ዘርአዳዊት ዘ-ኢትዮጵያ
በምስራቅ ሃረርጌ ዞን የቁልቢ ገብርኤል ገዳም አስተዳዳሪ የሆኑት መልዓክኃይል ቆሞስ አባ እንቁስላሴ ከቅዳሴ መልስ በቤታቸው ሞተው መገኘታቸውን ተከትሎ በተነሳ ተቃውሞ አንድ ሰው ሞቶ 5 ሰዎች መቁሰላቸውን ምንጮች ለቪ.ኦ.ኤ (VOA) አስታውቁ፡፡
ወገን ልብ በል፤ ዜናውን አስቀድሞ ያቀረበው የአሜሪካው ድምጽ ቪ. ኦ. ኤ ነው።
የብፁዕ አባታችን ነፍስ እግዚአብሔር ከቅዱሳን አበው ነፍስ ጋር ይደምርልን!
[የማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ ፳፬፥፮፡፲፫]
"ጦርንም የጦርንም ወሬ ትሰሙ ዘንድ አላችሁ፤ ይህ ሊሆን ግድ ነውና ተጠበቁ፥ አትደንግጡ፤ ዳሩ ግን መጨረሻው ገና ነው።
ሕዝብ በሕዝብ ላይ መንግሥትም በመንግሥት ላይ ይነሣልና፥ ራብም ቸነፈርም የምድርም መናወጥ በልዩ ልዩ ስፍራ ይሆናል፤ እነዚህም ሁሉ የምጥ ጣር መጀመሪያ ናቸው።
በዚያን ጊዜ ለመከራ አሳልፈው ይሰጡአችኋል ይገድሉአችሁማል፥ ስለ ስሜም በአሕዛብ ሁሉ የተጠላችሁ ትሆናላችሁ። በዚያን ጊዜም ብዙዎች ይሰናከላሉ እርስ በርሳቸውም አሳልፈው ይሰጣጣሉ እርስ በርሳቸውም ይጣላሉ፤ ብዙ ሐሰተኞች ነቢያትም ይነሣሉ ብዙዎችንም ያስታሉ፤ ከዓመፃም ብዛት የተነሣ የብዙ ሰዎች ፍቅር ትቀዘቅዛለች። እስከ መጨረሻ የሚጸና ግን እርሱ ይድናል።"
Blogger Comment
Facebook Comment