን አይነት ትርጉም የሌለው ንጝር ነው የሚናገሩት፧

ማነው ለመልአኩ ሀያል ክብርንና ማንም የማይቋቋመው አስፈሪ ሞገስን ያለበሰው፧

ድንገት አንድ መልአክ በፊቱ ቢገለፅ፣ ሞገሱን ተቋቁሞ ችሎ ሊቆም የማይችልና በግንባሩ የሚወድቅ ሁሉ በምድር ሆኖ “ለመልአክ አልሰግድም” እያለ ሲመፃደቅ ማየት እንዴት ይገርም ይሆን፧ የምላስ ሀይል ብቻ ከፍ ያደረጋቸው አላዋቂዎች ነው ወይስ እግዚአብሄርን “እንዲህ ሞገስ አልብሰህ ፈጥረህ አሳትከኝ፧” ብሎ ሊከሰው ነው፧


የኢትዮጵያ አባቶችና እናቶች፣ ዕቅዱስ ገብርኤል ይከተልህዕ፣ ዕቅዱስ ሚካኤል ይጠብቕዕ።።። ብለው ሲመርቁ ቢሰሙ፣ የዘመኑ አላዋቂዎች ዕይህ ለመልአክት አይባልምዕ፣ ዕክህደት ነውዕ፣ ዕበመፅሀፍ ቅዱስ የሌለ ነውዕ።።። ወዘተ ብለው ሊመፃደቁባቸው ይሯሯጣሉ።

ለመሆኑ ውጊያቸው ከማንጋር ነው፧

ከአባቶቻችን ከአብርሀምና ከይስሀቅ ጋር ነው፧ ካልሆነስ የእግዚአብሄር ውድ ልጁ ከሆነው፣ ዕእስራኤልዕ የሚለውን መጠሪያ ከአምላክ ከተቀበለው ያዕቆብ ጋር ነው ውጊያቸው፧ ያዕቆብ ልጆቹን በመረቀ ጊዜ በመፅሀፍ ቅዱስ ዘፍ ፬፰፡፪፩ ዕከክፉ ነገር ሁሉ ያዳነኝ መልአክ፥ እርሱ እነዚህን ብላቴኖች ይባርክዕ ብሎ ለተናገረው ቃል ሊከሱት የሚመፃደቁን ምን እንበላቸው፧ ነው ወይስ ውጊያቸው ክብራቸው የእግዚአብሄርን ፊት እስከማየት ከፍ ካለው ከመልአክት ጋር ነው፧

ከንቱ ተዋጊዎች ብሎም የኢትዮጵያ ቤተክርስትያን ህዝብ በልመናው ዕቅዱስ ሚካኤል ሆይ፣ እባክህን ከጠላት ውጊያ ጠብቀኝዕ፣ ዕቅዱስ ገብርኤል ሆይ ከመከራ ሰውረኝዕ።።። ብሎ በዚህ መልኩ መልአክትን ቢማፀን ዛሬ ራሳቸውን ያፀደቁ አላዋቂዎች ሊተቹና ሊሳደቡ ሲመፃደቁ ይታያል። ወይ በአባቶቻችን ዘመን ሎጥ መልአኩን ጌታዬ ሆይ ብሎ በልመና ቢማፀን ዕየተናገርካትን ከተማ እንዳላጠፋት እነሆ በዚህ ነገር የለመንከኝን ተቀብያለሁዕ ብሎ የመለሰለትን፣ ሊሄድባት ያሰባትንም መንደር ከጥፋት የታደጋትን መልአክ ዕስለምን ልመናን ትቀበላለህ፧ መች ስልጣን ሰጠሁህ፣ መች ፈቀድኩልህዕ ብለው ይቃወሙት ይሆናል። ምናልባትም መልአኩ ኢያሱ ዘንድ በመጣ ጊዜ በመፅሀፍ ቅዱስ እንደተፃፈው ዕ።።።እኔ የእግዚአብሔር ሠራዊት አለቃ ሆኜ አሁን መጥቼአለሁ አለ። ኢያሱም ወደ ምድር በግምባሩ ተደፍቶ ሰገደና። ጌታዬ።።።ዕ የሚለውን ባዩ ጊዜ በመልአኩና በኢያሱ ላይ ሌላም ሌላም ነገር እንናገር ሳይሉ የሚቀሩ አይመስሉም።

