ምከረው፣ ምከረው እምቢ ካለ መከራ ይምከረው! ጸረ ኢትዮጵያ ከኤርትራ ተማሩ!

ዘርአዳዊት ዘ-ኢትዮጵያ
በጣም አሳዛኝ ነገር ነውወገን ለመማር አለመቻሉ ደግሞ ብዙ ንዴትንና ቁጣን ይቀሰቅሳል።
በኤርትራ የሚኖሩ ወገኖቻችን ኢትዮጵያዊነታቸውን በመካድ ኤርትራ የምትባል አዲስ ሃገር ሲቆረቁሩ፤ በቃ ማርና ወተት የሚጎርፍባት የበለጸገች ሃገር ትሆናለች ብለው በጽኑ ያምኑ ነበር። በእውነት ለመናገር ስድስት ሚሊየን ብቻ ነዋሪዎች ያሏት ኤርትራ በቀይ ባሕር ጠረፍ ላይ የሚገኙትን ቦታዎች በማልማት በቱሪዝም ብቻ ትበለጽግ ነበር፤ ህዝቡም ታታሪ ስለሆነ እነ ምጽዋ እና የዳህላክ ደሴቶች ከግብጾቹ የቀይ ባሕር ቱሪስቶች ማዕከላት፡ ከ ሻርም አልሼክ እና ሁርጋዳ በበለጠ መልክ አውሮፓውያን ጎብኝዎችን በብዛት የመሳብ እድል ነበራቸው።
ነገር ግን ያው እንግዲህ የኢትዮጲያን ካባ አውልቀው ከጣሉ ሃያ ዓመታትን አስቆጥረዋል፤ ምንም የተሳካ ነገር የለም፤ ዜሮናዳእንዲያውም ትውልዱ ኢትዮጵያዊነቱን በመካዱ ብቻ ታይቶ የማይታወቅ መቀመቅ ውስጥ ለመግባት ተገድዷል። አንድ የሃበሻ ትውልድ ተሰድዶ በማለቅ ላይ ይገኛል፤ ወጣት ኤርትራውያን ድኻ ዘመዶቻቸው ለፍተው ያጠራቀሙላቸውን ገንዘብ ይዘው በመጓዝ የአረብ ሕገወጥ አዘዋዋሪዎች ምሳ በመሆን ላይ ናቸው፣ ከዚያ የተረፉት በሰሜን እና ምስራቅ ባሕራት ላይ የአሳ ነባሪዎች እራት ናቸው፤ የአባይ ወንዝ ቅዱሱን የጽዮን ተራሮች አፈር ጠራርጎ በመውሰድ ለአውሮፓው ባሕር ኢትዮጵያ ግብር የምትከፍለው አልበቃ ብሎ ኤርትራውያኑም ለዲያብሎስ የደም ግብር በውሃው ላይ እየከፈሉ ነው፣ በአረብ በርሃዎች ደግሞ የኩላሊትና ጉበት መለዋወጫ የሚገኙባቸው ሳጥኖች ሆነዋል፤ ሁሉም በነፃ፣ ሁሉም በፈቃዳቸው።
ቀደም ሲል፡ እነ ግራኝ አብዮት አመድ ለቀመሙት ዲያብሎሳዊ ሴራ ማጣፈጫ ይሆን ዘንድ የሰሜኑን ድንብር ለኤርትራውያን ክፍት ሲያደርጉ ኤርትራውያኑ ኢትዮጲያዊነታቸውን መልሰው እንዳገኙት ሆኖ ስለተሰማቸው በብዙ መቶ ሺህ የሚቆጠሩት ወደተቀረው የኢትዮጵያ ግዛት መጉረፍ ጀመሩ። ነገር ግን ይህ “የኩሽ መንገስት እንመሠርታለን” ብለው የተነሱትን እባቦቹን እነ ግራኝ አብዮት አህመድን አላስደሰታቸውም፤ “ኦሮሞ እንጅ ኢትዮጵያን መውረር ያለበት፣ ኢትዮጵያውያን ኢትዮጵያን መያዝ አይችሉም” በሚል የድንጋጤ ምላሽ፡ የኤርትራና ኢትዮጵያ ድንበር ወዲያው እንዲዘጋ አዘዙ።
አሁን ኤርትራውያን እንደገና በአረብ በረሃ ላይ እና በሜዲተራንያን ባሕር ውስጥ እያለቁ ነው። ኢትዮጵያዊነታቸውን ለመክዳት በመዘጋጀት ላይ ያሉት ሌሎቹ ግብዞች እና ከሃዲዎች በእውነት ሉሲፈርን በማገልገል አገር ለማጥፋት አቅደው ካልሆነ በቀር፡ እውነት በጎ ነገር ካሰቡ እንዴት ከዚህ መማር ያቅታቸዋልእንዴት መንደርተኘነቱን እንተው፣ የጠላት መጫወቻዎች መሆኑ ይብቃን ማለት ያዳግታቸዋል???
በ “ኢትዮጵያ” ላይ ከሁሉም አቅጣጫ ጦርነት እየተካሄደ ነው፤ ትውልድ እያለቀ ነው፡ ይህ በዝምታ የሚታለፍ ጉዳይ አይደለም፡ ወገን!
Share on Google Plus

ስለ የተለጠፈበት ቀን

    Blogger Comment
    Facebook Comment