የኢትዮጵያ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በተለያየ መንገድ ጥቃት እየደረሰባት ነው፤

ዘርአዳዊት ዘ-ኢትዮጵያ

የኢትዮጵያ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በተለያየ መንገድ ጥቃት እየደረሰባት ነው፤ ባለፉት ፵፭ ዓመታት ቤተክርስቲያን በመንግስት ደረጃ ስትገፋ ነው የⷆየችው።

አዎ! በሕገ–ወጥ መንግሥት በደንብ የተቀነባበረ ጂሃድ በተዋሕዶ ላይ እየተካሄደ ነው።

አሁን አሁንማ አይደንቀንም፤ ልክ እነ ጄነራል አሳምነውን በሚገድሉበት ሰሞን ግራኝ ዐቢይ አሕመድ አሊና የጂሃድ አጋሩ ደመቀ መኮንን ሃሰን ቀደም ብሎ የተዘጋጀውን ምክኒያት እየሰጡ ከኢትዮጵያ ሹልክ ብለው እንደወጡት አሁንም የቁልቢ ገብርኤልን አባታችንን ሲገድሏቸው ወደ ደቡብ ኮርያ እና አሜሪካ ሸሽተዋል። ሞኙ ወገኔ ይህን ሁሉ ዘመን በድክመቱ ገዳዩን መንግስቱ ኃይለማርያምን ለፍርድ ሳያቀርበው በመቅረቱ ሁሉም ንቀውታል፤ ግን ዛሬ እናንተን በድጋሚ እዲሁ ዝም አይላችሁም፤ ምንም ሳታደርጉለት ተቀብሮ የቆየውን ፍቅሩን በነጻ ከሰጣችሁ ሕዝብ የትም አታመልጧትም።

እነዚህን ከሃዲዎች ለፍርድ ለማቅረብና ለመቅጣት የሚያንገራግር የተዋሕዶ ልጅ እራሱ እንደ ክሃዲ ነው የሚቆጠረው። በዚያ ላይ ስለ ራሱ ሰዎች የማያስብ፣ ስለ ግል ራሱም ሆነ ስለሌሎችም ሊያስብ የማይችል ቆሞ የሞተ፤ ሕይወት እያለው በድን የሆነ ሰው ብቻ ነው።
ለክፋት ድል መቀዳጀት አስፈላጊው ብቸኛው ነገር ጥሩ ሰዎች ዝም ማለታቸው ወይንም ምንም ነገር አለማድረጋቸው ነው፡፡

ከአለመናገር ደጃዝማችነት ይቀራል እንደሚባለው ዝምታን አስወግደው ለእውነት የቆሙ፣ ለነጻነትና ለፍትህ የሚናገሩ ብዙ ኢትዮጵያውያን በተለያየ ቦታ ዝምታ ይብቃ በማለት ብቅ ብቅ በማለት ላይ መሆናቸው በጣም የሚያስደስት ነው።

በተዋሕዶ ልጆች ላይ፤ ክርስትያን በመሆናቸዉ ብቻ ግፍ ሲፈጸምባቸው፣ ሲፈናቀሉ፣ ሲሰደዱ፣ ሲታረዱ፣ ሲቃጠሉና ሲታነቁ፣ ዝም ጭጭ ማለት ከክህደት ይቆጠራል። አውሬዎቹ አሕዛብ ክርስቲያን ወንድሞቻችንን እና እህቶቻችንን በተከታታይ ሲገድሏቸውና ከእነ ቤተክርስቲያናቸው ሲያቃጥሏቸው ዝም ማለትና ቆሞ መመልከት ትልቅ ክህደት ነው፤ በ ፩ ጢሞቲዎስ ፭፥፰ ላይ የእርሱ ስለሆኑት ይልቁንም ስለ ቤተሰቦቹ የማያስብ ማንም ቢሆን ሃይማኖትን የከዳ ከማያምን ሰዉ ይልቅ የከፋ ነዉ ሲል ቅዱስ ጳዉሎስ ነግሮናል።

[፩ኛ ወደ ጢሞቴዎስ ምዕራፍ ፭፥፰]
" ነገር ግን ለእርሱ ስለ ሆኑት ይልቁንም ስለ ቤተ ሰዎቹ የማያስብ ማንም ቢሆን፥ ሃይማኖትን የካደ ከማያምንም ሰው ይልቅ የሚከፋ ነው። "
Share on Google Plus

ስለ የተለጠፈበት ቀን

    Blogger Comment
    Facebook Comment