የዚህ አይነቶቹን መከተል ራስን ማውረድ ነው። ለራሳቸው ፍርድ ተዋቸው፣ መፅሀፍ ቅዱስን አስቀድመህ ተከተል። ትላንት ከትላንት ወዲያ በተነሱት፣ ያውም እምነትን እንደሁለተኛ ወይ ከዛ በታች አድርገው በሚኖሩ ውጪዎች ባህል ሳይሆን፣ ለሺ አመታት ያውም ሳይቋረጥ ባህሏም፣ ምርምሯም፣ ጥበቧም ይኸንኑ አድርጋ፣ አምላክን ክርስቶስን ከጥንትም መሰረቷ አድርጋ በዚህ መልኩ በዘመን ሂደት የተቀረፀው ባህሏን፣ የኢትዮጵያ ክርስትናን ባህል መላበሱ ከብዙ በብዙ ይልቃል። ሲሆን ሲሆን፣ ይህችው ያንተው ሀገር የኢትዮጵያ ቤተክርስትያን መልክህ፣ ሀብጥ፣ ለዘመናት ያንተው አያት ቅድመአያቶጭ በእውነት ከክርስቶስ የተዋሀዱባት ማንነጥ፣ በአፍሪካውያን በአለምም ሁሉ ፊት ቀደምት ያንተው መከበሪያህ ነበረች። እሷም አምናም፣ ትላንትም፣ ዛሬም ነገም የተቀላቀሏት፣ የሚቀላቀሏትም ሁሉ እኩል ሀብት ናት።



በነሱ አፍ ሌላስ የትኛው ነው ከክርስቶስ የሚያርቀው፧

ሮብ ሮብ ሲሆን፣ እያዘኑ አንተን በዚህ እለት ያለጥፋጥ ሞት ፈረዱብህ፧ በማለት በዚህስ ቀንስ ምግብ አልበላም ብሎ ራስን ከምቹ ምግቦች ከስጋ ከወተት ቆጥቦ እስከ ፮ ና ፱ ሰአት እድሜልክ በራስ ፈቃድ መፆሙ፧

አርብ ሲሆን፣ በሀዘን በዚህ እለት ያለሀጢያጥ ከወንበዴዎች አባቴን ጋር ሰቀሉህ፧ ብሎ እንዲሁ ቀኑን በማሰብ ከልጅነት ጀምሮ እድሜ ልክ በዚህ እለት ምግብ ለግማሽ ቀን ሳይበሉ ቡሀላም በፆም ምግብ መዋል ነው ከኢየሱስ ክርስቶስ የሚያርቀው፧



የዚህ አይነት ከንቱ ጠማማነትን በመያዝ ሌላውን ከድህነት ይልቅ ጎራ ይዞ በድንቁርና ውሸት መከራከርን የሚመርጡትን ተዋቸውና አንተ ግን ራሽ በንሰሀ አፅድተህ፣ የሰራኸውን ላትደግመው ለራሽ አምነህ እንደልጅ በፍቅር ሆነህ አምላክህን ምህረትን፣ ከሚመጣው መአት መጠበቅን አንዴ ሳይሆን ዘወትር ለምነው።



ራሽንም በአምላክህ ዘንድ ዝቅ አድርገህ፣ ዘወትር ተግተህ ለምነው፣ ራሽንም ዝቅ አድርገህ፣ አይደለም ከሱ ከሀያሉ ጌታ፣ አገልጋዮቹ ከሆኑ ከመልአክቱም ስር በጥትና ወድቀህ ለምናቸው፣ ወደክርስቶስ እንዲለምኑልህ ለምናቸው። መልአክትን ለምኑልን ብሎ መጠየቅ አዲስ ነገር ሳይሆን በመፅሀፍ ቅዱስም መከራ በፀና ቁጥር ቅዱሳን የሚያደርጉት የጥትናና ራስን ዝቅ የማድረግ ተግባር ነውና፣ ያውም በመፅሀፍቅዱስ ላይ ከሁሉም የመጀመርያ ፅሁፍ በሆነው መፅሀፈ ሔኖክ ላይ ጭምር በመከራ ልመና የፀኑ ሰወች ወደአምላካቸው እየለመኑ እንደገናም ዕእናንተ በሰማይ ያላችሁ መላእክት ልመናችንን ወደእግዚአብሄር አግቡልንዕ እያሉ ሲማፀኑ ጭምር ቃል በቃልም ሰፍሯልና።
ለነገሩ ከነሱ ማን ይህንን መፅሀፍ ይቀበለውና፧

