ዘርአዳዊት ዘ-ኢትዮጵያ
በነዚህ የበዓላት ቀናት ትዝ ሲሉኝ የሚውሉት በዚህ በክረምት የተፈናቀሉትና ከቦታ ቦታ እየተዘዋወሩ በብርድና ቸነፈር የሚጎሳቆሉት ሕፃናት ናቸው።
"ከነዚህ ከታናናሾቹ አንዱን እንዳትንቁ ተጠንቀቁ፤ መላእክቶቻቸው በሰማያት ዘወትር በሰማያት ያለውን የአባቴን ፊት ያያሉ እላችኋለሁና።"
ፍልሰታ ለማርያም – ነሐሴ ፲፮
የእናታችን ወላዲተ አምላክ ትንሣኤና እርገት መታሰቢያ – በጾመ ፍልሰታ ወቅት ብዙዎች ከቤታቸው ተለይተው በመቃብር ቤት ዘግተው፣ አልጋና ምንጣፍ ትተው፣ በመሬት ላይ ተኝተው ዝግን ጥሬ እፍኝ ውኃ እየቀመሱ በጾምና በጸሎት በመትጋት በታላቅ ተጋድሎ ይሰነብታሉ፡፡ በሰሙነ ፍልሰታ ምእመናን ለእናታችን ድንግል ማርያም ያላቸውን ጽኑና ጥልቅ ፍቅር የሚያሳዩበት ነው፡፡

ጌታችን ሦስት መዓልት ሦስት ሌሊት በከርሰ መቃብር ቆይቶ ሙስና መቃብር ሳያገኘው፣ መግነዝ ፍቱልኝ መቃብር ክፈቱልኝ ሳይል በሥልጣኑ እሑድ በመንፈቀ ሌሊት እንደተነሣ ሁሉ እርሷም በተቀበረች በሦስተኛው ቀን ማኅደረ መለኮት ናትና ሙስና መቃብር ሳያገኛት መግነዝ ፍቱልኝ፣ መቃብር ክፈቱልኝ ሳትል የልጅዋ ሥልጣን ኃይል ሆኗት መነሣቷን ትንሣኤዋ "ከመ ትንሣኤ ወልዳ፤ እንደ ልጅዋ ትንሣኤ" ነው ተብሎ ሲከበርላት ይኖራል፡፡
በዚሁ በነሐሴ ፲፮ ቀን የሰማእቱ የቅዱስ ጊዮርጊስ ፍልሰቱ ነው፡፡ ሥጋው ከፋርስ ሀገር ወደ ሀገሩ ወደ ልዳ በክብር የፈለሰበት ነው፡፡ ፍልሰቴን ከፍልሰትሽ አድርጊልኝ፣ ብሎ ለምኗት ስለነበር ፍልሰቱ ከእመቤታችን ፍልሰት ጋር እንዳሰበው ሆኖለታል፡፡ ስለዚህም እርሷን መውደዱ የሚያውቁ ሥእሉን ከሥእሏ አጠገብ ይስላሉ፡፡ በስሙ ለሚማጸኑ የድኅነት ወደብ ይሆን ዘንድ፡ ፡
የእናታችን ወላዲተ አምላክ ድንግል ማርያም አማላጅነቷ አይለየን አሜን ፡፡
Blogger Comment
Facebook Comment