ተዋሕዶ አባቶች ሲታረዱ፣ አብያተ ክርስቲያናት በእሳት ሲጋዩ፣ ኢንጂነሮች እና ጄነራሎቹ ሲገደሉ፣ ጋዜጠኞች ወደ ቀዝቃዛማና ጨለማ ጉዳጓድ ውስጥ ሲወረወሩ፣ እናቶችን ከመኖርያ ሲፈናቀሉ፣ ህፃናትና እርጉዞች ሲንገላቱ፣ ዜጎችን ከእኔ ጋር አልተደመራችሁም እየተባሉ ከሥራዎቻቸው ሲባረሩ፣ ሰው በጠራራ ፀሃይ ተዘቅዝቆ ሲስቀል፣ ባንኮችና ትራንስፎርመሮች ሲዘረሩ፣ ሦስት ሚሊየን ኢትዮጵያውያን ከትውልድ ቦታቸው እየተፈናቀሉ ሲራቡ፤ ይህ በመላው ዓለም ለሰብዓዊ መብት ቆሚያለሁ፣ የሞራል ሞኖፖል አለኝ የሚለው ግብዝ ተቋም፡ ስለእነዚህ ከፍተኛ የሰብአዊ መብት ረገጣዎች እስካሁን ድረስ የተናገረው ነገር የለም፤ ጭጭ ብሏል።
Blogger Comment
Facebook Comment