ዘርአዳዊት ዘ-ኢትዮጵያ
…ነጠብጣቦቹን…እናገናኝ፦
– ግራኝ አብዮት አህመድ በግራ እጁ በጻፈው መጽሐፉ አስቀድሞ ይህን ብሎን አልነበር፦
“….ሰዎች ጥቅም ወዳድ ናቸውና በጥቅም ሂድባቸው…የሚፈልጉትን እያሳየህ ወደምትፈልገው ስፍራ ውሰድ እና ጣላቸው… ከዚያም በሬ ሆይ! ሳሩን አየህና ገደሉን ሳታይ… ብለህ ተርትባቸው“
+ ቅዱሱ መጽሐፍ ደግሞ ይህን ይለናል፦
[፩ኛ ወደ ጢሞቴዎስ ምዕራፍ ፭ ፥ ፲፯፡፲፰]
“በመልካም የሚያስተዳድሩ ሽማግሌዎች፥ ይልቁንም በመስበክና በማስተማር የሚደክሙት፥ እጥፍ ክብር ይገባቸዋል። መጽሐፍ። የሚያበራየውን በሬ አፉን አትሰር፥ ደግሞ። ለሠራተኛ ደመወዙ ይገባዋል ይላልና።”
ዕለተ ደመራ
አስራ አንድ ሰዓት አካባቢ ክብረ በዓሉ በመካሄድ ላይ እያለ አንድ ከየት እንደመጣ ያልታወቀ “ባለቤት–አልባ በሬ በመስቀል አደባባይ ሲንጎራደድ ይታያል። በዚህ ወቅት በበዓሉ ላይ የተሳተፉት አድባራትና የከበቧቸው ፖሊሶች አደባባዩን ሞልተውታል። በሬው ወዲያና ወዲህ እያለ ይወራጫል፤ በተዋሕዶ ልጆች ላይ አድሎና በደል የሚፈጽሙትን እንዲሁም የኢትዮጵያን ባንዲራ የሚከለክሉትን ጡት–ነካሽ ፖሊሶችን የሚፈልግ ይመስላል። ብዙም አልቆየም አንዱን ፖሊስ አግኝቶ መሬት ላይ አነጠፈው። ይህ “የፌደራል ፖሊስ” ለተባለው ፀረ–ኢትዮጵያ እና ፀረ–አዲስ አበባ ሠራዊት የተሰጠ ማስጠንቀቂያ ተደርጎ ሊወሰድ ይገባል። አዲስ አበባ ከፌደራል ሳይሆን የራሷ ፖሊስ ከራሷ ከተማ ነዋሪዎች መመልመል ይኖርባታልና ነው።
በኦሮሞ ብሔርተኞች በመዋጥ ላይ ያለው የፌደራል ፖሊስ ሠራዊት በአዲስ አበባ ነዋሪዎች ላይ ብዙ በደሎችን በየዕለቱ በመፈጸም ላይ ነው። ይህ የገዳይ አል–አብይ ሠራዊት ወደ ደመራ ክብረ በዓል በጥባጭ ቆርቆሮዎቹን ቄሮዎችን መላክ ሰልፈራ ያሰለጠነውን ምስኪን በሬ ወደ መስቀል አደባባይ መላኩን መረጠ።
እነዚህ የኢትዮጵያና የመስቀሉ ጠላቶች ለክፋት ያሰቡትን እግዚአብሔር ለበጎ አድርጎታል።
በሬ የሰውን ልጅ ለዘመናት ሲያገለግል የቆየ አሁንም በማገልገል ላይ ያለ ጠንካራና ጠቃሚ ፍጡር ነው። ያለበሬ ሰብል የለም፤ እህል የለም። አገልጋዩን በሬ እንደ ኢትዮጵያ አድርገን ብንወስደው ይህ በሬ የኢትዮጵያን ጡት የነከሱትንና ከ666ቱ ጋር የተደመሩትን ነበር ሲያሳድድ የነበረው። አዎ! “ጡት አጥብታ ያሳደገቻችሁን፣ የጠበቀቻችሁን፣ ያስተማረቻችሁንና ብዙ ነገር የሰጠቻችሁን ኢትዮጵያን አትንኳት!“ የሚል መልዕክት በሬው ያስተላለፈልን መሰለኝ። በሬው የጎዳቸው የኛዎቹስ? አትደመሩ! የሉሲፈር ኮከብ ያረፈበትን የኢትዮጵያ ባንዲራ አትያዙ!“ ተብለው አልነበረም!?
