በ ጎንደር የአቡነ ተክለ ሐይማኖት ቤተክርስቲያን ተቃጠለ

ዘርአዳዊት ዘ-ኢትዮጵያ
በደቡብ ጎንደር ፋርጣ ወረዳ የቅዱሱ አባታችን የአቡነ ተክለኃይማኖት ቤተክርስቲያን ተቃጥሏል።
የአከባቢው ነዋሪ እንደገለጸው ከሰሞኑን ለነዋሪው እንግዳ የሆኑ ሰዎች መታየታቸውን እና ምንም አይነት ሌላ ምክንያት እንደሌለው ገልጸዋል። ቤተክርስቲያኑ ሙሉ ለሙሉ በእሳት ወድሟል።
ስንት አባቶች፣ እናቶች፣ ሕፃናት እና አገልጋዮች መገደል አለባቸው ግራኝ አብዮት አህመድን ለመቅጣትስንት አብያተክርስቲያናት መቃጠል አለባቸው ለሰላማዊ ሠልፍ ለመውጣት?
የቤተክርስቲያናችንን የፈተና እና የሕዝባችንን የስቃይ ጊዜ በማራዘም ቁልፍ ሚና የሚጫወቱት አይን እያላቸው የማያዩት ፤ ጆሮ እያላቸው የማይሰሙት ወገኖች ናቸው። መጥፎውን ሽሹ መልካሙን እሹ!

[የማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ ፲፮፥፬]

“ክፉና አመንዝራ ትውልድ ምልክት ይሻል”
ተክልዬ አባቴ ሆይ፤ ይህንን መቅደስህን ሆን ብለው እሳት በለኮሱት የክርስቶስ ተቃዋሚዎች ላይ በእውነት አባታችን አንተ ማጥ ልቀቅባቸው።
የአባታችን የአቡነ ተክለ ሀይማኖት ምልጃና ጸሎታቸው ረድዔትና በረከታቸው በኛ በልጆቻቸው ላይ ይደርብን አሜን!
Share on Google Plus

ስለ የተለጠፈበት ቀን

    Blogger Comment
    Facebook Comment