ፕሮቴስታንቲዝም ሲመሰረት፣ የመፅሀፍቅዱስን ስብጥር እንዳዲስ ሲያደራጁ መፅሀፍት በዘመናት በተነሱ ጥፋቶች በመጥፋታቸውና በመበታተናቸው በነጮቹ እጅ መፅሀፈ ሔኖክ በትክክል ተሟልቶ ባለመኖሩ የተገኙትን ፮፮ መፅሀፍት በመፅሀፍ ቅዱስ ውስጥ አደረጓቸው። ቡሀላም በቅርብ በውጪዎቹ ፩፱፬፯ ሙትባህር አርኪዎሎጂስቶች ወጥቶ በጥናት ጊዜው ከሺ ሰባትመቶ አመታት በላይ አካባቢ መሆኑ የተመሰከረለት እውነተኛ የጥንት መፅሀፈ ሔኖክ በመገኘቱ ቡሀላም ሲስተያይ በኢትዮጵያ ቤተክርስትያን ውስጥ ብቻ ተጠብቆ ካለው መፅሀፈ ሔኖክ ጋር ተመሳሳይ ሆኖ መገኘቱ በይፋ የተዘገበና አለምን ያስገረመ ታሪክ ሆኗል። ቡሀላም ለክርስትያኖች የሚቀርብበት መንገድ እየተጠና፣ አንዳንድ ቦታላይም እየተያያዘ እየተሸጠ፣ በብዙ አጥኚዎች ጥናት እየተደረገ ይገኛል።

ታዲያ በዘመናት ተጠብቃ ተከልላ ሳትወረር ሳትበረዝ በቅድስና የኖረች በጃንደረባው አማካኝነት ከሁሉ ቀድማ መቀበሏ በመፅሀፍ ቅዱስ የተመሰከረላት፣ ከየዘመኑ ጋር አብሮ ለማስኬድ ብላ እምነቷን ሳትነካካ እንዳለ ያኖረች፣ ይህንንና መሰል ቅዱሳት መፅሀፍትን ጠብቃ በክብር ያኖረች እንቁ ክርስትያን ሀገር ውስጥ እየኖሩ፣ መፅሀፉን ፈልገው ካጡት ውጪዎች ጋር አብሮ መቸገር “ያባይ ልጅ ውሀ ጠማው” የሚያስብል፣ አሳዛኝ ያዲሱ ትውልድ የውጪ አምላኪነት ህመሙ ይመስላል።