ክፍል ፪
ዕለተ መስቀል / ቅዱስ እስጢፋኖስ ቤተክርስቲያን ግቢ / ጠዋት ላይ
ምዕመናን ወደተሰበሰቡበት ቦታ ሳመራ የደመራው በሬ መሬት ላይ ተጋድሞ አገኘሁት፤ አራቱም እግሮቹ ተጠፍረው ታስረዋል፣ አፉ ታስሯል፤ በብዙ ፖሊሶቹም ተከብቧል። የበሬው ስቃይ አሳዘነኝ፤ በዚህ ወቅት ሞባይሌን አወጣሁና ተንቀሳቃሽ ምስል ወድምጽ መቅረጽ እንደጀመርኩ “ተው! አታንሳ!” የሚል ድምጽ ከበስተጎኔ ሰማሁ ፥ እኔም፡ “ምን አገባህ!?” በማለት መለስኩለት። በዚህ ወቅት ሰውየው ወደኔ ጠጋ አለና መታወቂያ ነገር አሳየኝ። መለዮ ያልለበሰ የፌደራል ፖሊስ ነበር።
“ለምንድን ነው በሬውን የምትቀርጸው? ሞባይሉን አምጣ!ያነሳኽውን አሳያኝ” አለኝና ሞባይሌን ወሰደው። ቪዲዮውን ከደመሰሰ በኋላ ሞባይሉን መለሰልኝ። “የአዲስ አበባ ሰው ነህ? እዚህ ምን ትሠራለህ?” አለኝ። እኔም “ይህች የእኔ ቤተክርስቲያን ነች፤ እርስዎ እዚህ ምን ይሠራሉ? የተዋሕዶ ማሕተብ አለዎት?” አልኩት በድፍረት። እርሱም፡ “የለኝም!” በማለት መለሰልኝ። እኔም፡ “ስለዚህ እዚህ መገኘት የለብዎትም፤ ይህ የተዋሕዶ ብቻ የሆነ የመስቀል ክብረ በዓል ነው፤ መልካም በዓል” በማለት ተሰናበትኩት።
ከዚያም ከበሬው በመራቅ ወደ እስጢፋኖስ ክብረ በዓል አመራሁ። ክብረ በዓሉ ሲገባደድ የበሬውን ሁኔታ ለማየት ወደነበረበት ቦታ አመራሁ። በኢትዮጵያ ቦታ ያስገባሁትን በሬ ተጋድሞ ክፉኛ ሲንቀጠቀጥ ሳይ እምባየ መጣ ፥ በሬውን ሰዎች ከብበውታል፡ ፖሊሶች ግን በአላቦውው አልነበሩም። በዚህ ወቅት ካሜራየን አውጥቼ በስተመጨረሻ የሚታየውን ቪድዮ ቀረጽኩ። በቀጣዩ ቀን የበሬው ባለቤት መገኘቱንና በሬውም ከእስጢፋኖስ ቤተክርስቲያን ግቢ መውጣቱን ተነገረኝ።
“አይ! ይህ በሬ ሊያሳየን የፈለገው አንድ ትልቅ ነገር አለ” የሚለው ሃሳብ እስከ አሁን ድረስ አልለቀቀኝም።
ለመሆኑ፦
- በሬው የማን ነው?
- በሬውን ማን አመጣው?
- በሬው እንዴት ጥብቅ ፍተሻ ሲደረግበት ወደ ነበረው ወደ መስቀል አደባባይ ሊገባ ቻለ?
- በሬው ወደ ቅ/እስጢፋኖስ ቤተክርስቲያን ለምን ተወሰደ?
- በሬው ፌደራል ፖሊሶችን ለምን አሳሰባቸው? በጠዋትስ ለምን በእስጢፋኖስ ቤተክርስቲያን ተገኙ?
- + በመስቀል አደባባዩ ቦንብ ፍንዳታና ግድያ
- + ሆራ ደብረዘይት ለመስዋዕት በተከሰከሰው የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን
- + በባሕር ዳር እና በአዲስ አበባ በተፈጸመው ኢትዮጵያውያን ጄነራሎች ግድያ
Blogger Comment
Facebook Comment