ዘርአዳዊት ዘ-ኢትዮጵያ
ግብጽና ቱርክ ታሪካዊ ጠላቶቻችን ናቸው፤ ወዳጆቻችን ሊሆኑ ከማይችሉ ብዙ ሃገራት መካከል ሦስቱ ግብጽ፣ ቱርክ እና ሳውዲ አረቢያ ናቸው። ከአምስት መቶ ዓመታት በፊት በተለይ ግብጽ እና ቱርክ ነበሩ እርኩሱን ግራኝ አህመድን በክርስቲያን ኢትዮጵያ ላይ ያነሳሱት። ዛሬም ጂሃዱን መጀመሪያ ለስለስ ባለ መልክ በባንኮች፣ ትምህርት ቤቶች፣ ምግብ ቤቶች እና ዳቦ ቤቶች በማጧጧፍ ላይ ይገኛል፤ "እድሜ" ለዶ/ር ግራኝ አሕመድ።
ክፍላ ፩. በዚህ ወር መጨረሻ ላይ ግብጽ የንግድ ባንክ ቅርንጫፏን በሀገረ ኢትዮጵያ ልትዘረጋ ነው። ማን ፈቅዶላት? መገመት አያዳግትም፤ ያው ዳግማዊ ግራኝ አብዮት አሕመድ ነው የሚሆነው። ባንክ ዘራፊዎቹ የቄሮ አጋንንት ያስተረፉትን የድሃ ኢትዮጵያውያን ገንዘብ ግብጽ በይፋ እንድትሰርቅ ፈቃድ የተሰጣት ይመስላል። ለመሆኑ የትኛው ኢትዮጵያዊ ነው ገንዘቡን በግብጽ ባንክ ለማስቀመጥ የሚሻ???
ክፍል ፪. የክርስቶስ ተቃዋሚዋ ቱርክ የኢትዮጵያ ህፃናትን በእስልምና ቫይረስ ለመበከል "ትምህርት ቤቶችን"
ለመረከብ ወስናለች ቱርክ ከጉላን እንቅስቃሴ ጋር ትስስር ያላቸውን "ትምህርት ቤቶች" ለመውረስ ወስናለች። እነዚህ በኢትዮጵያ የሚገኙትና ከጉላን እንቅስቃሴ ጋር የተቆራኙን እነዚህን እስላማዊ ተልዕኮ ያላቸውን ትምህርት ቤቶች አምባገነኑ የቱርክ መሪ ኤርዶጋን በቁጥጥር ስር ለማዋል የወሰነው ከሦስት ዓመታት በፊት ፌቱላ ጉላን የተባለው ቱርካዊ ሸህ የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ አድርጎብኝ ነበር በሚል ውንጀላ ነው።
ሸህ ፌቱላ ጉላን የቱርኩ ፕሬዚደንት ኤርዶጋን የቅርብ ባላጋር የነበረና መጀመሪያ ላይም ስልጣኑን እንዲይዝ የረዳው ሸህ ነበር። ነገር ግን ይህ የሲ.አይ.ኤ ወኪል እንደሆነ የሚነገርለት ሸሁ በዩናይትድ ስቴትስ በስደት መኖር ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ በኤርዶጋን ፖለቲካዊ ድራማ ላይ ተቀናቃኝ የሆነውን ሚና እንዲጫወት ተደርጓል።
ኢትዮጵያዊው ንጉሥ ዳዊት "ጠላት ስጠኝ" ብሎ ሲፀልይ እንደነበረው ፕሬዚደንት ኤርዶጋንም ሊቆጣጠረው የሚችለውን ተቃዋሚ (Controlled Opposition) በፌቱላ ጉላን በኩል አግኝቷል። ልክ (ዶ/ር አሕመድ በጄነራል አሳምነው በኩል ለመፍጠር እንደሞከረው – የኤርዶጋንን ፈለግ እየተከተለ ነው)። ሁለቱም ቱርኮች፡ ዶ/ር አሕመድን ጨምሮ፡ የዲያብሎስ ወኪሎች ናቸው። ኢትዮጵያን ጨምሮ በመላው ዓለም የሚገኙት "ትምህርት ቤቶች" በሁለቱ ግለሰቦች ትብብርነት ነው የተከፈቱት። ትምህር ቤቶቹ በጉላን እንቅስቃሴ በቀስተ ደመና ፋውንዴሽን ስም ሲመዘገቡ አሁን ደግሞ መንግስታዊ የሆነው የማአሪፍ ፋውንዴሽን ተረክቧቸዋል። ከመዋዕለ ህፃናት እስከ ዩኒቨርሲቲ ድረስ ለመስፋፋት ህልም አላቸው።
ለመሆኑ የትኞቹ ኢትዮጵያውያን ናቸው ልጆቻቸውን ወደ ቱርክ እስላማዊ "ትምህርት ቤቶች" የሚልኩት?
Blogger Comment
Facebook Comment