ቀዳማዊ አጼ ቴዎድሮስ በዙፋን ስማቸው ወልደ አምበሳ እ.ኤ.አ ከ1413-1416 ዓ.ም. የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት የነበሩ ናቸው። የቀዳማዊ አጼ ዳዊትና የንግስት ጺዮን መንገሻ ልጅ ነበሩ፡፡ ታሪክ አጥኝው ዋሊስ በድጅ ቀዳማዊ ቴወድሮስ ለ3ዓመት [1]ነገሡ ቢልም በብዙ ታሪክ አጥኝወች ዘንድ ለ9 ወር ብቻ እንደነገሡ ይታመናል። ምንም እንኳ የነገሡበት ዘመን አጭር ቢሆንም የኒህ ንጉሥ ዘመን በጥንቱ የኢትዮጵያውያን ትዝታ ውስጥ ምንጊዜም የማይረሳና እጅግ ተወዳጅ ነበር። በ18ኛው ክፍለ ዘመን ጎንደር ተጉዞ የነበረው የስኮትላንዱ ጄምስ ብሩስ እንዲህ ሲል ይዘግባል፦
ቀዳማዊ ቴወድሮስ "ሃይማኖተኛና የሃይማኖት ድርሳናትን በጣም እሚወዱ" እንደነበር ዋሊስ በድጅ የተሰኘው የታሪክ አጥኝ ስንክሳሩን በመተርጎም አስቀምጧል። በኋላ ዳግማዊ አጼ ቴዎድሮስ እንደፈጸሙት የቤተክርስቲያናንን መሬት ለገበሬው አክፋፍለዋል። ይህም አጼይኩኖ አምላክ ለቤተክርስቲያን ይገባል ያሉትን 1/3ኛ የአገሪቱን መሬት ስምምነት የጣሰ ነበር። [3] እኒሁ ንጉስ ወደ እየሩሳሌም ለመጓዝ ፈልገው አቡነ ማርቆስ ለደህንነታቸው በመስጋት እንዳይሄዱ አድርገዋል።
ምንም እንኳ የቤተ ክርስቲያንን ይዞታ ለገበሬወች ቢያከፋፍሉም እኒሁ ንጉስ በኋላ ላይ በተዋህዶ ቤተከርስቲያን ቅዱሳን ተርታ ተመደቡ። ለዚህም ምንክንያታቸው ሃይማኖተኝነተቸው፣ ለድሆች የነበራቸው ሩህሩህነትና በጊዜው እንግዳ የነበረው በአንድ ሚስት መወሰናቸው ነበር።
ቴዎድሮስ ከአዳል ጋር ሲዋጉ አዋሽ ወንዝ ማዶ በጀግንነት አለፉ፣ በተድባባ ማርያምም ተቀበሩ። [4] [2] ሆኖም አጼ በእደ ማርያም ከተድባባ ማርያም አውጥተው አጽሙ በአጥሮንሳ ማርያም ቤተክርስቲያን፣ መርሐ ቤቴ እንዲያርፍ አደርጉ[5]።
ከቴዎድሮስ ማለፍ ቀጥሎ ታናሽ ወንድማቸው ዓፄ ይስሐቅ ዙፋን ላይ ወጡ።
2.
^ Taddesse Tamrat, Church and
State in Ethiopia (Oxford: Clarendon Press, 1972), p. 153n.5
3.
^ "Local History in Ethiopia" The
Nordic Africa Institute website (accessed 28 January 2008)
Blogger Comment
Facebook Comment