ከኦርቶዶክስ ተዋህዶም እምነት ቢሆን እንደዚሁ ስለሌሎች ሀይማኖቶች በጥላቻና ድፍንነት፣ በጎራ ያዥነትና አለመመርመር በከንቱ የሚናገሩትን ሚያጥላሉትን ተዋቸው። በሌሎችም ሆነ በፕሮቴስታንት ሀይማኖት ያሉት የዚህ መሰል ያለምርመራ ሀሰት ተናጋሪዎች ለማንም አይጠቅሙም። እውነትን ከመፈለግ ይልቅ ክርስቶስን ከመፈለግ ይልቅ የሀይማኖት ጎራን እንደአምልኮ ይዘው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስትያንን እንዲሁ በጥላቻ ብቻ በመስበክ የሚከራከሩትን አሁንም ተዋቸው። ይሁዳ በመልእክቱ በስሙ ጠርቶ የመሰከረለትን ነብዩን ሄኖክ፣ ወንጌላዊው ጳውሎስ ሄኖክ ከክብሩና ቅድስናው የተነሳ ሞትን እንኳን ሳይቀምሳት በእግዚአብሄር መወሰዱን፣ አምላክንም ደስ እንዳሰኘ የመሰከረለትን ሄኖክ እንደው ማን ነን ብለው፣ እንዴት ቢመፃደቁ ይሆን አንቀበልም የሚሉት፧ የሚቀበሉስ ቢኖሩ፣ ነብዩ ኤርሚያስን ተቀብሎ ትንቢተ ኤርሚያስ መፅሀፍን መጣል ምን ማለት ይሆን፧ ነብዩ ኢሳያስን ተቀብሎ ትንቢተ ኢሳያስንስ መፅሀፍን መጣል ምን ማለት ይሆን፧ ባካል ያላገኙት ከሄኖክ ከሺ ዘመናት በኋላ የመጡት ሀዋርያት፣ እነ ቅዱስ ጳውሎስ፣ እነ ይሁዳ በዘመናቸው ያነበቡትን፣ ሄኖክንም አውቀውት እንዲመሰክሩለት ያስቻላቸውን መፅሀፍ መጣል መቃወም እንዴት ያለ መመፃደቅና ክህደት እንደሆነ ራሳቸው የካዱት ይወቁት።

አንተ ግን አባጥ ክርስቶስን፣ እውነትን ለማወቅ ብቻ አላማህ አድርገህ ኑር። ከሚመጣው እንዲጠብቕ ለምነው።

የሚጠብቀን ውድቀታችን እጅግ የከፋ ነውና በሁሉ መንገድ እጅግ ተግተህ በሁሉ መንገድ በእንባ ለምነው። እውነትም መከራው ከሌላው አለም ኢአማንያን ይልቅ በኛ ይፀናልና። ከመጀመርያው በወንጌል ተጠማቂ ኢትዮጵያዊው ጃንደረባ ጀምሮ መቶ አይደለም፣ ሺዎች አመታትን በክርስትና፣ በእግዚአብሄር ተአምራት መሀል የኖርን፣ ምሳሌ በሚሆኑ የክርስቶስ ቅዱሳን ገድልና ታሪክ በዝቶ በሚነገርበት፣ ቅዳሴ ያለማቋረጥ በሚፈስበት ሀገር ላይ ሆነን በክህደት መንገድ ስንጓዝ፣ በውድቀት በርክስና መንገድ ስንነጉድ የቅጣት መከራችን እንዴት እንደሚበዛ መፅሀፍ ቅዱስን አንብቦ የሚያውቅ ክርስትያን ሁሉ እንግዳ አይሆንበትም። ምክንያቱም በመፅሀፍ ቅዱስ ወንጌል አንዴ ብቻ ሳይሆን ሁለቴም ሳይሆን ሶስት ቦታ ላይ በማቴዎስ በማርቆስ እንዲሁም በሌላ አገላለፅ በሉቃስ ወንጌል ላይ ይኸው ቃል ተደጋግሞ የተፃፈ ነውና

“ወዮልሽ ኮራዚ፤ ወዮልሽ ቤተ ሳይዳ፤ በእናንተ የተደረገው ተአምራት በጢሮስና በሲዶና ተደርጎ ቢሆን፥ ማቅ ለብሰው አመድም ነስንሰው ከብዙ ጊዜ በፊት ንስሐ በገቡ ነበርና። ነገር ግን እላችኋለሁ፥ በፍርድ ቀን ከእናንተ ይልቅ ለጢሮስና ለሲዶና ይቀልላቸዋል። ።።። ነገር ግን እላችኋለሁ፥ በፍርድ ቀን ከአንቺ ይልቅ ለሰዶም አገር ይቀልላታል።ዕ

በዚህ መሰረት የተተነበየው ጥፋትና መከራ በኛ ላይ እንደሚፀና ምስክር ነው። ሁላችንም እጅግ ተግተን ተባብረን ወደአምላካችን ልንጮህ ይገባናል። ለቅዱሳን ልጆቹ ስለገባቸው ቃልኪዳኖች ብሎ ይምረን ዘንድ ልንለምነው ይገባናል።






Share on Google Plus

ስለ የተለጠፈበት ቀን

    Blogger Comment
    Facebook Comment